Tender Detail

Tender Details


የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ለጃንሜዳ G+10 ለፌዴራል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን እና ለፌዴራል ዋና ኦዲተር መ/ቤት ግንባታ ፕሮጀክቶች አገልግሎት የሚውሉ Supply and fix Cable Ladder, Fire Fighting Pumps & Reserver Osmosis water treatment ግዥ ለመፈፀም ተጫራቾችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ


የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር DCE/SF/128/2026 DCE/SF/129/2026፣ DCE/SF/130/2026

የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ለጃንሜዳ G+10 ለፌዴራል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን እና ለፌዴራል ዋና ኦዲተር መ/ቤት ግንባታ ፕሮጀክቶች አገልግሎት የሚውሉ Supply and fix Cable Ladder, Fire Fighting Pumps & Reserver Osmosis water treatment ግዥ ለመፈፀም ተጫራቾችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

ተ.ቁ የዕቃውን ዓይነት የፕሮጀክት ስም የጨረታ ቁጥር የጨረታ መዝጊያ ቀን እና ሰዓት የጨረታ መከፈቻ ቀን እና ሰዓት የጨረታ ማስከበሪያ
1 Supply and fix Cable Ladder ጃንሜዳ G+10 ግንባታ ፕሮጀክት DCE/SF/128/2026 መስከረም 29/2019 ዓ.ም 4:00 ሰዓት መስከረም 29/2019 ዓ.ም 4፡15 ሰዓት 50,000.00
2 Supply & Fix, Test and Fire Fighting Pumps በፌዴራል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን ግንባታ ፕሮጀክት DCE/SF/129/2026 መስከረም 29/2019 ዓ.ም 4፡15 ሰዓት መስከረም 29/2019 ዓ.ም 4፡30 ሰዓት 100,000.00
3 Supply, Install, Test and Commission Re-servier Osmosis water treatment ፌዴራል ዋና ኦዲተር መ/ቤት ግንባታ ፕሮጀክት SF/130/2026 መስከረም 29/2019 ዓ.ም 4፡30 ሰዓት መስከረም 29/2019 ዓ.ም 4፡45 ሰዓት 100,000.00

ስለሆነም፡-

  1. ተጫራቾች በዘርፉ የተሰማሩ መሆኑን የሚገልፅ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉበት ማስረጃ፣ ለተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡበትን ግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፣ በጨረታ ለመሳተፍ የሚሰጥ የታደሰ የምስክር ወረቀት (ታክስ ክሊራንስ) እና የሀገር ውስጥ ተጫራቾች በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ መሆኑን የሚያረጋግጥ ኮፒ ወዘተ... ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡
  2. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ከላይ በሠንጠረዥ በተገለፀው መሠረት በባንክ የተረጋገጠ (CPO) ወይም ከታወቀ ባንክ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና (Unconditional Bank Guarantee) 120 (አንድ መቶ ሃያ) Calendar days የሚቆይ ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  3. ተጫራቾች ለእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ዘወትር በሥራ ሰዓት ቃሊቲ ቶታል ማደያ ዝቅ ብሎ የቀድሞ መ.ኮ.ድ ግቢ በሚገኘው የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ዋና መ/ቤት የግዥና አቅርቦት አስተዳደር መምሪያ ቢሮ መግዛት ይችላሉ፡፡
  4. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ በጨረታ ሰነድ በተያያዘው ዝርዝር እና ብዛት መሠረት መሆን ይኖርበታል፡፡
  5. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን የጨረታ ቴክኒካል ሰነድ እና ዋጋ በታሸገ ኤንቨሎፕ ከላይ በሰንጠረዡ በተገለፀው ቀንና ሰዓት በኢንተርፕራይዙ የግዥና አቅርቦት አስተዳደር መምሪያ ቢሮ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  6. ጨረታው ከላይ በሰንጠረዡ በተገለፀው መሠረት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድርጅቱ መሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል፡፡
  7. ኢንተርፕራይዙ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

አድራሻ፡- የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ቃሊቲ ቶታል ማደያ ዝቅ ብሎ የቀድሞ መ.ኮ.ድ ግቢ

የቀጥታ ስልክ ቁጥር 0114-40-34-34

ማዞሪያ 0114-42-22-70/71/72 E-mail info@dce-et.com

የድህረ ገፅ አድራሻ www.dce-et.com

የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ

✨ messages.ai_summary
Supply and fix cable ladders, fire fighting pumps, and reverse osmosis water treatment for Janmeda G+10, Federal Prison Commission, and Federal Auditor General building projects. Bidders must be licensed in the sector, VAT-registered, tax-compliant, and registered on the domestic suppliers list.
Save Tender

Supply & Fix Alarm System and Supply of Light Fitting and Distribution Board - Federal Auditor Gener...

READ MORE
Procurement of Office Equipment

READ MORE