Tender Detail

Tender Details

  • Company በቦሌ ክፍለ ከተማ ኤረር ጤና ጣቢያ
  • Address Addis Ababa:Ethiopia, Phone: 011-6-39-50-33
  • Website
  • Deadline09 Oct 2026, 10:00 AM
  • magazineAddis Zemen
  • Bid Document Priceለእያንዳንዱ ሎት የማይመለስ ብር 100.00 / አንድ መቶ ብር/
  • Bid Securityበሎት: ከብር 3,000.00 እስከ 25,000.00 (በባንክ በተረጋገጠ CPO)
  • opening dateበዚያው ቀን ከ ጠዋቱ በ 4:30 ሰዓት
  • Categories Finishing Work , Medical Equipment And Supplies , Office Machines And Computers

ለቦሌ ክፍለ ከተማ ኤረር ጤና ጣቢያ የሚገዛው ተዛማች አገልግሎት

በቦሌ ክፍለ ከተማ ኤረር ጤና ጣቢያ


የጨረታ ማስታወቂያ

የግዥ መለያ ቁጥር ቦሌ/ክ/ከ/ኤ/ጤ/ጣ/01/2019 ዓ.ም

የጨረታ ቁጥር 01/2019

ለቦሌ ክፍለ ከተማ ኤረር ጤና ጣቢያ የሚገዛው ተዛማች አገልግሎት:-

ተ.ቁየዕቃው አይነትየሚያስይዙት ሲ.ፒ.ኦ በብር
1የኤሌክትሮኒክስ፣ ሰርቨር እና ለሰርቨር ዝርጋታ የሚያስፈልጉ እቃዎች25,000.00
2አላቂ የቢሮ እቃዎች10,000.00
3አላቂ የጽዳት እቃዎች10,000.00
4የፈርኒቸር እቃዎች10,000.00
5የህትመት ስራዎች5,000.00
6ልዩ ልዩ የጥገና መሳሪያዎችን እና ብረታ ብረቶች3,000.00
7የተለያዩ መድሀኒቶች፣ ሬኤጀንቶች እና የህክምና መሳሪያዎች10,000.00
8የደንብ ልብስ10,000.00
9የፓርቲሽን ስራዎች እና የአሸጊት ስራዎች25,000.00
10የመኪና ኪራይ5,000.00

ስለሆነም መስፈርቱን የሚያሟሉ ተጫራቾች ቀርበው መወዳደር ይችላሉ::

  1. የሀገር ውስጥ ተጫራቾች አግባብነት ያለው በዘመኑ የታደሰ ንግድ ስራ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ::
  2. የሀገር ውስጥ ተጫራቾች አግባብነት ያለው በዘመኑ የታደሰ ንግድ ምዝገባ ማቅረብ የሚችሉ::
  3. የሀገር ውስጥ ተጫራቾች ግብር የመክፈል ግዴታቸውን የተወጡ መሆኑን የሚያረጋግጥ ከግብር ሰብሳቢው ባለስልጣን ጨረታ ላይ መሳተፍ እንዲችሉ የተሰጠ ክሊራንስ/ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው::
  4. የሀገር ውስጥ ተጫራቾች በአቅራቢዎች ዝርዝር ላይ የተመዘገቡ ለመሆናቸው የተጫራቾች የምስክር ወረቀት ያላቸው::
  5. የሀገር ውስጥ ተጫራቾች የግብር ከፋይነት መለያ ሰርተፊኬት ማቅረብ አለባቸው::
  6. የሀገር ውስጥ ተጫራቾች የቫት ተመዝጋቢ የሆኑና ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው::
  7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ለእያንዳንዱ ሎቶች በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ/ CPO/ ማቅረብ አለባቸው::
  8. ተጫራቾች በአማርኛ ቋንቋ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ለእያንዳንዱ ሎት የማይመለስ የኢትዮጵያ ብር 100.00 / አንድ መቶ ብር/ በመክፈል ቦሌ/ክ/ከተማ ወረዳ 07 ኤረር ጤና ጣቢያ አለማየሁ ህንፃ ፊት ለፊት ገባ ብሎ ወይም ቅዱስ ኡራኤል ቤተ ክርስቲያን አጠገብ 5ኛ ፎቅ ላይ መውሰድ ይችላሉ::
  9. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ ሲያቀርቡ ቫት ያጠቃለለና ከላይ የተጠቀሱትን ማስረጃዎች አሟልተው ለሚወዳደሩበት ሎት በእያንዳንዱ ሎት ኦርጅናል እና ኮፒ በታሸገ ኤንቬሎፕ ቴክኒካል እና ፋይናንሺያል በመለየት ፖስታው ላይ የሚወዳደሩበትን ሎት ለየብቻ በመለየት/ በመግለጽ በጤና ጣቢያው ግዥ ቡድን ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ እስከ አስራ አንደኛው (11ኛው) የስራ ቀን 2019 ዓ.ም. ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት ብቻ ማስገባት ይኖርባቸዋል። ሆኖም ግን ይህ ቀን የስራ ቀን ካልሆነ ቀጥሎ ባለው የመጀመሪያው የስራ ቀን የሚገባ መሆኑን እንገልጻለን::
    ተጫራቾች በተወዳደሩበት የእቃ አይነት ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ባሉት ሁለት ቀናት ናሙና የሚያስፈልጋቸው ሎቶች ማቅረብ አለባቸው::ከሰነዱ ጋር የተያያዘውን ስፔስፊኬሽን ላይ ማህተም በማድረግ መመለስ አለባቸው ዘግይቶ /ሰዓት/ቀን አሳልፎ የመጣ ሰነድ ተቀባይነት አይኖረውም::
  10. ጨረታው በዚያው ቀን ከ ጠዋቱ በ 4:30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ግዥ ቡድን ባዘጋጀው አዳራሽ 5ኛ ፎቅ ይከፈታል::
  11. ተጫራቾች የጨረታ አሸናፊ ሆነው የተገኙባቸውን ዕቃዎች ከአጠቃላይ ዋጋ 10% የውል ማስከበሪያ በማስያዝና ከግዥ ውል ስምምነት መፈፀም ይኖርባቸዋል::
  12. ለጥቃቅንና አነስተኛ ተደራጅተው ለሚወዳደሩ ለሚወዳደሩበት ሎት አምራች ስለመሆናቸው የሚገልፅ ከአደራጃቸው ወረዳ በበላይ ኃላፊ ተፈርሞ ማምጣት አለበት::
  13. ከላይ የተጠቀሱትን መስፈርት ሳያሟሉ በጨረታ ላይ ለመሳተፍ መሞከር ከጨረታው ያሰርዛል::
  14. መ/ቤቱ ጠቅላላ ለጨረታው ከቀረበው ብዛት 20% ከፍና ዝቅ ብሎ የግዥ ትእዛዝ ሊሰጥ ይችላል
  15. መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
  16. የተሰረዘ የተደለዘ ግልጽነት የሌለው የጨረታ ሰነድ ይሰረዛል::

አድራሻ:-ቦ/ክ/ከተማ ወረዳ 07 ኤረር ጤና ጣቢያ ከመገናኛ ወደ ጎሮ በሚወስደው ጃክሮስ አለፍ ብለው አለማየሁ ህንፃ ፊት ለፊት ገባ በማለት ወይም ቅዱስ ኡራኤል ቤተ ክርስቲያን አጠገብ 5ኛ ፎቅ ግዥ ቡድን ---ፎቅ ያነጋግሩን::

ስልክ ቁጥር:- 011-6-39-50-33

ወረዳ 07 ኤረር ጤና ጣቢያ

✨ messages.ai_summary
Supply of electronics, server equipment, consumable office and cleaning supplies, furniture, printing, maintenance tools, medicines, reagents, medical equipment, uniforms, partition and plastering works, and vehicle rental for Erer Health Station. Open to eligible domestic bidders meeting licensing, tax, VAT, and supplier registration requirements.
Save Tender