ታህሰብ የንግድ ሥራዎች አከሲዮን ማህበር በሕንጻ ውስጥ ያለውን የፓርኪንግ ቦታ መሬቱን ልሾ እና በቀለም ለማስዋብ የሚያስፈልጉ ዕቃዎችን አቅርቦ የሚሰራ ባለሙያ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡
የጨረታ ማስታወቂያ
ታህሰብ የንግድ ሥራዎች አከሲዮን ማህበር በሕንጻ ውስጥ ያለውን የፓርኪንግ ቦታ መሬቱን ልሾ እና በቀለም ለማስዋብ የሚያስፈልጉ ዕቃዎችን አቅርቦ የሚሰራ ባለሙያ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡
በዚህም መሠረት፡-
- በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያለው
- የዘመኑን ግብር አጠናቆ ለመከፈሉ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል
- ተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ መሆናቸውን ማረጋገጫ ሰነድ ማቅረብ የሚችል
- የጨረታ ሰነዱ ሽያጭ የሚካሄደው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 10 (አስር) ተከታታይ ቀናት ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች ይህ ጨረታ በማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የማይመለስ ብር 1000 (አንድ ሺ ብር) በመከፈል ዘወትር ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ጀምሮ እስከ ቀኑ 10፡30 ድረስ አከሲዮን ማህበሩ ገንዘብ ቤት በመቅረብ የጨረታ ሰነድ እና የተጫራቾች መመሪያ መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበት ዋጋ በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ በወጣ 11ኛ (አስራ አንደኛው) የሥራ ቀን ተጫራቶች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በአከሲዮን ማህበሩ ጽ/ቤት ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ብር 25,000 (ሃያ አምስት ሺ ብር) በባንክ በተመሰከረለት ሲፒኦ /በታህሰብ የንግድ ስራዎች አከሲዮን ማህበር ስም በማዘጋጀት ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ሌሎች ተጫራቾች ባቀረቡት ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ መስጠት አይቻልም፡፡
- አሸናፊው የጨረታ ውጤት ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ ባሉት 5 (አምስት) ተከታታይ ቀናት ውስጥ ቀርቦ የስራ ውል መዋዋል አለበት፡፡
- ለአከሲዮን ማህበሩ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታው በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ስልክ ቁጥር 2 79 30 65
ታህሰብ የንግድ ሥራዎች አከሲዮን ማህበር
✨ messages.ai_summary
Tahseb Trading Businesses Share Company seeks a qualified contractor to supply materials and finish/paint the floor of its building's parking area. Bidders must have a renewed business license, proof of tax payment, and VAT registration.
