Tender Detail

Tender Details

  • Company የቴፒ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት
  • Address ቴፒ ከተማ : ደቡብ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0924286400
  • Website
  • Deadline02 Oct 2026, 10:00 AM
  • magazineAddis Zemen
  • Bid Document Priceለጽሕፈት መሣሪያ 500 ብር (አምስት መቶ ብር) እና ለጽዳት ዕቃ 200(ሁለት መቶ ብር)
  • opening dateበአስራ ስድስተኛው የስራ 4፡30
  • Categories Cleaning & Janitorial , Office Supplies And Services , Stationery Materials

የቴፒ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት የግዥ/ፋ/ን/አስ/ር የስራ ሂደት ለቴፒ ከተማ አስ/ር ሴክተር መ/ቤቶች በ2019 ዓ/ም የጽህፈት መሳሪያ እና የጽዳት ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡


ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

የቴፒ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት የግዥ/ፋ/ን/አስ/ር የስራ ሂደት ለቴፒ ከተማ አስ/ር ሴክተር መ/ቤቶች በ2019 ዓ/ም የጽህፈት መሳሪያ እና የጽዳት ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

በዚሁ መሰረት በጨረታው መሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች የሚከተሱትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል፡፡

  1. ተጫራቾች በዘርፉ የተሰማሩበትን ለ2019 የታደሰ ንግድ ፍቃድ ማቅረብ ይኖርባቸዋል ፡፡
  2. የግብር ከፋይነት ምስከር ወረቀት ኮፒ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  3. ተጫራቾች የቫት (ተጨማሪ እሴት ታክስ) ምዝገባ ምስከር ወረቀት ኮፒ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  4. ተጫራቾች የአቅራቢነት ሰርተፍኬት ኮፒ ማቅረብ አለባቸው፡፡
  5. ተጫራቾች የ2018 ዓ.ም ግብር ስለመከፈላቸው ከገቢዎች የገቢ ከሊራንስ ማቅረብ አለባቸው፡፡
  6. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን ለጽሕፈት መሣሪያ ብር (20,000/ ሃያ ሺህ ብር/ እና ለጽዳት ዕቃዎች 10,000 (አስር ሺህ ብር) ባንከ በተረጋገገጠ በሲፒኦ (CPO) ብቻ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
  7. ተጫራቾች ጨረታውን ሲያሸንፉ ከሚያቀርቡት ጠቅላላ ዋጋ ለጨረታ ውል ማስከበሪያ የሚሆን 109% ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
  8. ዝርዝር የጨረታ ሰነዱን ከቴፒ/ከ/ፋይ/ጽ/ቤት ግዥ/ን አስ/ር የስራ ሂደት 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 42 በመቅረብ ለጽሕፈት መሣሪያ 500 ብር (አምስት መቶ ብር) እና ለጽዳት ዕቃ 200(ሁለት መቶ ብር) በመክፈል መውሰድ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
  9. ተጫራቾች ዝርዝር የጨረታ ሰነዱን 1/አንድ/ ኦርጅናል እና 2/ሁለት ኮፒ) በተለያየ ፖስታ በማሸግ በወቅቱ ለጨረታው በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ጨረታ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ማስገባት ይችላሉ፡፡
  10. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለአስራ አምስት ተከታታይ የሥራ ቀናት ጨረታው በአየር ላይ የሚቆይ ሲሆን ጨረታው በአስራ ስድስተኛው የስራ ቀን ከጧቱ 4፡00 ሰዓት ታሽጎ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት 4፡30 የሚከፈት ይሆናል፡፡ በአስራ ስድስተኛዉ ቀን በዓል ወይም ዝግ ከሆነ በሚቀጥለዉ የስራ ቀን ጨረታዉ የሚከፈት ይሆናል ፡፡
  11. የድርጅቱ ማህተም እና ፊርማ በፖስታው ላይ እና በእያንዳንዱ ጨረታ ሰነድ ላይ ማረፍ አለበት፡፡
  12. ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በሰዓቱ ካልተገኙ የመ/ቤቱ ጨረታ ኮሚቴ ጨረታውን የመከፈት መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  13. ተጫራቾች ጨረታን ሲያሸንፉ ያሸነፉትን የጽህፈት መሳሪያ ፤አላቂ ዕቃዎች እና የጽዳት ዕቃዎችን እስከ ቴፒ ከተማ ፋይናንስ ጽ/ቤት ንብረት ከፍል እስቶር ድረስ በራሳቸው ማቅረብ ግደታ አለባቸው፡፡
  14. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

የቴፒ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት

✨ messages.ai_summary
Tepi City Administration Finance Office seeks bidders to supply stationery and cleaning materials to Tepi city sector offices. Bidders must provide a renewed business license, tax payer and VAT registration certificates, supplier certificate, and tax clearance. Documents available at the office upon payment.
Save Tender