የዳታ/ቴሌ/ፋየር ሲስተም፣ ኤሌክትሮ መካኒካል (AC፣ BUS-WAY፣ Traffic Barriers)፣ ጀነሬተሮች እና ሊፍት /አሳንሰር/ አቅርቦት እና ገጠማ ስራ - ዘመን ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን
ZEMEN CONSTRUCTION CORPORATION (ዘመን ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን)
የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
ጨረታ ቁጥር 07/2019፣08/2019፣09/2019 እና 11/2019
ዘመን ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን እያገነባቸው ላሉት
- ለተለያዩ ፕሮጀክቶች አገልግሎት የሚውሉ የዳታ፣ቴሌ፣ቲቪ፣ኦዲዮ፣ፋየር ሲስተም፣መብረቅ መከላከያ፣ኬብል ትሪ እና ሌሎች አቅርቦት እና ገጠማ ስራ ጨረታ ቁጥር 07/2019
- ለተለያዩ ፕሮጀክቶች አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ ኤሌክትሮ መካኒካል (AC System)፣ የባዝ ወይ (BUS-WAY Systems) እና ትራፊክ ባርየር (Traffic Barriers) አቅርቦት እና ገጠማ ስራ ጨረታ ቁጥር 08/2019
- ለተለያዩ ፕሮጀክቶች አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ ጀነሬተሮች አቅርቦት እና ገጠማ ስራ ጨረታ ቁጥር 09/2019
- ለተለያዩ ፕሮጀክቶች አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ ሊፍት /አሳንሰር/ አቅርቦት እና ገጠማ ስራ ጨረታ ቁጥር 11/2019 ግዥ ለመፈጸም ህጋዊና ብቃት ያላቸው ፋብሪካዎችና አቅራቢዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
ስለዚህ በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች መሳተፍ የሚችሉ መሆኑን እየገለጽን፤
- በዘርፉ ለዘመኑ የታደሰ የንግድ ስራ ፈቃድና፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (TIN) እና የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ የምስክር ወረቀት ያለው/ያላት።
- የጨረታ ማስከበሪያ የጠቅላላ ዋጋውን ቫትን ጨምሮ 2% በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ ይኖርበታል።
- የጨረታ ሰነዱን ባ/ዳር ከተማ ዘመን ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን ቀበሌ 11 እና አ/አበባ ለገሃር አመልድ ህንፃ በሚገኘው ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ቢሮ 7ኛ ፎቅ ለተጠቀሱት ለእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 300.00 /ሶስት መቶ ብር/ በመክፈል ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት መውሰድ ይችላሉ።
- የጨረታ መዝጊያ እና መክፈቻ ቀናት ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ለጨረታ ቁጥር 07/2019 እና 08/2019 ኦርጅናልና ኮፒውን እንዲሁም ለጨረታ ቁጥር 09/2019 እና 11/2019 ቴክኒካል እና ፋይናንሺያል ሰነዶች ኦርጅናልና ኮፒውን በመለየት በተለያዩ ፖስታዎች በጥንቃቄ በማሸግ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለጨረታ ቁጥር 07/2019 እና 08/2019 እስከ 15ኛው ቀን (15 ተከታታይ ቀናትን በመቁጠር) እንዲሁም ለጨረታ ቁጥር 09/2019 እና 11/2019 እስከ 20ኛው ቀን (20 ተከታታይ ቀናትን በመቁጠር) ባህር ዳር ዋናው ቢሮ 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 108 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል። የጨረታ ሳጥኑ ለጨረታ ቁጥር 07/2019 እና 08/2019 በ15ኛው ቀን እና ለጨረታ ቁጥር 09/2019 እና 11/2019 በ20ኛው ቀን ከቀኑ 8:00 ሰዓት ታሽጎ 8:30 ይከፈታል። የተጠቀሱት የመክፈቻ እና የመዝጊያ ቀናቶች የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን እስከ ቀኑ 8:00 ሠዓት ድረስ ማስገባት የሚችሉ ሲሆን በእለቱ ቀን 8:00 ሰዓት ሳጥኑ ታሽጎ 8:30 ይከፈታል።
- የጨረታው ውድድሩ በሎት /በምድብ/ ድምር ዋጋ የሚታይ ሲሆን በአንድ ሎት /ምድብ/ ለተጠየቁ የስራ ዝርዝሮች ሙሉ በሙሉ ዋጋ መሞላት አለበት።
- በጨረታ የተሞላው ዋጋ የጨረታ ሠነዱ ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ለ45 ተከታታይ ቀናት ፀንቶ ይቆያል።
- ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
ለማንኛውም ተጨማሪ ማብራሪያ
ስልክ ቁጥር ባህር ዳር- 058-218-0538 / 09-18-01-06-17 /09-18-71-66-16
አዲስ አበባ - ስልክ ቁጥር 0111265338/09-18-80-03-64/09-11-90-86-29
ዘመን ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን
✨ messages.ai_summary
Supply and installation of data, telecom, TV, audio, fire, lightning protection and cable tray systems; electromechanical works including AC, bus-way and traffic barriers; generators; and lifts/elevators for Zemen Construction Corporation projects. Open to licensed factories and suppliers with valid business license, TIN and VAT registration.
