Tender Detail

Tender Details

  • Company መሸረቅ የገበያ ማዕከል አክሲዮን ማህበር
  • Address , Phone:
  • Website
  • Deadline08 Oct 2026, 5:00 PM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateበ11ኛው ቀን መስከረም 29/2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት
  • Categories Accounting & Auditing , Audit Service

መሸረቅ የገበያ ማዕከል አክሲዮን ማህበር ሕጋዊ ፈቃድ ያላቸውን የውጭ ኦዲተሮችን አወዳድሮ የ2018 ዓ.ም በጀት ዓመት ሂሳብ ማስመርመር ይፈልጋል፡፡

መሸረቅ የገበያ ማዕከል አክሲዮን ማህበር


የውጭ ሂሳብ ኦዲት ጨረታ ማስታወቂያ

መሸረቅ የገበያ ማዕከል አክሲዮን ማህበር ሕጋዊ ፈቃድ ያላቸውን የውጭ ኦዲተሮችን አወዳድሮ የ2018 ዓ.ም በጀት ዓመት ሂሳብ ማስመርመር ይፈልጋል፡፡

በዚሁ መሰረት ተጫራቾች

  1. አውቅና ያላቸውና ከዋናው ኦዲተር መስሪያ ቤት የሙያ ብቃት ማረጋገጫ የተሰጣቸው በመስኩ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑ ግብር የከፈሉና የገበያ ማዕከል አክሲዮን ማህበራትን ሂሳብ በመመርመር የሥራ ልምድ ያላቸው መሆን ይኖርበታል፡፡
  2. የማህበሩን ሂሳብ ለመመርመር የሚያስችሉትን ዋጋ መጠን ሥራውን አጠናቀው የሚያስረክቡበትን የጊዜ ገደብ መጥቀስ ይኖርበታል፡፡
  3. ተወዳዳሪዎች ዋጋ ከማቅረባቸው በፊት የማህበሩን የሂሳብ ሰነድ አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 1 ሲኒማ ራስ ሐጂ ለገሰ ሸረፋ ህንፃ 5ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 503/504 በሚገኘው የማህበሩ ጽ/ቤት መመልከት ይኖርባቸዋል፡፡
  4. ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ማለትም ከሰኞ እስከ አርብ ከጠዋቱ 3፡00 እስከ ቀኑ 6፡00 እና ከቀኑ 7፡00 ሰዓት እስከ ቀኑ 10፡00 ሰዓት እንዲሁም ቅዳሜ ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት እስከ ቀኑ 6፡00 ሰዓት ባለው ጊዜ የጨረታ ሰነዱን በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ለጽ/ቤቱ ማቅረብ ይችላሉ፡፡
  5. የጨረታው ማስታወቂያ በጋዜጣ ታትሞ በወጣ በ11ኛው ቀን መስከረም 29/2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በማህበሩ ጽ/ቤት ይከፈታል፡፡

ማሳሰቢያ፡-

ማህበሩ ለሥራው የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

አድራሻ፡- አ/ከ/ከተማ ወረዳ 01 ሲኒማ ራስ ሐጂ ለገሠ ሸረፋ ህንፃ 5ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 503/504

ስልክ ቁጥር 0118 27 76 37/0925 59 89 14/ 0925 69 65 93/0980 63 0898

መሸረቅ የገበያ ማዕከል አክሲዮን ማህበር

✨ messages.ai_summary
Mesherek Market Center Share Company seeks licensed external auditors to audit its 2018 fiscal year accounts. Bidders must be recognized, hold a competency certificate from a main audit firm, have a relevant business license, be tax-compliant, and have experience auditing market center share companies.
Not stated in the notice: bid security, bid document price. Check the original document or ask the issuer.
Save Tender