Tender Detail

Tender Details

  • Company ወልቂጤ ማረሚያ ተቋም
  • Address ወልቂጤ ከተማ ፡ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል : ኢትዮጵያ, Phone: 011-3-30-01-54
  • Website
  • Deadline05 Oct 2026, 11:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid Securityከጠቅላላ አቅርቦት ዋጋ 2% የብር 50,000 /ሃምሳ ሺህ ብር ብቻ/ CPO
  • opening date11ኛው ቀን ከረፋዱ 5፡30 ሰዓት
  • Categories Agriculture And Farming , Food Items And Drinks , Agricultural Products

የወልቂጤ ማሪሚያ ተቋም ለህግ ታራሚዎች ለቀለብ አገልግሎት የሚውል ከዚህ በታች በሠንጠረዡ ውስጥ የተመለከቱትን አቅርቦቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለ3 ወራት በሚቆይ የአቅርቦት ጊዜ ሆኖ በአቅራቢና ተቀባይ መካከል በሚደረገው የውል ስምምነት መሠረት ሶስት ወራት ለሚደርስ የግዥ ዘዴ በየወሩ ለሚያቀርቡ አቅራቢዎችን በጨረታ አወዳድሮ ለመስጠት ይፈልጋል፡፡

ወልቂጤ ማረሚያ ተቋም


ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር ወማተ/አ2/470/2019

የወልቂጤ ማሪሚያ ተቋም ለህግ ታራሚዎች ለቀለብ አገልግሎት የሚውል ከዚህ በታች በሠንጠረዡ ውስጥ የተመለከቱትን አቅርቦቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለ3 ወራት በሚቆይ የአቅርቦት ጊዜ ሆኖ በአቅራቢና ተቀባይ መካከል በሚደረገው የውል ስምምነት መሠረት ሶስት ወራት ለሚደርስ የግዥ ዘዴ በየወሩ ለሚያቀርቡ አቅራቢዎችን በጨረታ አወዳድሮ ለመስጠት ይፈልጋል፡፡

ተ.ቁ የአቅርቦቱ አይነት መለኪያ የአቅርቦት መጠን የማቅረቢያ ጊዜ ርከከቡ የሚፈፀምበት ቦታ በቅድሚያ ለ033 ወራት ቆይታ ጊዜ ከ-እስከ
01 ነጭ ሠርገኛ ጤፍ በኩ/ል ከ150-200 ኩንታል ወር በገባ ከ25-30ድረስ ተቋሙ ቅጥር ግቢ ከ1/02/2019-30/04/2019
02 ነጭ በቆሎ በኩ/ል ከ450-650 ኩንታል ወር በገባ ከ25-30ድረስ ተቋሙ ቅጥር ግቢ ከ1/02/2019-30/04/2019
03 ባቄላ በኩ/ል ከ60-80 ኩንታል ወር በገባ ከ25-30ድረስ ተቋሙ ቅጥር ግቢ ከ1/02/2019-30/04/2019
04 የሀገር ውስጥ ስንዴ በኩ/ል ከ40-45 ኩንታል ወር በገባ ከ25-30ድረስ ተቋሙ ቅጥር ግቢ ከ1/02/2019-30/04/2019
05 የሽሮ ጓያ በኩ/ል ከ40-50 ኩንታል ወር በገባ ከ25-30ድረስ ተቋሙ ቅጥር ግቢ ከ1/02/2019-30/04/2019
06 ጎመን ዘር በኪ.ግ ከ20-50 ኪ.ግራም ወር በገባ ከ25-30 ተቋሙ ቅጥር ግቢ ከ1/02/2019-30/04/2019
07 ቀይ ሽንኩርት ቀላፎ በኪ.ግ ከ500-600 ኪ.ግራም ወር በገባ ከ25-30ድረስ ተቋሙ ቅጥር ግቢ ከ1/02/2019-30/04/2019
08 የዳቦ እርሾ በፓኬት ከ30-40 ፓኬት ወር በገባ ከ25-30ድረስ ተቋሙ ቅጥር ግቢ ከ1/02/2019-30/04/2019
09 ሻይ ቅጠል በፓኬት ከ100-180 ፓኬት ወር በገባ ከ25-30ድረስ ተቋሙ ቅጥር ግቢ ከ1/02/2019-30/04/2019
10 ጨዉ በኮ/ል ከ5-6ኩንታል ወር በገባ ከ25-30ድረስ ተቋሙ ቅጥር ግቢ ከ1/02/2019-30/04/2019
11 የተጨ በርበሬ 1ኛዉ በኪ/ግ ከ150-280ኪ.ግራሚ ወር በገባ ከ25-30ድረስ ተቋሙ ቅጥር ግቢ ከ1/02/2019-30/04/2019
12 ግንዲላ የማገዶ እንጨት በሜ.ኩ ከ50-80ሜትር ኩብ ወር በገባ ከ25-30ድረስ ተቋሙ ቅጥር ግቢ ከ1/02/2019-30/04/2019
  1. በየመስኩ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያለውላት የዘመኑን ግብር የከፈለ/ች/ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥርያለው/ላት፤ ከማንኛውም ግብርና ታክስ ከፋይነት ነፃ እንዲሆኑ ከተፈቀደላቸው ድርጅቶችና ዩኒየኖችና ተመሳሳይ የንግድ ድርጅቶች በስተቀር የVATI5% ተመዝጋቢ የሆኑና የምዝገባ የምስከር ወረቀት ማስረጃ ሊያቀርቡ የሚችሉ፣ መሆን አለባቸው፤
  2. ተጫራቾች ለሚጫረቱበት አቅርቦት በቀደምት የሥራ ዘመን ተጫርተው በማሸነፍ ለማረሚያ ተቋማት ወይንም ለሌሎች መንግስታዊና ሕዝባዊ ድርጅቶች ለዐ1 (አንድ) አመት እና ከዚያም በላይ ለሆነ ጊዜያት ያለ እንከን ስለማቅረባቸው የመልካም ሥራ አፈፃፀም ደብዳቤ /ምስክር ወረቀት/ ማስረጃ ከሌሎች መጫረቻ ሰነዶች ጋር አያይዘው ማቅረብ የሚችሉ ፤
  3. አሸናፊው ተጫራች ለአቅርቦቱ ከላይ በተዘረዘሩት መስፈርቶች መሠረት ከጥቅምት 1/2019 ዓ/ም ጀምሮ ለ3 ወራቶች በየወሩ ለማቅረብ ህጋዊ የውል ሰነድ የሚፈርምና ያሸነፈው ነጠላ ዋጋ እንደተጠበቀ ሆኖ ለማቅረብ ፈቃደኛ የሚሆን ፣
  4. ተጫራቾች ይህ ጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመንጋዜጣ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ወልቂጤ ማረሚያ ተቋም ግዥና ፋይናንስ ንብ/አስ/ደ/ሥራ ሂደት ቢሮ በመቅረብ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ በነፃ መውሰድ የሚችሉ ሲሆን፤የጨረታ ማስከበሪያን በሚመለከት ከጠቅላላ አቅርቦት ዋጋ 2% የብር 50,000 /ሃምሳ ሺህ ብር ብቻ/ CPO/ተመሳሳይ ሰነድ በማሰራት ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዞ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  5. ተጫራቾች:- ይህ ጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10/አስር/ተከታታይ ቀናት የእያንዳንዱን እህል ማጣፈጫ የአንዱን ኩንታል/ኪ/ግራም) ነጠላ ዋጋ ከነማስረጃው ኮፒዎች ጋር በማድረግ በሰም በታሸገ ኤንቬሎፕ አዘጋጅተው ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  6. ተጫራቶች የእህል ዓይነቶችን እና የበርበሬ ናሙና የማቅረብ ግዴታ እንዳለባቸው መዘንጋት የለባቸውም
  7. ጨረታው በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 5፡00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ ተጫራቾች ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት 11ኛው ቀን ከረፋዱ 5፡30 ሰዓት በማረሚያ ተቋሙ ቅጥር ግቢ አዳራሽ /ቢሮ/ የሚከፈት መሆኑን ስንገልጽ ዕለቱ የበዓላት /የዕረፍት ቀን ከሆነ በማግስቱ በተመሳሳይ ሰዓት የሚከፈት መሆኑን እያሳሰብን መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር:- 011-330-0154 011-330 1139፥011-330-158

ወልቂጤ ማ/ተቋም

✨ messages.ai_summary
Welqite Correctional Facility seeks suppliers for food and agricultural items for inmate meals, including teff, maize, beans, wheat, shiro, cabbage seed, onions, yeast, tea, salt, pepper, and firewood, delivered monthly to the facility. Bidders need a valid trade license, tax registration, VAT registration, and prior supply experience.
Not stated in the notice: bid document price. Check the original document or ask the issuer.
Save Tender