Tender Detail

Tender Details

  • Company Ethiopian Press Agency (የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት)
  • Address አራት ኪሎ ከብርሃንና ሰላም ማተሚያ ቤት ፊት ለፊት : አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 011-1-56-98-69
  • Websitehttps://press.et/
  • Deadline14 Oct 2026, 10:00 AM
  • magazineAddis Zemen
  • Bid Document Price100 ብር (የማይመለስ)
  • Bid Securityበሎት (CPO/ቢድቦንድ): ሎት-1 ብር 254,503.60፣ ሎት-2 ብር 120,000.00፣ ሎት-3 ብር 50,000.00፣ ሎት-4 ብር 50,000.00
  • opening dateበዕለቱ 4፡30 (በ16ኛው ቀን)
  • Categories Food Items And Drinks , Computer Laptop And Accessories , Vehicle Spare Parts

የመኪና መለዋወጫ፣ አድቫንስ ዲስክቶፕ፣ የቆሎ የውሃና ቡና እና የውሃ ማጣሪያ ግዥ - የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት (ኢ.ፕ.ድ 007/2019)

Ethiopian Press Agency (የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት)


የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር ኢ.ፕ.ድ 007/2019

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት በ2019 በጀት ዓመት ከዚህ በታች የተገለጹትን እቃዎች በግልጽ ጨረታ የግዥ ዘዴ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

  1. የመኪና መለዋወጫ (በድጋሚ የወጣ)
  2. አድቫንስ ዲስክቶፕ
  3. የቆሎ የውሃና ቡና
  4. የውሃ ማጣሪያ (በድጋሚ የወጣ)

ስለሆነም፡- ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ።

በዘርፉ የዘመኑ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያለው

  • የንግድ ምዝገባ
  • የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ሰርተፍኬት
  • የቫት ሰርተፍኬት
  • በመንግሥት ግዥ በአቅራቢነት የተመዘገበ
ሎት-1የመኪና መለዋወጫ የጨረታ ማስከበሪያ መጠን 254,503.60 ( ሁለት መቶ ሃምሳ አራት ሺህ አምስት መቶ ሶስት ብር ከ60/100 ሳንቲም)
ሎት-2አድቫንስ ዲስክቶፕ የጨረታ ማስከበሪያ መጠን 120,000.00(አንድ መቶ ሃያ ሺህ ብር)
ሎት-3የቆሎ የውሃና ቡና የጨረታ ማስከበሪያ መጠን 50,000.00 ( ሃምሳ ሺህ ብር)
ሎት- 4የውሃ ማጣሪያ የጨረታ ማስከበሪያ መጠን 50,000.00 ( ሃምሳ ሺህ ብር)

በሲ.ፒ.ኦ፣ቢድቦንድ ወይም ለጥቃቅንና አነስተኛ ከአደራጃቸው አካል የሚሰጥ የዋስትና ደብዳቤ በማያያዝ ይህ ጨረታ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ በሚቆጠር 15 ተከታታይ ቀናት አንደኛ ፎቅ በሚገኘው አቅርቦት መምሪያ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ቴክኒካል ዶክመንት ዋና እና ቅጂ እንዲሁም የሚወዳደሩበትን ዋጋ ዋና እና ቅጂ በሚል በጉልህ በሚታይ መልኩ በመጻፍና የሚወዳደሩበትን ሎት በፖስታዎቹ ላይ በመግለጽ በአራት የተለያየ ፖስታ በማሸግ ማስገባት የሚኖርባቸው ሲሆን፤ የጨረታ ማስከበሪያ ቴክኒክ ዋና ሰነድ ፖስታ ውስጥ ተያይዞ መገኘት አለበት።

  • በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት የማይመለስ 100 ብር በመክፈል የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።
  • ስርዝ ድልዝ ያለውና ያልተፈረመ እንዲሁም በጉልህ የማይታይ አጠራጣሪ ሰነድ ተቀባይነት የለውም።
  • ጨረታው በ16ኛው ቀን ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዕለቱ 4፡30 በኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት አቅርቦት መምሪያ 1ኛ ፎቅ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት ሲሆን፤ የተጫራቹ አለመገኘት ጨረታውን ከመክፈት አያስተጓጉለውም። የጨረታ መክፈቻው ቀን እሁድ ወይም የበዓል ቀን ከሆነ በቀጣይ ባለው የሥራ ቀን የሚከፈት ይሆናል።
  • ድርጅታችን አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

አድራሻ፡- አራት ኪሎ ከብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት ፊት ለፊት

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት

✨ messages.ai_summary
Ethiopian Press Agency seeks suppliers for vehicle spare parts, advance desktop computers, corn, water and coffee, and water filters via open tender. Eligible bidders need a valid trade license, business registration, taxpayer ID, VAT certificate, and government supplier registration. Bids must be submitted in four sealed envelopes.
Save Tender