ሕብረት ባንክ አ.ማ. አዲስ አበባ ከተማ፣ በልደታ ክ/ከተማ፣ በወረዳ 7 ስንጋ ተራ አካባቢ አዲስ ባስገነባው የዋናው መስሪያ ቤት ሕብረት ሕንፃ ዘጠነኛ /9ኛ/ ወለልን ለቢሮ አገልግሎት እንዲውል በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማከራየት ይፈልጋል:: ስለሆነም ኪራይ ፈላጊዎች ከዚህ በታች በተገለፀው መሠረት የጨረታ ሰነዱን በመግዛት የመጫረቻ ሰነድ ሊያቀርቡ ይችላሉ::
የጨረታ ማስታወቂያ
ጨረታ ቁጥር፡ ሕባ/001/2019
ሕብረት ባንክ አ.ማ. አዲስ አበባ ከተማ፣ በልደታ ክ/ከተማ፣ በወረዳ 7 ስንጋ ተራ አካባቢ አዲስ ባስገነባው የዋናው መስሪያ ቤት ሕብረት ሕንፃ ዘጠነኛ /9ኛ/ ወለልን ለቢሮ አገልግሎት እንዲውል በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማከራየት ይፈልጋል:: ስለሆነም ኪራይ ፈላጊዎች ከዚህ በታች በተገለፀው መሠረት የጨረታ ሰነዱን በመግዛት የመጫረቻ ሰነድ ሊያቀርቡ ይችላሉ::
- ተጫራቾች ይህ ጨረታ ለመጀመሪያ ጊዜ በጋዜጣ ከወጣ ከ2 ቀናት በኋላ ማለትም ከመስከረም 9 ቀን 2019 ዓ.ም. ጀምሮ እስከ መስከረም 21 ቀን 2019 ዓ.ም. የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ) በአቅራቢያ በሚገኙ የሕብረት ባንክ ቅርንጫፍ በሂሳብ ቁጥር IN0403007 በመክፈል የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ::
- የጨረታ ሰነዱን በልደታ ክፍለ ከተማ፤ ወረዳ 7 ሰንጋ ተራ አካባቢ በሚገኘው የባንኩ ዋና መስሪያ ቤት ሕንፃ 19ኛ ወለል በግዥ እና ኮንትራት አስተዳደር መምሪያ በመገኘት መግዛት ይቻላል::
- ለጨረታ የቀረበውን ወለል ለመጎብኘት የሚፈልጉ ተጫራቾች ጨረታው ክፍት ሆኖ በሚቆይበት ማለትም ከመስከረም 7 ቀን 2019 ዓ.ም. ጀምሮ እስከ መስከረም 21 ቀን 2019 ዓ.ም. ውስጥ ሰኞ፣ ዕሮብ እና አርብ ከጠዋቱ 3፡00 - 10፡00 ሰዓት በባንኩ ዋና መ/ቤት በመገኘት ማየት ይችላሉ::
- ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዱን ሞልተው ከማስገባታቸው በፊት በጨረታ ሰነዱ ላይ የተካተተውን የተጫራቾች መመሪያ በደንብ ማየት ይኖርባቸዋል::
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (Bid Bond) ለጨረታ የቀረበውን ይዞታ ቢከራዩ የሚከፍሉትን የአንድ ወር ኪራይ አንድ አራተኛ (25%) በባንክ የክፍያ ማዘዣ (ሲፒኦ) የጨረታ ሰነዱን ሲያቀርቡ ማስያዝ የሚኖርባቸው ሲሆን የዋስትናው የአገልግሎት ጊዜውም Validity Date/ ዘጠና (90) ቀናት ይሆናል፣
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የሚያስይዙትን የባንክ የክፍያ ማዘዣ (ሲፒኦ) የሚያስሩት ከሕብረት ባንክ ውጪ በሆኑ በማንኛውም ባንኮች መሆን አለበት::
- እያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ መቅረብ አለበት::
- ተጫራቾች ለጨረታው አስፈላጊ የሆኑ ሰነዶችን በማሟላት ልደታ ክፍለ ከተማ፣ ወረዳ 7፣ ሰንጋ ተራ አካባቢ በሚገኘው የባንኩ ዋና መስሪያ ቤት ሕንፃ 19ኛ ፎቅ በግዥ እና ኮንትራት አስተዳደር መምሪያ በሚገኝ የጨረታ ማስገቢያ ሳጥን ውስጥ መስከረም 19፣ 20 እና 21 ቀን 2019 ዓ.ም. እስከ ከቀኑ 10፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይችላሉ::
- ጨረታው መስከረም 22 ቀን 2019 ዓ.ም. ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት በባንኩ ዋና መስሪያ ቤት አራተኛ /4ኛ/ ወለል ላይ በሚገኘው አዳራሽ ተጫራቾች/ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል::
- በጨረታ ሰነዱ ላይ ባለው የተጫራቾች መመሪያ መሠረት ያልቀረበ የመጫረቻ ሰነድ/ተጫራች ከውድድር ሊሰረዝ ይችላል::
- ባንኩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 011- 470 41 72 ደውሱ መጠየቅ ይቻላል::
ሕብረት ባንክ
በሕብረት እንደግ!!
✨ messages.ai_summary
Hibret Bank invites bids to rent the 9th floor of its new headquarters building in Addis Ababa for office use. Bidders must buy the tender document, follow the bidder instructions, submit in sealed envelopes, and provide a bid bond as a CPO from a bank other than Hibret Bank.
