የጋምቤላ ሕ/ብ/ክ/መንግስት ፋይናንስ ቢሮ ለፋይናንስ ግልጽነትና ተጠያቂነት አገልግሎት የሚውል የተለያዩ የህትመት አይነቶችን የማሳተም አገልግሎት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
የጋምቤላ ሕ/ብ/ክ/መንግስት ፋይናንስ ቢሮ
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 0001/2019
የጋምቤላ ሕ/ብ/ክ/መንግስት ፋይናንስ ቢሮ ለፋይናንስ ግልጽነትና ተጠያቂነት አገልግሎት የሚውል የተለያዩ የህትመት አይነቶችን የማሳተም አገልግሎት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
በዚህም መሰረት ተጫራቾች:-
- ተጫራቾች በመስኩ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች በመ/ቤቱ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) በመክፈል ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 የሥራ ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት ከቢሮ ቁጥር 30 መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ ስለመሆናቸውንና የዘመኑን እንቅስቃሴ የሚያመለከት ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ጨረታው ከመከፈቱ በፊት በቅድሚያ የጨረታ ማስከበሪያ በጥሬ ወይም በባንክ የተመሰከረለት ሲፒኦ (CPO) ለሚጫረቱበት ዋጋ ብር 30000 (ሰላሳ ሺህ ብር) ማስያዝ ይኖርባቸዋል፤
- ተጫራቾች የአቅራቢነት የምዝገባ ሠርተፍኬት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- የዋጋ ማቅረቢያና ሌሎች መረጃዎች የያዘው የጨረታ ሰነድ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ኦርጅናልና ኮፒ ከጨረታው መዝጊያ ቀንና ሰዓት በፊት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይጠበቅባቸዋል፤
- ጨረታው የሚከፈተው የጨረታ ማስታወቂያ በወጣበት ቀን መስከረም 16/1/2019 በ16ኛው ቀን እስከ 3፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት አለባቸው፡፡ ጨረታው በዚሁ ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ታሽጎ በ4፡00 ሰዓት ይከፈታል፡፡ ዕለቱ የሥራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓትና ቦታ ይከፈታል፡፡
- የጨረታ ሠነድ ማስገቢያ ቦታ በክልሉ ፋይናንስ ቢሮ ቢሮ ቁጥር 30 ለዚህ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት አለባቸው፡፡
- ቢሮው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታዉን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 0933800793 ይጠቀሙ፤
የጋምቤላ ሕ/ብ/ክ/መ/ፋይናንስ ቢሮ
✨ messages.ai_summary
The Gambella Regional State Finance Bureau seeks printing services for various print materials supporting financial transparency and accountability. Bidders must hold a valid business license, provide tax payment evidence, be VAT-registered, and submit a supplier registration certificate. The Bureau reserves the right to cancel the tender in part or fully.
