Tender Detail

Tender Details

  • Company በኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ጉሩፕ የኦሞ ኩራዝ ቁጥር 1 እና 3 ስኳር ፋብሪካ
  • Address Addis Ababa, Ethiopia, Phone: +251-963442882
  • Website
  • Deadline24 Sep 2026, 10:00 AM
  • magazineAddis Zemen
  • Bid Document Priceብር 300 (ሶስት መቶ ብር) የማይመለስ
  • opening dateበተመሳሳይ ቀን 14/01/2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡10 ሰዓት
  • Categories Cleaning & Janitorial , Office Supplies And Services , Printing And Publishing

በስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ የኦሞ ኩራዝ ቁጥር 1 እና 3 ጽ/ቤት የተለያዩ ለፋብሪካ አገልግሎት የሚውሉ የጽህፈት መሳሪያዎች፣ የጽዳት እቃዎች እና የህትመት ግዥ በዘርፉ ከተሰማሩ ህጋዊ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡


ብሔራዊ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር: LP/OT/003/OKSF1&3/2019

በስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ የኦሞ ኩራዝ ቁጥር 1 እና 3 ጽ/ቤት የተለያዩ ለፋብሪካ አገልግሎት የሚውሉ የጽህፈት መሳሪያዎች፣ የጽዳት እቃዎች እና የህትመት ግዥ በዘርፉ ከተሰማሩ ህጋዊ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

  1. ተጫራቾች ከሚያቀርቡት ሰነድ ጋር ህጋዊ የታደሰ አዲስ የንግድ ፈቃድ፣ የዘመኑን ግብር መክፈላቸውን የሚያረጋግጥ ከግብር ሰብሳቢው ባለሥልጣን የተሰጠ የምስከር ወረቀት፤ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር እና ለተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስከር ወረቀት፤ በተጨማሪም ተጫራቾች የገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር ወይም በመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር አጀንሲ ባዘጋጀው የዕቃና አገልግሎት አቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ መካተታቸውን መመዝገባቸውን የሚያረጋግጥ ሰነድ መረጃ ማቅረብ አለባቸው፡፡
  2. ተጫራቾች የማይመለስ ብር 300 (ሶስት መቶ ብር) በመክፈል ለዚሁ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ከሚመለከተው አድራሻ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ጨረታው መዝጊያ ቀን ድረስ ዘወትር በሥራ ሰዓት (ከሰኞ እስከ ዓርብ ከሰዓት በፊት ከ2፡30-6፡00፣ ከሰዓት ከ7፡00-10፡30 እና ቅዳሜ ከሰዓት በፊት ከ2፡30-6፡00) ቀጥሎ ከተመለከተው አድራሻ በመቅረብ ገዝተው በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ፡፡
  1. በኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ
  2. የኦሞ ኩራዝ ቁጥር 1 እና 3 ስኳር ፋብሪካ
  3. ገዥ ቡድን (ማስተባበር ቢሮ)
  4. አድራሻ፡- ኮልፈ ቀራኒዮ፣
  5. ከጦር ሃይሎች ወደ ዘነብ ወርቅ በሚወስደው መንገድ
  6. በተስምዶ 3 ቁጥር ማዞሪያ / ቶታል ገባ ብሱ
  7. የፈደራል ቤቶች ኮርፖረሽን ህንፃ ሳደ
  8. ሕ - B ቢሮ ቁጥር 1371/125 ፎቅ፡፡
  9. የስልክ ቁጥር (አድራሻ) +251963442882/+251913544731/251-916170834
  10. አዲስ አበባ
  1. ተጫራቾች ለሚወዳደሩባቸው የፋብሪካ ኬሚካሎች የጨረታ ማስከበሪያ በሲፒኦ ወይም በቅድመ ሁኔታዎች ላይ ያልተመሠረተ የባንክ ጋራንቲ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  2. ተጫራቾች የመጨረቻ ሰነዶቻቸውን በታሸገ ኢንቨሎፕ በማድረግ ጨረታው ከመዘጋቱ በፊት ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ በጨረታው መክፈቻ ላይ መገኘት የሚፈልጉ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው 14/01/2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ በተመሳሳይ ቀን 14/01/2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡10 ሰዓት ላይ ይከፈታል፡፡ ዘግይቶ የሚቀርብ የጫረቻ ሰነድ ውድቅ ይደረጋል፡፡
  3. ጨረታው ዋጋ ፀንቶ የሚቆየው ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ለ30 ቀናት ነው፡፡
  4. የጨረታው ማስረከቢያ ዋስትና ፀንቶ የመቆያ ጊዜ ለ 90 ቀናት ነው፡፡

ፋብሪካው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

በስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ የኦሞ ኩራዝ 1 እና 3 ስኳር ፋብሪካ ጽ/ቤት

✨ messages.ai_summary
Omo Kuraz Sugar Factories No. 1 and 3 invite legal bidders to supply office supplies, cleaning materials, and printing items for factory use. Bidders must submit a valid trade license, tax clearance and VAT registration certificates, and proof of registration on the suppliers list.
Save Tender