በአዲስ አበባ ከተማ እና በዙሪያዋ ለሚገኙ ነዋሪዎች ለሁሉም ከ/ከተሞች ጤና መድህን ተጠቃሚዎች ለፈዴራል ጤና መድህን ተጠቃሚዎች መንግሥታዊ እና መንግሥታዊ ላልሆኑ ድርጅቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳዳር የመንግስት ልማት ድርጅቶች አስተዳደር ባለስልጣን ከነማ ፋርማሲዎች ድርጅት
የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 003/2019
በአዲስ አበባ ከተማ የመንግሥት ልማት ድርጅቶች አስተዳደር ባለሥልጣን ከነማ ፋርማሲዎች ድርጅት
በአዲስ አበባ ከተማ እና በዙሪያዋ ለሚገኙ ነዋሪዎች ለሁሉም ከ/ከተሞች ጤና መድህን ተጠቃሚዎች ለፈዴራል ጤና መድህን ተጠቃሚዎች መንግሥታዊ እና መንግሥታዊ ላልሆኑ ድርጅቶች ጥራታቸውና ፈዋሽነታቸው የተረጋገጡ መድኃኒቶች እና የህከምና መገልገያዎችን በተመጣጣኝ ዋጋ በማቅረብ በ53 መድኃኒት ቤቶች እና የጅምላ ንግድ አከፋፋይ ድርጅቶች የዱቤ /credit እና የጥሬ ገንዘብ / cash ሽያጭ አገልግሎት እየሰጠ ያለ የመንግስት የልማት ድርጅት ነው:: ስለሆነም ድርጅቱ ከነማ ፋርማሲ የኮስሞቲክስ እና ወተት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል መስፈርቱን የምታሟሉና ብቁ የሆናችሁ ተወዳዳሪዎች በጨረታው መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
- በንግድ ዘርፍ ወይም በመስኩ የታደሰ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያለው እና የቲን ማስረጃዎች፡፡
- ተጫራቾች የማይመለስ ብር 500 (አምስት መቶ ብር) በመከፈል ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት የመጀመሪያ ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት (ቅዳሜን ግማሽ ቀን ጨምሮ ) ጉለሌ ክ/ከተማ ሰሜን ማዘጋጃ አካባቢ SMSS / ኤስ ኤም ኤስ ኤስ / ህንጻ 3ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 306 በመቅረብ የጨረታ ሰነድ መግዛት ይችላሉ፡፡
- ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ማስታወቂያው አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ እስከ 11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት የሚቻል ሲሆን 4፡30 ሰዓት የጨረታው ሳጥን የሚታሸግ ስለሆነ አርፍዶ የሚመጣ ተቀባይነት የለውም፡፡ በዚሁ ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የጨረታው ሳጥን በድርጅቱ ግዥ ዳይሬክቶሬት ከፍል 4ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 403 የሚከፈት ይሆናል፡፡
ማሳሰቢያ:- ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
አድራሻ፡- ከፒያሳ ወደ አዲሱ ገበያ በሚወስደው መንገድ ሰሜን ማዘጋጃ አካባቢ SMSS / ኤስ ኤም ኤስ ኤስ / ህንጻ 4ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 403፤
የሥራ ሰዓት፡- ከሰኞ እስከ አርብ ከጠዋቱ 2፡00 ሰዓት እስከ 6፡00 ሰዓት ከሰዓት ከ7፡00 ሰዓት እስከ 11፡00 ሰዓት ፤ ቅዳሜ ከጠዋቱ 2፡00 ሰዓት እስከ 6፡00 ሰዓት
ለተጨማሪ መረጃ ስልክ ቁጥር፡- 0118-27-91-23
በአዲስ አበባ ከተማ የመንግሥት ልማት ድርጅቶች አስተዳደር ባለሥልጣን ከነማ ፋርማሲዎች ድርጅት
