ድርጅታችን ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን እና ለስራ የሚጠቀምባቸውን ልዩ ልዩ የህትመት ማሽኖች በጨረታ አወዳድሮ ለማስጠገን ይፈልጋል።
የጨረታ ማስታወቂያ የጨረታ ቁጥር 024/18
ድርጅታችን ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን እና ለስራ የሚጠቀምባቸውን ልዩ ልዩ የህትመት ማሽኖች በጨረታ አወዳድሮ ለማስጠገን ይፈልጋል። በመሆኑም ጥገናውን ማድረግ የምትፈልጉ ድርጅቶች ማሽኑን በአካል በማየት (lnspection) ለጥገናው የሚያስፈልግ መለዋወጫና የሚወስደውን ጊዜ በግልፅ በማስቀመጥ መወዳደር የምትችሉ ሲሆን በተጨማሪም ወቅታዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የገንዘብ ሚኒስቴር የዕቃ አቅራቢዎች ምዝገባ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ የምስክር ወረቀት፣ የግብር ከፋይ ምስክር ወረቀት እና በጨረታ መሳተፍ የሚያስችል የታክስ ክሊራንስ ያላቸው ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በድርጅቱ ዋና መ/ቤት (አራት ኪሎ) አዲሱ ህንፃ 5ኛ ፎቅ በሚገኘው የዕለት ገንዘብ ተቀባይ ቢሮ ብር 500.00 ከፍለው በመግዛት የፋይናንሺያል እና የቴክኒካል የመጫረቻ ሰነዶቻቸውን ዋናውን እና ኮፒ በተለያየ ፖስታ በማድረግ በብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት 6ኛ ፎቅ ነባሩ ህንፃ በግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ።
ተጫራቾች በጨረታ ማስከበሪያ ብር 30,000 በባንክ ክፍያ ማዘዣ (ሲፒኦ) ማስያዝ አለባቸው። ጨረታው 26/1/ቀን 2019 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰአት ተዘግቶ በዕለቱ የቴክኒካል መጫረቻ ሰነድ (ከላይ የተገለፁ ለቅድመ ግምገማ የሚያገለግሉ ዶክመንቶች እና የጨረታ ማስከበሪያ) ብቻ ከሰዓት 8፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት ነባሩ ህንፃ 6ኛ ፎቅ በሚገኘው በግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ይከፈታል፡፡ የፋይናንሺያል የመጫረቻ ሰነዶች የሚከፈቱት ቴክኒካል ተቀባይነት ላገኙት ብቻ ነው። ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ በጨረታው አይገደድም።
| ተ.ቁ | የማሽኑ አይነት | ብዛት |
| 1 | Sakurai 266-2 | 1 |
| 2 | Sakurai 266-1 | 1 |
| 3 | Sakurai 480 | 1 |
| 4 | Solna D302 | 1 |
| 5 | Solna D-25 | 1 |
ስልክ ቁጥር 011-1-55-52-30
ድረ ገፅ ( www.ethbspe.org )
Berhanena selam printing enterprise
አዲስ አበባ
ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት
