የአዲስ አበባ ከተማ አስተደደር የአዲስ መሶብ የአንድ ማዕከል ዲጅታል የመንግስት አገልግሎት በ2019 በጀት ዓመት የሚያስፈልጉ የተለያዩ እቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
አዲስ መሶብ አንድ ማዕከል ዲጅታል የመንግስት አገልግሎት
የጨረታ ማስታወቂያ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተደደር የአዲስ መሶብ የአንድ ማዕከል ዲጅታል የመንግስት አገልግሎት በ2019 በጀት ዓመት የሚያስፈልጉ የተለያዩ እቃዎችሎት1፡ አላቂ ዕቃዎች፣ሎት 2፡-ደንብ ልብስሎት 3፡ ቋሚ ዕቃዎች (ኤሌክትሮኒክስ እና ሌሎች) ሎት 4፡- የህትመት ስራዎች፣ሎት 5፡ የተሽከርካሪ መለዋወጫ ዕቃዎች፣ሎት 6፡- የኢቨንት ስራዎችሎት 7፡-የፅዳት ዕቃዎች እና ሎት 8 ፡ የተለያዩ ለጥገና የሚሆኑ የመለዋወጫ ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
ስለሆነም ተጫራቾች፡-
1. የዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው እና የዘመኑ ግብር የከፈሉ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ መሆን አለባቸው።
2. በኢፌዴሪ የመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ በአቅራቢነት ዝርዝር የተመዘገቡበት ማስረጃ ማያያዝ አለባቸው።
3. የጨረታ ሰነዱ የማይመለስ ብር 1000 (አንድ ሺ ብር) በመክፈል ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት አራት ኪሎ በሚገኘው አራዳ ክ/ከተማ ህንጻ ጎን 6ኛ ፎቅ ፋይናንስ ዳይሬክቶሬት መግዛት ይችላሉ።
4. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ ህጋዊ ሥልጣን ያለውን አካል ፊርማ በማኖር በሰም በታሸገ ማህተም ያረፈበት ኤንቨሎፕ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
5. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ክፍት ሆኖ የሚቆይ ሲሆን በ10ኛው የሥራ ቀን 11፡30 ሰዓት ተዘግቶ በ11ኛው ቀን 4፡00 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት 5ኛ ፎቅ የግዥ፣ንብረት አስተዳደርና ጠቅላላ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ቢሮ ይከፈታል። ነገር ግን በ 11ኛው ቀን በዓል ወይም እሁድ ላይ ከዋለ በሚቀጥለው የሥራ ቀን 4፡00 ሰዓት ላይ የሚከፈት ይሆናል።
6. ተጫራቾች ለሚያቀርቡት አጠቃላይ ዋጋ 2% Unconditional Bank Guaranty ወይም CPO ማስያዝ አለባቸው። እያንዳንዱ ተወዳዳሪ የቴክኒክና የፋይናንስ ሰነድ አንድ ኦርጂናል እና አንድ ኮፒ ማቅረብ አለባቸው::
7. መስሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉየመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ መረጃ ስልክ ቁጥር፡- +251116198683
አዲስ መሶብ አንድ ማዕከል
ዲጅታል የመንግስት አገልግሎት
