የአማራ ብሔ/ከ/መ/የሰ/ሸዋ/ዞን የመንዝ ጌራ ምድር ወረዳ ገንዘብ ፅ/ቤት ግ/ን/አሰ/ቡድን ለተለያዩ ሴ/መስሪያ ቤቶች የተለያዩ ቋሚ እና አላቂ ማቴሪያሎች ለ2019 ዓ.ም አገልግሎት የሚውሉ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
የመንዝ ጌራ ምድር ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 02/2019
የአማራ ብሔ/ከ/መ/የሰ/ሸዋ/ዞን የመንዝ ጌራ ምድር ወረዳ ገንዘብ ፅ/ቤት ግ/ን/አሰ/ቡድን ለተለያዩ ሴ/መስሪያ ቤቶች የተለያዩ ቋሚ እና አላቂ ማቴሪያሎች ለ2019 ዓ.ም አገልግሎት የሚውሉ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
- የጽህፈት መሣሪያ ሎት 1 የጨረታ ማስከበሪያ 80000
- የጽዳት እቃዎች ሎት2 የጨረታ ማስከበሪያ 15000
- ኮምፒውተርና ተዛማጅ ሎት 3 የጨረታ ማስከበሪያ 80000
- ኤሌክትሮኒክስ ሎት 4 የጨረታ ማስከበሪያ 10000
- የተለያዩ መጋረጃ እና ምንጣፍ ሎት 5 የጨረታ ማስከበሪያ 10000
- የመኪና ጥገና ሎት 6 ለ2ኛ ጊዜ የወጣ የጨረታ ማስከበሪያ 10000
- የመኪና መለዋወጫ ሎት 7 ለ2ኛ ጊዜ የወጣ የጨረታ ማስከበሪያ 20000 ብር
ጨረታው በአየር ላይ የሚቆይበት ከ16/7/2019 ዓ.ም እሰከ 25/1/2019 ዓ.ም ለ10 ተከታታይ ቀናት በአየር ላይ ቆይቶ በ10ኛው ቀን በዚሁ ዕለት ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ ወዲያውኑ 4:30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
- በጨረታ የሚሣተፍ በዘመኑ የታደሰ የንግድ ስራ ፍቃድ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን ነምበር/ የቫት ተመዝጋቢ የተጨማሪ እሴት ታክስ መረጃውን አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፤
- በሚያቀርቡት የጨረታ ዋጋ ላይ የጨረታ መዝጊያ ሰዓት ከተጠናቀቀ በኋላ ማሻሻያ ማድረግና ራሳቸውን ከጨረታው ማግለል አይችሉም።
- ተጫራቾች የሞሉበትን የጨረታ ማስከበሪያ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ ቢድ ቦንድ ወይም የባንክ ዋስትና እንዲሁም ከባንክ የተረጋገጠ CPO ማቅረብ አለባቸው።
- የንግድ ፍቃድና የመሣሠሉት መረጃዎች ከኦርጅናል ዶከመንት ጋር ተያይዘው መቅረብ አለባቸው፡፡
- በፖስታው ላይና እንዲሁም የጨረታ ዋጋ መሙያ የጨረታ ሠነድ ላይ የተጫራቾች ስምና ፊርማና ማህተም ሊኖረው ይገባል።
- በሌላ ተጫራቾች ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም።
- በአንዱ ዋጋ ላይ ሆነ በጠቅላላ ድምር ምንም አይነት ስርዝ ድልዝ መኖር የለበትም ስርዝ ድልዝ ካለው ከጨረታ ውጪ ይሆናል።
- ተጫራቹ ጠቅላላ ድምር አጠቃሎ ያልደመረ ከጨረታ ውጪ ይሆናል።
- ተጫራቹ ጠቅላላ የደመረው እና ትክክለኛ አርቲሜቲክ ቼክ ተሰርቶ ልዩነቱ ከ3% በላይ ወይም በታች ከሆነ ከጨረታ ውድድር ውጪ ይሆናል።
- ተጫራቾች አሸናፊነታቸው በተገለፀላቸው ከ 5 ተከታታይ የስራ ቀናት በኋላ ባሉት ተከታታይ ቀናት ውስጥ በጽ/ቤታችን በመገኘት የውል ማስከበሪያ 10% በማስያዝ ውል መፈፀም አለባቸው በተሰጠው የጊዜ ገደብ ውስጥ ቀርበው ውል ካልፈፀሙ በግዥ መመሪያው መሠረት የጨረታ ማስከበሪያውን ውርስ በማድረግ ለመንግስት ገቢ ይደረጋል፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ አፈፃፀም ሂደት ላይ ቅሬታ ካላቸው በግዥ አዋጅ መሠረት አሸናፊነቱ በተገለፀ በተከታታይ በ5 የስራ ቀን ውስጥ ቅሬታውን ማቅረብ ይችላሉ፤
- ለአሸናፊ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙትን ብር ከአሸናፊ ተጫራች ጋር ውል እንደተፈፀመ ተመላሽ ይደረጋል።
- በጨረታ ሰነዱ ላይ የተዘረዘሩትን ሁሉንም ተጫራቹ መሙላት አለበት ሁሉንም ካልሞሉ ከውድድር ውጪ ይደረጋል።
- ጨረታው በሚከፈትበት ወቅት የሀዝብ በዓላት፣ ቅዳሜና እሁድ ከዋለ በቀጣዩ የስራ ቀናት በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
- የጨረታ ሰነዱን በመንዝ ጌራ ምድር ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ድረስ በመምጣት ብር 200 /ሁለት መቶ ብር በማይመለስ መግዛት የሚቻል ሲሆን ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ መግዛትና መውሰድ ይችላሉ።
- ሂሳብ የሚከፈለው አሸናፊው ተጫራች በውሉ መሰረት እቃዎቹን ሲያጠናቅቅ ከፍያን ይወስዳል።
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- አሸናፊ የሚለየው በጥቅል ወይም በተናጠል መብቱ የሚያዋጣ ነው፡፡
- የተለያዩ ሌሎች ሳምፕል ለሚያስፈልጋቸው ሳምፕሉን በማየት ዋጋ በመሙላት ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ከ500 ሺህ ብር በላይ የሚቀርብ የጨረታ ሰነድ የቫት ተመዝጋቢ ሰርተፍኬት ማቅረብ አለበት፡፡
- ተጫራቾች ተጨማሪ ማብራሪያ ሲፈልጉ በስልክ ቁጥር 011 6851461/0106 በመደወል መጠየቅ ይችላሉ።
- ለጥቃቅን ኢንተርፕራይዝ ለተደራጁ ተጫራቾች በመመሪያ ቁጥር 144/2018 ልዩ አስተያየት ይደረግላቸዋል።
የመንዝ ጌራ ምድር ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
✨ messages.ai_summary
The finance office seeks suppliers for office supplies, cleaning materials, computers and accessories, electronics, curtains and carpets, vehicle maintenance, and vehicle spare parts. Bidders need a renewed business license, TIN, and VAT registration; those bidding over 500,000 birr must provide a VAT certificate.
Not stated in the notice: bid security. Check the original document or ask the issuer.
