Tender Detail

Tender Details

  • Company የጎንደር ዩኒቨርሲቲ እቴጌ ምንትዋብ ንግድና ማማከር ኢንትርፕራይዝ
  • Address ጎንደር ከተማ : አማራ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0908085555
  • Website
  • Deadline05 Oct 2026, 10:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price200.00(ሁልት መቶ ብር)
  • Bid Security1%
  • opening dateጨረታው አየር ላይ ለተከታታይ 16 ቀን ቆይቶ በ 16 ኛው ቀን 4፡30 ሰዓት የሚከፈት ይሆናል፡፡
  • Categories Printing And Publishing

የጎንደር ዩኒቨርሲቲ እቴጌ ምንትዋብ ንግድና ማማከር ኢንተርፕራይዝ በ2019 ዓ.ም በተፈቀደ መደበኛ በጀት የሕትመት የግብዓት እቃዎች እና የስንዴ ዱቄት ግዥ በዘርፉ ንግድ ፈቃድ አውጥተው ከተሰማሩ ሕጋዊ አቅራቢዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈጸም ይፈልጋል፡፡

የጎንደር ዩኒቨርሲቲ እቴጌ ምንትዋብ ንግድና ማማከር ኢንትርፕራይዝ


የግዥ ጨረታ ማስታወቂያ

የግዥ መስያ ቁጥር E/M/T/C/E NCB/02/2019

የጎንደር ዩኒቨርሲቲ እቴጌ ምንትዋብ ንግድና ማማከር ኢንተርፕራይዝ በ2019 ዓ.ም በተፈቀደ መደበኛ በጀት የሕትመት የግብዓት እቃዎች እና የስንዴ ዱቄት ግዥ በዘርፉ ንግድ ፈቃድ አውጥተው ከተሰማሩ ሕጋዊ አቅራቢዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈጸም ይፈልጋል፡፡

1. በዘርፉ የወጣና ለዘመኑ የንግድ ሥራ ፈቃድ ኮፒ፣ ግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ኮፒ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ሰርተፍኬት ኮፒ ፣ በማንኛውም የመንግሥት ግዥ ጨረታ እንዲሳተፉ በሀገር ውስጥ ገቢ ባለሥልጣን የተሰጠ ድጋፍ ደብዳቤ ኮፒ ፈርመውና በድርጅታቸው ማህተም አረጋግጠው ዋናውን ማቅረብ አለባቸው፡፡

2. ማንኛውም፣ ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የሚሆን የጠቅላላ ዋጋውን 1% ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር በማያያዝ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ በጥሬ ገንዘብ ወይም ከታወቀ ባንክ በሚሰጥ ሲፒኦ ወይም በባንከ የተረጋገጠ የከፍያ ማዘዣ ቼከ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንከ ዋስትና በእቴጌ ምንትዋብ ንግድና ማማከር ኢንተርፕራይዝ ስም አሠርተው ማቅረብ አለባቸው። በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ ዋስትና ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ቢያንስ ከ90 ቀን በታች መሆን የለበትም፡፡

3. ተጫራቾች በተ.ቁ 1 እና 2 የተጠቀሱትን ማስረጃዎች በአንድ ፖስታ እንዲሁም የዋጋ መወዳደሪያ ሰነዳቸውን ኦርጅናልና ኮፒ በማለት በተለያየ ፖስታ በማሸግና በማያሻማ ሁኔታ በጀርባው ላይኦርጅናልና ኮፒ በሚል ቃል በጽሑፍ በማመላከትና በድርጅታቸው ማህተም በማረጋገጥ ማቅረብ አለባቸው፡፡

4. ሁሉም (ሶስቱም) ፖስታዎች በአንድ ትልቅ ፖስታ ተጠቃለው ታሽገውና በድርጅቱ ማህተም ተረጋግጠው መግባት አለባቸው፡፡ 

5. ማንኛውም ተጫራች የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ጎንደር ዩኒቨርሲቲ እቴጌ ምንትዋብ ንግድና ማማከር ኢንተርፕራይዝ ፋይናንስና አስተዳደር ገንዘብ ያዥ ቢሮ ቁጥር 06 የማይመለስ ብር200.00 (ሁለት መቶ ብር) በመከፈል መውሰድ ይችላሉ፡፡

6. ተጫራቾች የጨረታ ማወዳደሪያ ሰነዳቸውን በጎንደር ዩኒቨርሲቲ እቴጌ ምንትዋብ ንግድና ማማከርኢንተርፕራይዝ ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ይህ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በሚቆጠር እስከ 16ኛው ቀን ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይችላሉ። ጨረታውም ታዛቢዎችና ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዚሁ ዕለት ከረፋዱ 4፡01 ታሽጎ በዕለቱ 4፡30 ሰዓት እቴጌ ምንትዋብ ንግድና ማማከር ኢንተርፕራይዝ ይከፈታል፡፡

የጎንደር ዩኒቨርሲቲ እቴጌ ምንትዋብ ንግድና ማማከር ኢንተርፕራይዝ

✨ messages.ai_summary
Gondar University Etege Mintiwab Trade and Consultancy Enterprise seeks eligible suppliers with a valid trade license for the sector to bid for printing input materials and wheat flour. Bidders must submit a trade license copy, taxpayer ID, VAT certificate, and a domestic revenue support letter.
Save Tender