የድሬዳዋ አስተዳደር ውሃና ፍሣሽ ባለሥልጣን ለ2019 በጀት ዓመት የተለያዩ የተሸከርካሪ መለዋወጫ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
በድጋሚ የወጣ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የድሬዳዋ አስተዳደር ውሃና ፍሣሽ ባለሥልጣን ለ2019 በጀት ዓመት የተለያዩ የተሸከርካሪ መለዋወጫ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለዚህ ቀጥሎ የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተወዳዳሪዎች በጨረታው እንዲሳተፉ ይጋብዛል፡፡
- ማንኛውም ተጫራች በዘርፉ በዕቃና አገልግሎት አቅራቢነት በፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር መመዝገቡን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት፣ በዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድና የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ የምስክር ወረቀት መወዳደሪያ ኤንቨሎፕ ውስጥ ኦርጂናልና አንድ ኮፒ በማድረግ እስከ ጨረታው መዝጊያ ቀን ድረስ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
- የጨረታው ዶክመንት የማይመለስ ብር 500 /አምስት መቶ ብር/ በመክፈል ድሬዳዋ አስተዳደር ውሃና ፍሣሽ ባለሥልጣን ከግዥ ፋይናንስና ደጋፊ የሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 10 በጥሬ ገንዘብ በመከፈል ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት እለት ጀምሮ በ15 ቀናት ውስጥ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
- የጨረታ ሰነድ በውሃና ፍሣሽ ባለሥልጣን ቢሮ ቁጥር 10 ከ1፡30 እስከ 11፡30 ዘወትር በሥራ ሰዓትና ቀን መግዛትና ማስገባት ይቻላል፡፡
- ጨረታው በማስታወቂያ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15ኛው ቀን በ3፡30 የጨረታ ሳጥኑ ተዘግቶ በተመሣሣይ ቀን 4፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች ብር 60,000.00 /ስልሳ ሺህ ብር/ የጨረታ ማስከበሪያ በተረጋገጠ የባንክ ዋስትና CPO ወይም በጥሬ ገንዘብ ዶክመንቱ ሲከፈት ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- የጨረታው ዶክመንት በታሸገ ፖስታ የእያንዳንዱ ዋጋና ጠቅላላ ዋጋ በግልጽ ማስቀመጥ አለበት፡፡ በተጨማሪ በጨረታ ዶክመንቱ ውስጥ የተዘጋጁት ፎርማት ተሞልተውና ተፈርመው በሁለት ኮፒ መቅረብ አለባቸው፡፡
- ያሸነፈው ተጫራች የተጠየቀውን እቃ የግዥ ትዕዛዝ እንደተሰጠው በእስፔስፊኬሽኑ እና በናሙናው መሠረት በ30 ቀናት ውስጥ በድሬዳዋ አስተዳደር ውሃና ፍሣሽ ባለሥልጣን በሚገኝበት መጋዘን አቅርቦ ማስረከብ አለበት፡፡
- በዶክመንቱ ከተሰጠው ስፔስፊኬሽን ወይም ሳምፕል ውጪ የሚቀርብ ተቀባይነት የለውም፡፡
- የጨረታው አሸናፊ ካሸነፈው ዋጋ 10% ውል ማስከበሪያ በተረጋገጠ የባንክ ዋስትና CPO ወይም በሁኔታ ያልተገደበ የባንክ ጋራንቲ ማስያዝ መስጠት የሚችል መሆን አለበት፡፡
- በጨረታው ሂደት ጨረታውን ለማዛባት ለማጭበርበር የሞከረ ተጫራች ከጨረታው ውጭ እንደሚሆንና በመንግሥት ግዢ እንዳይሳተፍ ይደረጋል፡፡
- ጨረታ ሳጥኑ ከተዘጋ በኋላ የሚመጣ የጨረታ ዶክመንት ተቀባይነት የለውም፡፡
- ባለስልጣን መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻ፡- ድሬዳዋ አስተዳደር ውሃና ፍሣሽ ባለሥልጣን ቀበሌ 03 ስልክ ቁጥር 025112 48 92 ፖ.ሳ.ቁ 44
የድሬዳዋ አስተዳደር ውሃና ፍሣሽ ባለሥልጣን
✨ messages.ai_summary
Dire Dawa Water and Sewerage Authority seeks to buy various vehicle spare parts through open tender. Bidders must be registered with the Ministry of Finance and Economic Development as goods and service suppliers, hold a renewed business license and VAT registration certificate, and submit these in the bid envelope.
