አልሺማ የምግብ አምራች ኃ/የተ/የግ/ማህበር የ2020 ሞዴል ያገለገለ ሁለት የጣልያን አይቪኮ (Model 50C15/E3 Year 2020: ተሽከርካሪን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡
አልሺማ የምግብ አምራች ኃ/የተ/የግ/ማህበር
ለሁለተኛ ጊዜ የወጣ የተሽከርካሪ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር አ/ የም/ስም/ኃ/የተ/የግ/ማህበር ሽያጭ/0006/2026
አልሺማ የምግብ አምራች ኃ/የተ/የግ/ማህበር የ2020 ሞዴል ያገለገለ ሁለት የጣልያን አይቪኮ (Model 50C15/E3 Year 2020: Chassis no EBPBCAHAALD000015 EBPBCAHAAD000016 Motor no: FICE3481)3827324 AS FICE3481) 38273261 Clour: White Vehicle type: Bus: CC: 2998 እንዲሁም በጥሩይዞታ ላይ የሚገኝ የ2017 ሞዴል ሊፋን X60 ቻንሲ ቁጥር LCN64ED50M0097133 የሞተር ቁጥር LFB479Q-170300359* ተሽከርካሪን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡
በዚህም መሠረት በጨረታው ላይ ለመሳተፍ የሚፈልጉና ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ማንኛውም ተጫራቾች ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 (አስራ አምስት) ተከታታይ ቀናት መጫረት ይችላሉ።
- ማንኛውም የመጫረት ፍላጎት ያለው በጨረታው ላይ መሳተፍ ይችላል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸውን ሲያቀርቡ ለተጫረቱበት ተሸከርካሪ የጨረታ ማስከበሪያ የጠቅላላ ዋጋውን 10 % (አስር በመቶ) በባንክ በተመሰከረለት ሲፒኦ ማስያዝ ይኖርባቸዋል። ከሲፒኦ ውጪ የሚያቀርቡ የጨረታ ማስከበሪያ ተቀባይነት የለውም።
- የጨረታ ሰነዱን የገዙ ተጫራቾች ተሽከርካሪው አዳማ በሚገኘው የድርጅቱ ፋብሪካ ቅጥር ግቢ በአካል በመቅረብ ማየት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት ሲፒኦ አሸናፊው ተለይቶ ከታወቀ በኋላ የሚመለስ ይሆናል፡፡
- ጨረታው አሸናፊ ለተሽከርካሪው የሚከፈሉ ማንኛውንም የመንግስት ከፍያዎችን ሁሉ ይሸፍናል፡፡
- ማንኛውም ተጫራቾች ሌሎች በሰጡት ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይችልም።
- የጨረታው አሸናፊ መሆኑ የተገለፀለት ተጫራች ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘው 10% (አስር በመቶ) እንደውል ማስከበሪያ ይቆጠራል፡፡ የጨረታው አሸናፊ የገባውን ውል ካልፈፀመ ለጨረታ ማስከበሪያ የተያዘው ዋስትና እንደ ውል ማስከበሪያ ተቆጥሮ የተያዘውን ገንዘብ አልሺማ የምግብ አምራች ኃ/የተ/የግ/ማህበር ወደ ራሱ ካዝና ገቢ ያደርጋል፣
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ከድርጅቱ ፋይናንስ መምርያ አዳማ ወይንም አዲስ አበባ ከሚገኘው ቢሮ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) በመከፈል መግዛት ይችላሉ።
- ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ዕለት አንስቶ ለ 15 (አስራ አምስት) ተከታታይ ቀናት አየር ላይ ቆይቶ በ16ኛው የስራ ቀን ከቀኑ በ 8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በተመሳሳይ ቀን አዳማ ከተማ በሚገኘው የድርጅቱ /ፋብሪካ ቅጥር ግቢ ከቀኑ በ 8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይንም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ከላይ በተጠቀሰው ቀን እና ሰዓት ለጨረታ ሰነድ ማስገቢያ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው:: በጨረታ ሰነዱ ላይ ያልተሞላ ወይንም በሌላ ወረቀት ላይ የተሞላ ዋጋ ተቀባይነት የለውም።
- የጨረታው አሸናፊ የሚለየው ባቀረበው የመግዣ ዋጋ መሠረት ብቻ ነው::
- የጨረታ አሸናፊ ጨረታውን ማሸነፉ በተገለጸ በ7 ቀናት ውስጥ በአካል ቀርቦ ውል መፈፀም አለበት፡፡
- የጨረታው አሸናፊ ውል እንዲፈፅም በተገለፀለት በ 7 ቀናት ውስጥ ቀርቦ ውል ባይፈፅም ድርጅቱ ለጨረታ ማስከበሪያ የተያዘውን ዋስትና ወደ ራሱ ካዝና ገቢ ያደርጋል፡፡
- ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታን ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር፡- 0984551186/0973300059
አልሺማ የምግብ አምራች ኃ/የተ/የግ/ማህበር
✨ messages.ai_summary
Alshima Food Producers Union is selling by open bid two used 2020 Italian Iveco vehicles (Model 50C15/E3, white, bus type, 2998cc) and one used 2017 Lifan X60. Bidders must submit a bank-certified CPO for 10% of the total price; other guarantees are rejected.
