የምስራቅ ዕዝ ሜንቴናንስ መምሪያ ግልፅ ጨረታ ቁጥር 01/2019 ዓም በሀገር መከላከያ ሚ/ር የምስራቅ ዕዝ ሜንቴናንስ መምሪያ ለ2019 በጀት አመት ለዕዙ አገልግሎት የሚውል፡-
በአገር መከላከያ ሚኒስቴር የምስራቅ ዕዝ ሜንቴናንስ መምሪያ ግዥ ዴስክ ሐረር
የጨረታ ማስታወቂያ
የምስራቅ ዕዝ ሜንቴናንስ መምሪያ ግልፅ ጨረታ ቁጥር 01/2019 ዓም በሀገር መከላከያ ሚ/ር የምስራቅ ዕዝ ሜንቴናንስ መምሪያ ለ2019 በጀት አመት ለዕዙ አገልግሎት የሚውል፡-
- የቀላልና ከባድ ተሽከርካሪዎች መለዋወጫ ዕቃዎች
- የጄኔተር እና የዳቦ ማሽን መለዋወጫ ዕቃዎች
- የወታደራዊ ተሽከርካሪ አላቂ መስሪያ ዕቃዎች
በዘርፋ ከተሰማሩ ህጋዊ ተጫራቾች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶችን የሚያሟሉ ተጫራቾች ጨረታውን መወዳደር የሚችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡ በዚህ መሠረት በተሰማሩበት ሥራ ዘርፍ የታደሰ ንግድ ፍቃድ፣ የግብር ከፋይ ሰርትፍኬት ያላቸው ፣ የተጨማሪ ዕሴት ታከስ ሰርተፍኬት ያላቸው ፣ የምዝገባ የምስክር ወረቀት ያላቸው ፣ ተጫራቾች የማይመለስ ብር 500/አምስት መቶ ብር/ ብቻ በመክፈል ዘወትር በስራ ሰዓት ከጠዋቱ ከ2:30 እስከ 6፡00 ሰዓት እና ከ7:30 እስከ 11፡00 ሰዓት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ሐረር ምስራቅ ዕዝ ሜንቴናንስ መምሪያ በሚገኘው ግዥ ዴስክ ቢሮ በመቅረብ ጨረታ ስነድ መግዛት ይችላሉ፡፡ ጨረታው መስከረም 18/2019 ዓ/ም ከጠዋቱ 4፡15 ሰዓት ተዘግቶ በዕለቱ 4:30 ተጫራቶች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ሐረር ቀላዳንባ በሚገኘው ሜንቴናንስ መምሪያ ግቢ ይከፈታል፡፡ መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከሰም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው፡፡
ስልክ ቁጥር 0920437143 0937120956 0913971279
በሀገር መከላከያ ሚኒስቴር የምስራቅ ዕዝ ሜንቴናንስ መምሪያ ግዥ ዴስክ
