Tender Detail

Tender Details

  • Company በጉምሩክ ኮሚሽን የጋላፊ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት
  • Address , Phone: 0335590114
  • Website
  • Deadline23 Sep 2026, 9:30 AM
  • magazineAddis Zemen
  • Bid Document Priceብር 100.00 (አንድ መቶ ብር) የማይመለስ
  • Bid Securityየጨረታ ማስከበሪያ ገንዘብ መጠን በየሎቱ ይለያያል።
  • opening dateበ13/01/2019 ዓ.ም ከጠዋት 4:00 ሰዓት
  • Categories Cleaning & Janitorial , Cloth And Shoes , Cosmotics

በኢፌዴሪ ጉምሩክ ኮሚሽን የጋላፊ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት በህገ ወጥ መንገድ ሲንቀሳቀሱ ተይዘው የተወረሱ የተለያዩ ኮስሞቲክስ ዘርፍ ዕቃዎች፣ አልባሳት ዘርፍ እቃዎች፣ የንጽህና መጠበቂያ ዘርፍ እቃዎች፣ ኤሌክትሮኒክስ ዘርፍ እቃዎች፣ ስፔር ፓርት ዘርፍ እቃዎች እና ልዩ ልዩ ዘርፍ እቃዎች በሀራጅ ጨረታ በጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 03/2019 ዓ.ም እቃዎቹን ባሉበት ሁኔታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።

በጉምሩክ ኮሚሽን የጋላፊ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት


የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 03/2019

በኢፌዴሪ ጉምሩክ ኮሚሽን የጋላፊ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት በህገ ወጥ መንገድ ሲንቀሳቀሱ ተይዘው የተወረሱ የተለያዩ ኮስሞቲክስ ዘርፍ ዕቃዎች፣ አልባሳት ዘርፍ እቃዎች፣ የንጽህና መጠበቂያ ዘርፍ እቃዎች፣ ኤሌክትሮኒክስ ዘርፍ እቃዎች፣ ስፔር ፓርት ዘርፍ እቃዎች እና ልዩ ልዩ ዘርፍ እቃዎች በሀራጅ ጨረታ በጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 03/2019 ዓ.ም እቃዎቹን ባሉበት ሁኔታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።

ስለሆነም፦ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የጨረታ መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቶች ጨረታው መሳተፍ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

  1. በጨረታው ሽያጭ ስርዓት ለመወዳደር የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች በዘርፉ የጸና የታደሰ ንግድ ፍቃድ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፊኬት፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር እና የዘመኑን ግብር የከፈለ ስለመሆኑ ከግብር ሰብሳቢ መስሪያ ቤት የተሰጠ ማስረጃ ማቅረብ ያለበት ሲሆን፤ በሀራጅ ጨረታ ለሚወዳደሩባቸው እቃዎች ከላይ የተጠየቁትን መረጃዎች በጨረታ መከፈቻ ቀን ይዘው መቅረብ አለባቸው፡፡
  2. ከላይ በተራ ቁጥር አንድ የተገለጸው ቢኖርም ግምታዊ ዋጋው ከብር 500 ሺህ በታች የሆነ ማንኛውም እቃ ለመግዛት የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ እያስፈልግም እንዲሁም የሚሸጠው እቃ ተሽከርካሪ ሲሆን የተሽከርካሪው አስመጪ ወይም ባለቤትና ቤተሰብ ከሆነ ሰው በስተቀር ማንኛውም እድሜው ከ 18 ዓመት በላይ የሆነ ኢትዮጵያዊ ቅድመ ሁኔታዎቹን ማሟላት ሳያስፈልገው በጨረታው ሊሳተፍ ይችላል።
  3. በሀራጅ ጨረታ ለወጡት እቃዎች ለመሳተፍ ለምድብ 1 ኮስሞቲክስ ዘርፍ ዕቃዎች ብር 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ ብር)፤ ለምድብ 2 አልባሳት ዘርፍ እቃዎች ብር 51,000 (ሃምሳ አንድ ሺህ ብር)፣ ለምድብ 3 አልባሳት ዘርፍ እቃዎች ብር 50,000 (ሃምሳ ሺህ ብር)፣ ለምድብ 4 ልዩ ልዩ ዘርፍ እቃዎች ብር 50,000 (ሃምሳ ሺህ ብር)፣ ለምድብ 5 ንጽህና መጠበቂያ ዘርፍ እቃዎች ብር 50,000 (ሃምሳ ሺህ ብር) ለምድብ 6 ንጽህና መጠበቂያ ዘርፍ እቃዎች ብር 50,000 (ሃምሳ ሺህ ብር)፣ ለምድብ 7 ኤሌክትሮኒክስ ዘርፍ እቃዎች ብር 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ ብር)፣ ለምድብ 10 ስፔር ፓርት ዘርፍ እቃዎች ብር 100,000 (አንድ መቶ ሺህ ብር) እና ለምድብ 11 ልዩ ልዩ ዘርፍ እቃዎች ብር 300,000 (ሶስት መቶ ሺህ ብር) ለየብቻው የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ CPO በቀጥታ አካውንት ቁጥር 1000296553216 በጋላፊ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ስም በማሰራት የጨረታ ሰነዱን እና በተራ ቁጥር አንድ የተገለጹትን መረጃዎች በመያዝ በቀን 13/01/2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ላይ መገኘት አለባቸው፡፡
  4. ከላይ በተራ ቁጥር 3 በተገለጸው መሰረት በቂ የጨረታ ማስከበሪያ ያላስያዘ ተጫራች መወዳደር ወይም መጫረት አይችልም።
  5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ዘወትር በስራ ሰዓት ከሰኞ እስከ አርብ እና ቅዳሜ ጠዋት ከ2፡00-6፡00 ሰዓት ከሰዓት በኋላ ከ9:00-12:00 የእቃዎቹን ዝርዝር የያዘ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር) በመከፈል ይህ ጨረታ ጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 13/01/2019 ጠዋት 3፡30 ሰዓት ድረስ በውርስ መጋዘን አስተዳደር የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 08 መግዛት ይችላሉ፡፡
  6. ለጨረታ የሚቀርቡ ዕቃዎች ለናሙና ዕይታ የሚቀርቡበት ጊዜ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት መስከረም 8/2019 ዓ.ም ጀምሮ እስከ መስከረም 13/2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡30 ድረስ ዘወትር ከሰኞ እስከ አርብ ጠዋት ከ2:00-6፡30 ሰዓት ከሰዓት በኋላ ከ9:00-12፡00 ሰዓት እና ቅዳሜ ጠዋት 2፡00-6:00 ሰዓት የእቃዎቹን ዝርዝር መመልከት ይችላሉ፡፡ በተጨማሪም ተጫራቶች የእቃውን ናሙና ሳያዩ በሰጡት ዋጋ ምክንያት ለሚፈጠር ቅሬታ በቅ/ጽ/ቤቱ ተቀባይነት የለውም፡፡
  7. ተጫራቾች በሚከተለው የጨረታ የጊዜ ሰሌዳ (ስኬጁል) መሠረት መጫረት ይችላሉ፡፡
ተ.ቁ ቅ/ጽ/ቤቱ ስም ቅ/ጽ/ቤት የንብረት መመልከቻ ቀን የጨረታው መዝጊያ እና መከፈቻ ቀንና ሰዓት
1 ጋላፊ ጉሙሩክ ቅ/ጽ/ቤት ሀራጅ ጨረታ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 13/01/2019 ከጠዋቱ 3፡30 ድረስ በ13/01/2019 ዓ.ም ከጠዋት 4:00 ሰዓት ይከፈታል።
  1. የጨረታ መክፍቻ ቦታ፦ ጋላፊ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት የሚካሄድ ሲሆን ጨረታው ተጫራቶች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በሚገኙበት ይከፈታል። ተጫራቶች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በቦታ ባይገኙም የጨረታ ሰነዱ በታዛቢዎች ፊት ይከፈታል፡፡ ተጫራቾች በተራ ቁጥር አንድ የተጠቀሱ ማስረጃዎች አርጅናል ይዘው መቅረብ አለባቸው፡፡
  2. በተጫራቾች የተሰጠ የመወዳደሪያ ዋጋ የጨረታው ሂደት ተጠናቆ የጨረታው ውጤት እስከሚገሰጽ ድረስ ፀንቶ ይቆያል፡፡
  3. በጨረታ ለሚሸጥ እቃ የጨረታ ውጤት እንደተገለጸ ከአሸናፊው ጋር የሽያጭ ውል እንደተደረገ ይቆጠራል፡፡
  4. ምድብ ለወጣላቸው ሀራጅ እቃዎች ጨረታው የሚካሄደው በምድብ ሲሆን ተጫራቶች አሸናፊ የሚያደርጋቸው ለምድቡ ባቀረቡት የእያንዳንዱ እቃዎች ዋጋ ድምር ከፍተኛው ዋጋ ይሆናል፡፡ በተጨማሪም ተጫራቾች በምድቡ ለቀረቡት ለእያንዳንዱ እቃዎች ዋጋ መስጠት አለባቸው፡፡
  5. ተጫራቶች ከአሸነፉበት የእቃ ዋጋ ላይ ተጨማሪ እሴት ታክስ (15%) የሚጨመር ይሆናል፡፡
  6. ተጫራቾች ያስያዙትን የጨረታ ማስከበሪያ (CPO) በተመለከተ ለአሸናፊው ተጫራች ካሸነፉት የዕቃ ዋጋ ላይ የሚታሰብላቸው ሲሆን ለተሸናፊ ተጫራቾች የጨረታ ውጤቱ በተገለጸ በ3 (ሶስት) ቀናት ውስጥ ተመላሽ ይደረግላቸዋል፡፡
  7. አሸናፊው ተጫራች ዕቃዎቹን ባሉበት ቦታ እና ሁኔታ የመረከብ ግዴታ አለበት፡፡ በተጨማሪም ለማጓጓዝ የሚያስፈልጉ ወጪዎችን ሁሉ ራሱ ይችላል፡፡
  8. አሸናፊ ተጫራች ማሸነፋቸውን በደብዳቤ ከተገለጸላቸው ቀን ጀምሮ በ05 (በአምስት) ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን እቃ ዋጋ ገቢ በማድረግ እቃውን መረከብ ያለበት ሲሆን ይህን ባይፈጽም ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት (CPO) ለመስሪያ ቤቱ ገቢ ተደርጎ ዕቃው በድጋሚ ለጨረታ የሚቀርብ ሲሆን ነገር ግን አሸናፊው የአሸነፈበትን የእቃ ዋጋ ገቢ አድርጎ በተቀመጠው ጊዜ ውስጥ እቃውን ያላነሳ እንደሆነ ለሚቆይበት ተጨማሪ ጊዜ የመጋዘን ኪራይ የሚከፍል ይሆናል፡፡ ሆኖም እቃውን በሁለት ወር ውስጥ ካላወጣ ለንብረቱ የተከፈለው ዋጋ ለመስሪያ ቤቱ ገቢ ሆኖ እቃው እንደተተወ ተቆጥሮ በሽያጭ ይወገዳል።
  9. በጨረታ የሚሸጠው እቃ በቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ከመወረሱ በፊት የእቃው አስመጪ ወይም ባለቤትና ቤተሰብ የነበሩ ሰዎች በጨረታው መሳተፍ አይችሉም፡፡
  10. ለጨረታ የቀረቡት እቃዎች የሚገኙበት ቦታ ጋላፊ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት መሆኑ ይታወቅ፡፡
  11. ኮሚሽኑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ ለተጨማሪ መረጃ ውርስ መጋዘን አስተዳደር የስራ ሂደት ስልክ ቁጥር 033-559-0114 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡

በጉምሩክ ኮሚሽን የጋላፊ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት

✨ messages.ai_summary
The Ethiopian Customs Commission's Galafi branch invites bids to buy confiscated goods—cosmetics, clothing, cleaning supplies, electronics, spare parts, and miscellaneous items—sold as-is via auction. Bidders need a valid trade license, VAT registration, TIN, and tax payment proof.
Save Tender