የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ በ2019 በጀት ዓመት ለቢሮ አገልግሎት የሚውሉ ከዚህ ቀጥሎ በሎት የተከፋፈሉ ግዥዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 01/2019
የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ በ2019 በጀት ዓመት ለቢሮ አገልግሎት የሚውሉ ከዚህ ቀጥሎ በሎት የተከፋፈሉ ግዥዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
- ሎት አንድ (1) አላቂ የቢሮ ዕቃዎችና የጽህፈት መሳሪያ
- ሎት ሁለት (2) የጽዳት ዕቃዎች
- ሎት ሶስት (3) ኤሌክትሮኒከስና ተጓዳኝ ዕቃዎች
- ሎት አራት (4) ፈርኒቸር ዕቃዎች
- ሎት አምስት (5) ሞተር ሳይክል ናቸው፡፡
በዚሁ መሰረት በጨረታው መሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች የሚከተሉትን ማሟላት ይኖርባችኋል፡፡
- በሚወዳደሩበት ዘርፍ አግባቢነት ያለውና ለዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር፣ የዘመኑን ግብር ስለመከፈላቸው ከሚመለከተው አካል ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
- በፌዴራል ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ ዌብ ሳይት የተመዘገቡ ስለመሆናቸው ከዌብ ሳይት አትመው ከጨረታ ሰነድ ጋር ማያያዝ የሚችሉ ወይም በክልሎች በአቅራቢነት ስለመመዝገባቸው የአቅራቢነት የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣
- የግዥው መጠን ከብር 500,000 /አምስት መቶ ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ ለተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣
- ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ ሥራ ቀናት ለተጫራቾች ክፍት ሆኖ ይቆያል፡፡
- ተጫራቾች ጨረታው ክፍት ሆኖ በሚቆይበት ጊዜ ውስጥ በቢሮው የተዘጋጀውንና የጨረታውን ዝርዝር ሁኔታ የሚያሳይ የጨረታ ሰነድ የንግድ ፈቃዳቸውን በማሳየት ዘወትር በሥራ ሰዓት ቢሮ ቁጥር 7 ቀርበው በእያንዳንዱ ሎት የማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል መውሰድና የመጫረቻ ሰነዶቻቸውን በአግባቡ በማዘጋጀት በፖስታ አሸገው ጨረታው ለተጫራቾች ክፍት ሆኖ በሚቆይበት ቀን እስከ 1፡25 ሰዓት ድረስ በቢሮው ቅጥር ግቢ ውስጥ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው ክፍት ሆኖ በሚቆይበት የመጨረሻው ቀን 11፡30 ሰዓት ላይ ተዘግቶ ቀጥሎ ባለው 11ኛው ቀን ከቀኑ 3፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግዥ ፋይ/ንብ/ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 10 ይከፈታል፡፡ 10ኛው እና ከኛው ቀን የሚውለው ቅዳሜና እሁድ ወይም የህዝብ በዓላት ቀን ላይ ከሆነ ጨረታው በሚቀጥለው የሥራ ቀን በ3፡00 ሰዓት ተዘግቶ 3፡30 ሰዓት ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች ከላይ በተገለጸው መ/ቤት ስም ለጨረታው ማስከበሪያ የሚሆን
- ሎት አንድ (1) ብር 10,000.00
- ሎት ሁለት (2) ብር 4,000.00
- ሎት ሶስት (3) ብር 50,000.00
- ሎት አራት (4) ብር 30,000.00
- ሎት አምስት (5) ብር 40,000.00 ዋስትና ሲ.ፒ.ኦ እና ፋይናንሻል እንዲሁም ስፔስፊኬሽ ለወጣላቸው ዕቃዎች የፋይናንሻልና የቴክኒክ ሰነድና ሲ.ፒ.ኦ በተለያየ ፖስታ በማሸግ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ የሚቀርበው የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የጨረታው አየር ላይመቆያ ጊዜ ከሚያበቃበት መጨረሻው ቀን ጀምሮ ባሉት 45 ተከታታይ ቀናት የሚያገለግል መሆን ይኖርበታል፡፡
- አሸናፊው ተጫራች አሸናፊነቱ ከተገለጸበት በ05 ቀናት ውስጥ አሸናፊ የሆነበትን የዕቃ ጠቅላላ ዋጋ 10% የውል ማስከበሪያ ሲ.ፒ.ኦ በመያዝ በ15 ቀናት ውስጥ ዕቃውን አጠናቀው ለማቅረብ ውል መግባት የሚችሉ መሆን አለበት፡፡
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት የፋይናንስ፣ የቴክኒካል ግምገማና ሲ.ፒ.ኦ ፖስታ በሎት ተለይቶ መቅረብ አለበት፡፡
- ቢሮው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 046-221-9988 / 046-220-03-26 በመደወል ማብራሪያ መጠየቅ የሚቻል መሆኑን እንገልጻለን፡፡
ሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ
✨ messages.ai_summary
The Sidama National Regional State Industry Development Bureau seeks suppliers for office consumables and stationery, cleaning materials, electronics and accessories, furniture, and motorcycles, divided into five lots. Bidders must have a valid business license, tax identification, tax payment proof, and federal or regional supplier registration.
