Tender Detail

Tender Details

  • Company የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልላዊ መንግሥት መንገዶች ባለስልጣን
  • Address በምዕራብ ኦሞ ዞን ጀሞ ከተማ ፡ ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0474527941
  • Website
  • Deadline02 Oct 2026, 9:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን ጋዜጣ
  • Bid Document Priceብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) የማይመለስ
  • opening dateበ16ኛ ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት
  • Categories Construction Equipment And Machinery , Machinery , Machinery Rental

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልላዊ መንግስት መንገዶች ባለስልጣን ዋና መ/ቤት በተለያዩ ፕሮጀክቶች እና ጥገና ጽ/ቤቶች ለሚያከናውናቸው የመንገድ ግንባታ እና ጥገና ሥራ አገልግሎት የሚውሉ ከዚህ በታች የተዘረዘሩ ማሽነሪዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመከራየት ይፈልጋል።


ጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ መስያ ቁጥር ደ/ም/መ/ባ/02/2019

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልላዊ መንግስት መንገዶች ባለስልጣን ዋና መ/ቤት በተለያዩ ፕሮጀክቶች እና ጥገና ጽ/ቤቶች ለሚያከናውናቸው የመንገድ ግንባታ እና ጥገና ሥራ አገልግሎት የሚውሉ ከዚህ በታች የተዘረዘሩ ማሽነሪዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመከራየት ይፈልጋል።

የማሽኑ ዓይነት የማሽኑ ፈረስ ጉልበት የስሪት ዘመን እ.ኤ.አ የሚጠቀመው የነዳጅ ዓይነት ለአንድ ማሽን የሚፈለገው ሰዓት ብዛት በዲስትሪከት ቦንጋ ታርጫ ሚዛን
ዶዘር 305 እና በላይ 2012 እና በላይ ናፍጣ 1200 2 2 2
ኤክስካቫተር 247 እና በላይ 2016 እና በላይ ናፍጣ 1200 1 1 1
ሮለር 140 እና በላይ 2013 እና በላይ ናፍጣ 800 2 2 2

በዚህ መሰረት ከዚህ በታች በተዘረዘሩት ዝርዝሮች መሰረት አቅራቢዎችን ይጋብዛል፡-

  1. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ የሚያስችለውን የዘመኑን ግብር የተከፈለበትን ከሚፈለገው አገልግሎት ጋር የተዛመደ የንግድ ሥራ ፈቃድ ወይም የአገልግሎት ሥራ ፈቃድ፣ የአቅራቢነት ምስክር ወረቀት፣ ተጨማሪ እሴት ታክስ፣ የንግድ ምዝገባ ሰርተፍኬት፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (TIN NO) እና በጨረታ ለመሳተፍ ከሀገር ውስጥ ገቢ ቢሮ የድጋፍ ደብዳቤ ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር አያይዞ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
  2. ተጫራቾች ዋጋቸውን በታሸገ ኤንቨሎፕ የፋይናንሻል እና ቴክኒካል ፕሮፖዛሉን በተለያዬ ፖስታ በማድረግ አንድ ዋና እና ሁለት ኮፒ ‹‹ኦርጅናል›› እና ‹‹ኮፒ›› በማለት እና የጨረታ ማስከበሪያውንም ለእያንዳንዱ ሎት በተለያዬ ፖስታ ለየብቻ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  3. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) በባለስልጣን መ/ቤቱ የባንክ ሂሳብ ቁጥር 1000642058936 ገቢ በማድረግ የባንክ ደረሰኝ በመያዝ ከባለስልጣን መ/ቤቱ ግዥ እና ንብረት አስተዳደር ኬዚ ቲም ቢሮ መውሰድ ይችላሉ።
  4. የጨረታው አሸናፊ የሚወሰነው በጨረታ ሰነዱ ውስጥ በተመለከቱት መስፈረቶች መሰረት ሲሆን ጨረታው ዜግነትን ሳይመለከት ለማንኛውም አቅራቢ ክፍት ነው።
  5. አቅራቢዎች ጨረታውን ለዚህ ተግባር በተዘጋጀ ሳጥን ገቢ የሚያደርጉበት ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛ ቀን ሲሆን ጨረታው ከቀኑ 11፡30 ሰዓት ድረስ ይሆናል። ጨረታው በ16ኛ ቀን ከጠዋቱ 3፡00 ተዘግቶ በዕለቱ ጠዋት 3፡30 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት ይከፈታል። ዕለቱ የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይሆናል።
  6. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) በቅድመ ሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና፣ በባንክ በተረጋገጠ ቼክ ወይም ሲፒኦ (CPO) ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር በማያያዝ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፣ ከዚህ ውጪ በኢንሹራንስ ወይም በሌላ መልክ የሚቀርብ የጨረታ ማስከበሪያ ተቀባይነት የለውም።
  7. ተጫራቾች በጨረታው ደንብና መመሪያ መሰረት ጨረታቸውን ማቅረብ አለባቸው ከጨረታ ደንብና መመሪያ ውጪ የሚቀርብ የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት የለውም።
  8. ተጫራቾች ከ2015 ዓ.ም ጀምሮ በተመሳሳይ ዘርፍ ከሰሩበት የመንግሥት መ/ቤት ቢያንስ አንድ የመልካም ሥራ አፈፃፀም ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር አያይዞ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
  9. መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለበለጠ መረጃ ተጫራቾች የሚከተለውን አድራሻ መጠቀም ይችላሉ።

በምዕራብ ኦሞ ዞን ጀሙ ከተማ በሚገኘው የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል መንግስት መንገዶች ባለስልጣን ዋና መ/ቤት በግብዓት አቅርቦትና አስተዳደር ዘርፍ ግዥና ንብረት አስተዳደር ኬዚ ቲም ቢሮ በአካል በመቅረብ ማነጋገር ወይም በስልክ ቁጥር 0474527941 0474527727 ደውለው ማነጋገር ይቻላል፡፡

ምዕራብ ኦሞ ዞን ጀሙ ኢትዮጵያ

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልላዊ መንግስት መንገዶች ባለስልጣን ዋና መ/ቤት

✨ messages.ai_summary
South West Ethiopia Peoples' Region Roads Authority seeks to rent out bulldozers, excavators and rollers for road construction and maintenance projects. Open to any supplier regardless of nationality. Bidders must submit a valid business or service license, supplier certificate, VAT and TIN registration, tax clearance, and a supporting letter from the inland revenue office.
Save Tender

Dashen Breweries S.C invites interested & qualified Bidder for Supply, Delivery, Commissioning, Test...

READ MORE
Procurement of Machinery

READ MORE