Tender Detail

Tender Details

  • Company Alsam Group (አልሳም ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር)
  • Address አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: Office Contact Numbe
  • Websitehttps://www.alsamgroup.com/
  • Deadline30 Sep 2026, 10:00 PM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price1000.00
  • Bid Security10%
  • opening dateጨረታው አየር ላይ ለተከታታይ 11 ቀን ቆይቶ በ 11 ኛው ቀን 4፡30 ሰዓት የሚከፈት ይሆናል፡፡
  • Categories Academic

አልሳም ዲማ ኢንዱስትሪ ማዕከል ያገለገሉ የፈትል ከፍል ማሽኖችን፣ የሽመና ክፍል ማሽኖችና የጨርቅ ማቅለሚያ ማሽኖች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።

Alsam Group (አልሳም ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር)


የጨረታ ማስታወቂያ

አልሳም ዲማ ኢንዱስትሪ ማዕከል ያገለገሉ የፈትል ከፍል ማሽኖችን፣ የሽመና ክፍል ማሽኖችና የጨርቅ ማቅለሚያ ማሽኖች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል። በዚህም መሰረት ህጋዊ ተጫራቾች የሚከተትን የጨረታ መስፈርቶች በማሟላት እንድትወዳደሩ እየጠየቅን ለበለጠ ማብራሪያ ከታች በሚገኘው የስልክ አድራሻ በመጠየቅ መረዳት ይችላሉ፡፡

የስራው አይነት የጨረታው ሰነድ ግዥና መመዝገቢያ ቀን የጨረታው መክፈቻ ቀንና ሰዓት
ያገለገሉ ማሽኖች  መሸጥ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይየስራ ቀናት

በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግልጽ በፋብሪካው ቅጥር ግቢ ተዘግቶ 4፡30 ይከፈታል፡፡ 

 ከ11ኛው ቀን እሁድ ወይም ሌላ በዓል ከሆነ በተመሳሳይ ሰዓት በሚቀጥለው የስራ ቀን ይሆናል፡፡

ስለሆነም-

1. የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው እና ኮፒውን ማቅረብ የሚችሉ፤

2. የንግድ ምዝገባ ምስከር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፤

3. የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር /TIN Number/ ቁጥር ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ፣

4. የተጨማሪ እሴት ታክስ /NAT/ ከፋይነት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፣

5. ተጫራቾች ያስገቡትን ዋጋ 10 ከመቶ የጨረታ ማስከበሪያ በአልሳም ዲማ ኢንዱስትሪ ማዕከል (ADIC) ስም የተዘጋጀ በንግድ ባንክ በተመሰከረለት የባንከ ቼh (CPO) ማቅረብ የሚችሉ፣

6. ተጫራቾች በሌላ ተጫራች ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም፡፡

7. ተጫራቾች የጨረታውን ሙሉ ዝርዝር የያዘ ሰነድ የማይመለስ ብር 1000 (አንድ ሺህ ብር) በመክፈል ይህ ጨረታ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት አስር ተከታታይየስራ ቀናት ሰበታ ዲማ ከሚገኘው ድርጅታችን የፋይናንስ መምሪያ ቢሮ ቀርበው መግዛት ይችላሉ፤

8. ተጫራቾች በጨረታው መከፈቻ ሥነ-ስርዓት ባይገኙ የጨረታውን መክፈት ሂደት አያስተጓጉልም፡፡

9. ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለበለጠ መረጃ፡- ስ.ቁ፡- 0993-901016፣ 0912-617391

አልሳም ኃሳ/የተ/የግል ማህበር

✨ messages.ai_summary
Alsam Dima Industry Center invites legal bidders to buy used spinning, weaving, and textile dyeing machines via open bid. Bidders must submit a renewed business license, commercial registration, TIN, VAT certificate, and a 10% CPO bid security. Full bid documents cost 1000 birr.
Save Tender