Tender Detail

Tender Details

  • Company Oromia Seed Enterprise (የኦሮሚያ ምርጥ ዘር ኢንተርፕራይዝ)
  • Address ጎተራ አጎና ሠራዊት ሲኒማ አጠገብ ባለኬር ሕንፃ /Baleker Tower/ 4ኛ ፎቅ : አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 011-416 03 09
  • Websitehttps://oromiaseedenterprise.com/
  • Deadline27 Sep 2026, 2:00 PM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Priceብር 360
  • opening dateጨረታው አየር ላይ ለተከታታይ 15 የስራ ቀናት ቆይቶ በ 16 ኛው ቀን 8፡30 ሰዓት የሚከፈት ይሆናል፡፡
  • Categories Maintenance And Repair , Vehicle (Garage Service)

የኦሮሚያ ምርጥ ዘር ኢንተርፕራይዝ የተለያዩ ተሸከርካሪዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሠራት


የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር OSE NCB/004/2019

የኦሮሚያ ምርጥ ዘር ኢንተርፕራይዝ የተለያዩ ተሸከርካሪዎችን  በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሠራት ይፈልጋል።

ስለሆነም አስፈላጊውን መስፈርት የምታሟሉ በጨረታውም ሳቶ ና የምትቸሉ መሆኑን እየገለጽን ተጫራቾች፡-

  1. የንግድ ምዝገባ ሰርተፊኬት
  2. ዘመኑን የታደሰ ንግድ ፈቃድ
  3. የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ ሰርተፊኬት
  4. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (Tin No)
  5. የአቅራቢነት ማስረጃ (Suppliers List)
  6. የሚፈለግባቸውን የመንግሥት ግብር ስለመወጣታቸው የሚገልጽ ማስረጃ፣ ፎቶ ኮፒ ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር በማያያዝ ማቅረብ አለባቸው፡፡

ተጫራቾች ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ፡- ለ15 ተከታታይ ቀናት ሰነዱን በመግዛት በ16ኛው የሥራ ቀን ጨረታው የሚዘጋና የሚከፈት ይሆናል፡፡ የጨረታ ሰነድ መግዣ ዋጋ ብር 360 ሶስት መቶ ስልሳ መሆኑን እየገለጽን፣ ተጫራቾች የዋጋ ማቅረቢያቸውን ቢፖሲታ በማሸግ በተጠቀሱት ቀናት ከጠዋቱ 2:30-8:00 ሰዓት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ በማስገባት በጨረታው እንዲትሳተፉ እጋብዛለን፡፡

የጨረታ ሳጥኑ ከላይ በተጠቀሱት ቀናት 8፡00 ሰዓት ተዘጥቶ በ8፡3ዐ ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኢንተርፕራይዙ ዋና መ/ቤት ጎተራ እና ሠራዊት ሲኒማ አጠገብ ባለኬር ህንፃ Baleker Tower 4ኛ ፎቅ ላይ በሚገኘው የኦሮሚያ ምርጥ ዘር ኢንተርፕራይዝ ቢሮ ቁጥር 402 ይከፈታል፡፡

ኢንተርፕራይዙ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

የኢንተርፕራይዙ የሥራ ሰዓት፡- ከሰኞ እስከ አርብ ጠዋት ከ3፡ዐዐ-6፡3ዐ ከሰዓት በኋላ ከ7፡3ዐ-11፡3ዐ ነው፡፡

ማብራሪያ፡- ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 011-416 03 09/011-466-25-27 መጠየቅ ይችላሉ፡፡

የኦሮሚያ ምርጥ ዘር ኢንተርፕራይዝ

✨ messages.ai_summary
Oromia Seed Enterprise invites bids to repair various vehicles through open tender. Bidders must submit a business registration certificate, renewed trade license, VAT registration, TIN, supplier list, and proof of tax payment.
Save Tender