የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ለ2019 በጀት ዓመት የተሸከርካሪ ዓመታዊ ጥገና አገልግሎት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
በግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ 01/2019
የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ለ2019 በጀት ዓመት የተሸከርካሪ ዓመታዊ ጥገና አገልግሎት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
በዚሁ መሰረት በጨረታው መሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች የሚከተሉትን ማሟላት ይኖርባችኋል፡፡
- በሚወዳደሩበት ዘርፍ አግባብነት ያለውና ለዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር፣ የዘመኑን ግብር ስለመከፈላቸው ከሚመለከተው አካል ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡
- በፌዴራል ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ ዌብ ሳይት የተመዘገቡ ስለመሆናቸው ከዌብ ሳይት አትመው ከጨረታ ሰነድ ጋር ማያያዝ የሚችሉ ወይም በክልሎች በአቅራቢነት ስለመመዝገባቸው የአቅራቢነት የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣
- የግዥው መጠኑ ከብር 200,000 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ ለተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣
- ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ ሥራ ቀናት ለተጫራቾች ክፍት ሆኖ ይቆያል፡፡
- ተጫራቶች ጨረታው ክፍት ሆኖ በሚቆይበት ጊዜ ውስጥ በቢሮው የተዘጋጀውንና የጨረታውን ዝርዝር ሁኔታ የሚያሳይ የጨረታ ሰነድ የንግድ ፈቃዳቸውን በማሳየት ዘወትር በሥራ ሰዓት ቢሮ ቁጥር 7 ቀርበው በእያንዳንዱ ሎት የማይመለስ ብር 200.00/ሁለት መቶ ብር/ በመከፈል መውሰድና የመጫረቻ ሰነዶቻቸውን በአግባቡ በማዘጋጀት በፖስታ አሽገው ጨረታው ለተጫራቾች ክፍት ሆኖ በሚቆይበት ቀን እስከ 1፡25 ሰዓት ድረስ በቢሮው ቅጥር ግቢ ውስጥ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው ክፍት ሆኖ በሚቆይበት የመጨረሻው ቀን 11፡30 ሰዓት ላይ ተዘግቶ ቀጥሎ ባለው በ11ኛው ቀን ከቀኑ 3፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግዥ ፋይ/ንብ/ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 10 ይከፈታል፡፡ 10ኛው እና 11ኛው ቀን የሚውለው ቅዳሜና እሁድ ወይም የህዝብ በዓላት ቀን ላይ ከሆነ ጨረታው በሚቀጥለው የሥራ ቀን በ3፡00 ሰዓት ተዘግቶ 3፡30 ሰዓት ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ስም ለጨረታው ማስከበሪያ የሚሆን ብር 10,000.00 /አስር ሺህ ብር/ ዋስትና በጥሬ ገንዘብ ወይም በሲፒኦ ወይም በባንክ የተረጋገጠ ዋስትና ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- የፋይናንሻልና የቴክኒክ ሰነድና ሲ.ፒ.ኦ በተለያየ ፖስታ በማሸግ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ የሚቀርበው የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የጨረታው እየር ላይ መቆያ ጊዜ ከሚያበቃበት የመጨረሻው ቀን ጀምሮ ላሉት 45 ተከታታይ ቀናት የሚያገለግል መሆን ይኖርበታል
- አሸናፊው ተጫራች አሸናፊነቱ ከተገለጸበት በ 05 ቀናት ውስጥ አሸናፊ የሆነበትን የጥገና አገልግሎት ጠቅላላ ዋጋ 10% የውል ማስከበሪያ ሲ.ፒ.ኦ በመያዝ በ 15 ቀናት ውስጥ ለአንድ ዓመት የሚቆይ ጥገና ውል መግባት የሚችሉ መሆን አለበት፡፡
- ቢሮው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
በስልክ ቁጥር 046-221-9988 / 046-220-03-26 በመደወል ማብራሪያ መጠየቅ የሚቻል መሆኑን እንገልጻለን፡፡
ሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ሀዋሳ
✨ messages.ai_summary
The Sidama National Regional State Industry Development Bureau seeks annual vehicle maintenance services via open tender. Bidders need a valid business license, tax registration and payment proof, federal or regional supplier registration, and VAT registration if the contract exceeds 200,000 birr.
