በየካ ክ/ከተማ ወረዳ 10 የሚገኘው የሚሊንየም አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት በ2019 ዓ.ም ለትምህርት ቤቱ የፅዳት እቃዎች የእስቴሽነሪ አላቂና ቋሚ የቢሮ ዕቃዎች በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
የግዥ ጨረታ መስያ ቁጥር 01/2019
በየካ ክ/ከተማ ወረዳ 10 የሚገኘው የሚሊንየም አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት በ2019 ዓ.ም ለትምህርት ቤቱ የፅዳት እቃዎች የእስቴሽነሪ አላቂና ቋሚ የቢሮ ዕቃዎች በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም-
- ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉበትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታውን ዝርዝር የያዘ ሰነድ ለሚጫረቱበት አይነት (ሎት) የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) በመከፈል ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 10 ቀናት ዘወትር በስራ ሰአት በየካ ከ/ከተማ ወረዳ 10 የሚገኘው የሚሊኒየም አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ፋይናንስ ቢሮ ቁጥር 10 መቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡
- በዚሁ መሰረት ለሎት፡ የፅዳት እቃ ብር 5000 አምስት ሺ ብር/፣ ሎት 2 የደንብ ልብስ 5000 /አምስት ሺ ብር/፤ ሎት 3 እስቴሽነሪ አላቂና ቋሚ የቢሮ እቃ ብር 6000/ስድስት ሺ ብር/፣ ሎት 4 ቋማ እቃ እና ኤሌክትሮኒክስ 8000/ ስምንት ሺ ብር/ በሲፒኦ ማስያዝ ይኖርባችኋል፡፡
- የሚቀርቡት ነጠላ ዋጋ ተጨማሪ እሴት ታከስ/ቫት/ ያካተተ እና የቀረበው ነጠላ ዋጋ ተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ጨምር መሆኑን መገለጫ መስጠት አለበት፡፡
- ጥቃቅንና አነስተኛ ተጫራቾች ካደራጃቸው አካል በጨረታ መሳተፍ እንዲችሉ የሚገልፅ የድጋፍ ደብዳቤ ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የጨረታ ማስከበሪያ እና የውል ማስከበሪያ የምታፅፉ ጥቃቅን እና አነስተኛ አቅራቢዎች የተሰማራችሁበትን የንግድ ስራ መስክ /ዘርፍ/ የሚገልፅ ደብዳቤ መቅረብ አለባት፡፡
- ተጫራቾች የሚጫረቱበት ዋጋ በሚገባ በታሸገ እና ማህተም ባረፈበት ኤንቨሎፕ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ በስራ ሰአት ከላይ በተጠቀሰው ቢሮ በመቅረብ የሚወዳደሩበት ዋጋ በተዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ላይ በመሙላት ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ለሚጫረቱባቸው እቃዎች ናሙና ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ያሸነፉትን ዋጋ 10 ፐርሰንት የውል ማስከበሪያ ማስያዝ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች በጨረታው አሸናፊ የሆኑባቸውን እቃዎች በሙሉ ገቢ ማድረግ ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን ወይም በዓል ከሆነ በሚቀጠለው የስራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ታሽጎ ወዲያው 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግልጽ ይከፈታል፡፡
- መስሪያ ቤቱ ለጨረታ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻ :- የካ ከ/ከተማ ወደ ኮተቤ በሚወስደው መንገድ በተለምዶ 02 ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ወደ ህዝብ ደህንነት በሚያስወጣው አስፋልት ከፍ ብሎ ሚሊኒየም አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት። ለተጨማሪ መረጃ በሲቁ 011 668 34 63 ወይም ወረዳ 10 ሚሊኒየም አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ፋይናንስ ቢሮ በግንባር በመቅረብ አስፈላጊውን መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡
ሚሊንየም አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት
✨ messages.ai_summary
Millennium General Secondary School seeks to procure cleaning supplies, stationery, consumable and fixed office supplies, uniforms, and electronics through a tender. Bidders must hold a valid business license, provide tax payment proof, submit samples, and deposit a 10% contract bond.
