Tender Detail

Tender Details

  • Company Tsedey Bank S.C. (ፀደይ ባንክ አ.ማ)
  • Address ሰንጋተራ አካባቢ በሚገኘው የባንኩ ዋና መ/ቤት ህንጻ 16ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 09 ፡ አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0115584896
  • Websitehttps://tsedeybank-sc.com/
  • Deadline08 Oct 2026, 10:00 AM
  • magazineReporter
  • Bid Document Priceየማይመለስ አምስት መቶ ብር /500.00/
  • Bid Securityየአጠቃላይ ዋጋውን 2% ወይም የአጠቃላይ ዋጋው 2% ከብር 500,000.00 በሲፒኦ /CPO/ ወይም በሁኔታዎች ላይ ያልተመሠረተ የባንክ ጋራንቲ የ90 ቀን
  • opening dateOct 08, 2026, 10:30 AM
  • Categories Electrical And Electromechanical , Installation, Maintenance And Other Engineering Services

ፀደይ ባንክ አ.ማ. አዲስ ላስገነባው የዋና መ/ቤት ህንፃ ከ17-29ኛ ወለል የተጓደሉ የመብራት መስመሮችን ለማሟላት ግዥ ለመፈፀም Grade 1 Electrical or Electromechanical Contractor ፈቃድ ያላቸውን ተጫራቾች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል።

Tsedey Bank S.C. (ፀደይ ባንክ አ.ማ)


የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር ብ/ግ/ጨ/002/2019

ፀደይ ባንክ አ.ማ. አዲስ ላስገነባው የዋና መ/ቤት ህንፃ ከ17-29ኛ ወለል የተጓደሉ የመብራት መስመሮችን ለማሟላት ግዥ ለመፈፀም Grade 1 Electrical or Electromechanical Contractor ፈቃድ ያላቸውን ተጫራቾች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል።

ስለሆነም ከዚህ በታች የቀረበውን መስፈርት የሚያሟላ ማንኛውም በዘርፉ የተሰማራ ድርጅት/ነጋዴ/መወዳደር የሚችል መሆኑን እንገልጻለን።

1.     የ2018 ዓ.ም የታደሰ ንግድ ፈቃድ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ የምስክር ወረቀት፣ የግብር መክፈያ ሰርተፊኬት፣ የታክስ ክሊራንስና የብቃት ማረጋገጫ ሊኖራቸው ይገባል። ቴክኒካል ዶክሜንትና የሚያቀርቡበትን ዋጋ በጨረታ ዶክሜንቱ መሠረት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

2.     ለጨረታ ማስከበሪያ የአጠቃላይ ዋጋውን 2% ወይም የአጠቃላይ ዋጋው 2% ከብር 500,000.00 በሲፒኦ /CPO/ ወይም በሁኔታዎች ላይ ያልተመሠረተ የባንክ ጋራንቲ የ90 ቀን በፀደይ ባንክ አማ ስም ማሠራት ይኖርባቸዋል። ከየትኛውም የፀደይ ባንክ አማ ቅርንጫፍ የተሰጠ ሲፒኦምሆነ ባንክ ጋራንቲ ተቀባይነት የለውም።

3.     በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ከመስከረም 14 ቀን 2019 ዓ.ም ጀምሮ ባሉት የስራ ቀኖች ማለትም ከሰኞ እስከ አርብ ከጠዋቱ 2:00 ሰዓት እስከ 6:00 ሰዓት እና ከሰዓት በኋላ ከ7:00 ሰዓት እስከ ምሽቱ 11:00 ሰዓት እንዲሁም ቅዳሜ ከጠዋቱ 2:00 ሰዓት እስከ 6:00 ሰዓት የማይመለስ አምስት መቶ ብር /500.00/ ፀደይ ባንክ ለገሃር ቅርንጫፍ ወይም በማንኛውም የፀደይ ባንክ ቅርንጫፍ በመክፈል ሰንጋተራ አካባቢ በሚገኘው የባንኩ ዋና መ/ቤት 16ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 09 ከግዥ ክፍል ሰነዱን መዉሰድ ይችላሉ።

4.     ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን የጨረታ ሰነድ በሰም በታሸገ ፖስታ እስከ መስከረም 28 ቀን 2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ አዲስ አበባ ሰንጋተራ አካባቢ በሚገኘው ፀደይ ባንክ ዋና መ/ቤት 16ተኛ ፎቅ ግዥና ዉል አስተዳደር ቢሮ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል:: ጨረታው በዚሁ ዕለት በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር ከጠዋቱ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በመስሪያ ቤቱ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል።

5.     የጨረታዉ መዝጊያ ሰዓት ካለፈ በኋላ የሚመጣ ማንኛዉም የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት አይኖረዉም።

6.     ባንኩ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

አድራሻ፡- አዲስ አበባ ሰንጋተራ አካባቢ ጤና ሚኒስቴር ዝቅ ብሎ በሚገኘው የፀደይ ባንክ ዋና መ/ቤት ስልክ ቁጥር 0115581658

ፀደይ ባንክ አ.ማ.

✨ messages.ai_summary
Tsedey Bank seeks eligible bidders to complete missing lighting lines on floors 17–29 of its new headquarters building. Open to Grade 1 Electrical or Electromechanical Contractors. Bidders must submit technical documents and pricing per the tender document.
Save Tender