Tender Detail

Tender Details

  • Company በኢትዮጵያ ንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽን የትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ አገልግሎት ዘርፍ
  • Address ቃሊቲ ቆርኪ ፋብሪካ ፊት ለፊት ፡ አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 011 4552358
  • Website
  • Deadline15 Sep 2026, 10:30 AM
  • magazineAddis Zemen
  • Bid Document Priceብር 500 ብር አምስት መቶ
  • Bid Security50,000.00 /ሃምሳ ሺህ ብር/ የጨረታ ማስከበሪያ በሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና
  • opening dateበዚሁ ዕለት ከጠዋቱ 4:30 ሠዓት
  • Categories

በኢትዮጵያ የንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽን የትራንስፖርትና ሎጀስቲከስ አገልግሎት ዘርፍ ዘርፋችን ቃሊቲ በሚገኘው ግቢ ውስጥ ያሉትን ያገለገሉ ብረታ ብረቶች፣ ንቃይ ቆርቆሮች፣ ቁርጥራጭ የተሽከርካሪና ሌሎች ብረታ ብረቶችና የተለያዩ መጠን ያላቸው የመኪና ባትሪዎች በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡

በኢትዮጵያ ንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽን የትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ አገልግሎት ዘርፍ


የጨረታ ማስታወቂያ

በኢትዮጵያ የንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽን የትራንስፖርትና ሎጀስቲከስ እገልግሎት ዘርፍ ዘርፋችን ሳሪስ በሚገኘው ግቢ ውስጥ ያሉትን ያገለገሉ ብረታ ብረቶች፣ንቃይ ቆርቆሮች፡ቁርጥራጭየተሽከርካሪና ሌሎች ብረታ ብረቶችና የተለያዩ መጠን ያላቸው የመኪና ባትሪዎች በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም በጨረታ ላይ መወዳደር የሚፈልጉ ድርጅቶች ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መመዘኛዎች ማሟላት አለባቸው፡፡

1.     ስለአሻሻጡ የተዘጋጀውንና የጨረታ ሠነድ የማይመለስ ብር 500 ብር አምስት መቶ/ በመክፈል ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ መስከረም 4 ቀን 2019 ዓ.ም ዘወትር ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው ቃሊቲ በሚገኘው ዋናው መ/ቤት /አዲስ አበባ/ ከሰኞ እስከ አርብ ከጠዋቱ 3፡00-6፡30 እንዲሁም ከሰዓት 7፡30-11፡30 እና ቅዳሜ ከ3፡00 እስከ 6፡30 ሠዓት መግዛት ይችላሉ፡፡

2.     ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን እስከ ጨረታው መዝጊያ ዕለት እስከ መስከረም 4 ቀን 2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡30 ሠዓት ድረስ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸዉ::

3.     ተጫራቾች ለሚጫረቱበት ንብረት 50,000.00 /ሃምሳ ሺህ ብር/ የጨረታ ማስከበሪያ በሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንከ ዋስትና በዘርፋችን ስም አሰርተው ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር ማቅረብ አለባቸው፡፡

4.     ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ ሲሞሉ በግልፅ 15 % የተጨማሪ እሴት ታከስ VAT ማሳየት አለባቸው፡፡

5.     ጨረታው መስከረም 5 ቀን 2019 ዓ.ም. ከጠዋቱ 4፡30 ተዘግቶ በዚሁ ዕለት ከጠዋቱ 4:30 ሠዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዋና መ/ቤት የመሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል፡፡

6.     የጨረታው አሸናፊ ተጫራች በጨረታው ያሸነፉትን ንብረት ሙሉ ከፍያ በ5 /አምስት የስራ ቀናት ውስጥ በመከፈል ማንሳት ይኖርባቸዋል፡፡ በተጠቀሰው የጊዜ ገደብ ውስጥ ካላነሱ ከ5ኛው ቀን በኋላ ላላነሱበት ቀን በየቀኑ ብር 100.00 /አንድ መቶ ብር/ ቅጣት የሚከፍሉ ይሆናል፡፡

7.     አሸናፊው በራሱ ወጪ የተለያዩ ብረታ ብረቶች ንቃይ ቆርቆሮች፣ቁርጥራጭ የተሽከርካሪና ሌሎች ብረታ ብረቶች የተለያዩ መጠን ያላቸው የመኪና ባትሪዎች፣ማንሳት ማስጫንና ማጓጓዝ ይኖርበታል፡፡

8.    ዘርፉ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ይሁን በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለማንኛውም ማብራሪያ በአካል በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር 095384581 መጠየቅ ይቻላል፡፡

አድራሻ ፡ ቃሊቲ ቆርኪና ጣሳ ፋብሪካ ፊት ለፊት

ስልክ ቁጥር: 0953845811

የኢትዮጵያ ንግድ ስራዎች ኮርፖረሽን የትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ አገልግሎት ዘርፍ

Save Tender