Tender Detail

Tender Details

  • Company ወንዶ ንግድና ኢንቨስትመንት ኩባንያ ኃ/የተ/የግል ማህበር
  • Address መስቀል አደባባይ እስጢፋኖስ ቤተክርስቲያን ፊት ለፊት ፊንፊኔ ህንፃ 7ኛ ፎቅ : አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 011-5-52-10-09
  • Website
  • Deadline14 Oct 2026, 2:00 PM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price300(ሦስት መቶ ብር)
  • Bid Securityብር 50,000.00 (ሀምሳ ሺህ) በሲ.ፒ.ኦ በባንክ በተረጋገጠ ቼክ
  • opening dateበዚሁ ዕለት ከቀኑ 8፡30 ሰዓት በዋናው መ/ቤት አዲስ አበባ ይከፈታል
  • Categories Spare Parts , Vehicle Spare Parts

ወንዶ ንግድና ኢንቨስትመንት ኩባንያ ኃ/የተ/የግል ማህበር የ2019 ዓ.ም. በጀት ዓመት 5L ቶዮታ ፒካፕ መኪና ሞዴል 2005 መኪና ዕቃ መለዋወጫ ግዥ በግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

ወንዶ ንግድና ኢንቨስትመንት ኩባንያ ኃ/የተ/የግል ማህበር


በድጋሚ የወጣ የቶዮታ መኪና ፒካፕ 5L ሞዴል 2005 ዕቃ መለዋወጫ ግዥ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

ወንዶ ንግድና ኢንቨስትመንት ኩባንያ ኃ/የተ/የግል ማህበር የ2019 ዓ.ም. በጀት ዓመት 5L ቶዮታ ፒካፕ መኪና ሞዴል 2005 መኪና ዕቃ መለዋወጫ ግዥ በግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

በመሆኑም ከዚህ በታች በተዘረዘረው መስፈርት መሰረት የምታሟሉ ተጫራቾች በጨረታው እንድትሳተፉ እየገለጽን፡-

  1. ተወዳዳሪዎች በጨረታ ለመወዳደር የሚችሉ ለመሆናቸው የንግድ ፈቃድ፣ የሙያ ማረጋገጫ ሰርተፊኬትና የዘመኑን ግብር አጠናቀው ስለመከፈላቸው ማስረጃ ከሚመለከተው አካል ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  2. ተጫራቾች በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ በጨረታ ለመሳተፍ የሚችሉ ለመሆናቸው ከሚመለከተው ሕጋዊ አካል የተፃፈ የታደሰ የታክስ ክሊራንስ ማስረጃ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት ምዝገባ ሰርተፍኬት ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማያያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
  3. ተጫራቾች ከዚህ ቀደም ከሠሩባቸው መ/ቤቶች ለሠሩበት ምስክርነት የመልካም ሥራ አፈፃፀም ማስረጃዎችን ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  4. ተጫራቾች ጨረታውን 300 /ሦስት መቶ ብር/ በመክፈል የጨረታ ሰነድ መግዛት ይችላሉ፡፡
  5. ማንኛውም ተጫራች ጨረታውን ለመወዳደር የሚያስችል ብር 50,000.00 (ሀምሳ ሺህ) የጨረታ ማስከበሪያ በሲ.ፒ.ኦ በባንክ በተረጋገጠ ቼክ ከጨረታው ሰነድ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  6. ፋይናንሻል እና ቴክኒካል በኦርጂናል እና በኮፒ እያንዳንዱ ሰነድ ላይ የድርጅታቸውን ማህተምና ፊርማ በማሳረፍና በፖስታ በማሸግ በጨረታ ሣጥን ውስጥ ዋናው መ/ቤት አ.አ 7ኛ ፎቅ ማስገባት አለባቸው፡፡
  7. አሸናፊው ድርጅት በአምስት ቀናት ውስጥ ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ 10% (አስር በመቶኛ የውል ማስከበሪያ በማስያዝ የስምምነቱን ውል መፈረም አለበት፡፡
  8. የጨረታ መዝጊያው ሰዓት ከደረሰ እና የጨረታ ሣጥኑ ከታሸገ በኋላ የሚቀርቡ የጨረታ ሰነዶች ተቀባይነት አይኖራቸውም፡፡
  9. ማንኛውም ተጫራች በሌላ ተጫራች ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይችልም፡፡
  10. ጨረታው አ.አ መስቀል አደባባይ ፊንፊኔ ሕንፃ ወንዶ ንግድና ኢንቨስትመንት ኩባንያ ኃ/የተ/የግ/ማህበር ፋይ/ግዢ/ንብ/አስ/መምሪያ 7ኛ ፎቅ የሚከፈት ይሆናል፡፡
  11. ጨረታው በሚከፈትበት ቀን ለመገኘት ፍላጎት ያላቸው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ባይገኙም የሚከፈት ይሆናል፡፡
  12. የጨረታ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት 16ኛው (አስራ ስድስተኛው) ቀን ላይ ቀኑ የሥራ ቀን ከሆነ በዕለቱ ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚሁ ዕለት ከቀኑ 8፡30 ሰዓት በዋናው መ/ቤት አዲስ አበባ ይከፈታል፡፡
  13. የጨረታ መዝጊያው ሰዓት ከደረሰ እና የጨረታ ሣጥኑ ከታሸገ በኋላ የሚቀርቡ የጨረታ ሰነዶች ተቀባይነት አይኖራቸውም፡፡
  14. ኩባንያው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

አድራሻ፡-

  • ወንዶ ንግድና ኢንቨስትመንት ኩባንያ ኃ/የተ/የግ/ማህበር፡- መስቀል አደባባይ እስጢፋኖስ ቤተክርስቲያን ፊት ለፊት ፊንፊኔ ሕንፃ 7ኛ ፎቅ
  • ስልክ ቁጥር፡- 011 552 10 09 /011 552 14 58/
    ፖ.ሣ.ቁ. 9515 ፋክስ 011 551 3654
    አ/አበባ

ወንዶ ንግድና ኢንቨስትመንት ኩባንያ ኃ/የተ/የግል ማህበር

✨ messages.ai_summary
Wendo Trading and Investment Company invites bids for the supply of spare parts for a 5L Toyota pickup, model 2005. Bidders must provide a valid business license, professional certificate, tax clearance, VAT registration, and proof of good performance. The company reserves the right to cancel the tender.
Save Tender