የጆሽዋ ቁጠባና ብድር ኃ/የተ/መ/የኃ/ሥ/ማ ለ25 ዓመታት በቁጠባና ብድር ህብረት ስራ ማህበር በመስራት ላይ ያለ ማህበር (SACCO) ሲሆን፤ ማህበራችን የ2018 በጀት አመት የነ(አንድ) ዓመት ኦዲት ለማስደረግ የውጭ ሂሳብ ኦዲት አድራጊ ድርጅቶችን አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡
ጆሽዋ ቁጠባና ብድር ኃ/የተ/መ/የኅ/ሥ/ማህበር
የውጭ ሂሳብ ኦዲት የጨረታ ማስታወቂያ
የጆሽዋ ቁጠባና ብድር ኃ/የተ/መ/የኃ/ሥ/ማ ለ25 ዓመታት በቁጠባና ብድር ህብረት ስራ ማህበር በመስራት ላይ ያለ ማህበር (SACCO) ሲሆን፤ማህበራችን የ2018 በጀት አመት የነ(አንድ)ዓመት ኦዲት ለማስደረግ የውጭሂሳብ ኦዲት አድራጊ ድርጅቶችን አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም ከዚህ በታች ያሉትን መስፈርቶች የምታማሉ ድርጅቶች በጨረታው ለመሳተፍ የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
* የ 2018 ዓ.ም የታደሰ የንግድ ፍቃድ ማቅረብ የሚችሉ፤
* የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ ሰርተፍኬት (VAT) ያላቸው፤
* የግብር ከፋይ ምዝገባና ሰርተፍኬት መለያ ቁጥር (TIN) ሰነድ ያላቸው፤
* በጨረታ መሳተፍ የሚያስችል የታከስ ከሊራንስ ማቅረብ የሚችል
* ከኢትዮጵያ ሂሳብ አያያዝና ኦዲት ቦርድ የሙያ ብቃት ማረጋገጫ የምስክርወረቀት ያገኘ
* ወዳዳሪዎች የቁጠባ እና ብድር ህብረት ስራ ማህበር (SACO) ተመሳሳይዘርፍ የሂሳብ ምርመራ ልምድ እና በቂ ባለሙያ ያላቸው መሆን + ይጠበቅባቸዋል፤
* ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ)በመከፈል አዲስ አበባ ዋናው ቢሮ ማግኘት ይችላሉ፤
* አንድ ተጫራች ባቀረበው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ ተቀባይነት + የለውም፤
የዋጋ ማስገቢያ ሰነዱ ላይ ስርዝ ድልዝ እንዲሁም ከፍት ካለው ሰነዱ ተቀባይነት አይኖረውም፤
*ተጫራቾች ስለጨረታው ሙሉ ዝርዝር ሁኔታ የያዘውን የጨረታ ሰነድ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 10(አስር) የስራ ቀናት ጊዜ ውስጥ ከድርጅታችን የሰው ሀብት እና አስተዳደር ከፍል በአካል በመቅረብ የጨረታ ሰነዱን መግዛት የሚቻል ሲሆን የጨረታ ማወዳደሪያ ሰነድ ኦርጅናልና ፎቶ ኮፒ የፋይናንስ ለብቻ የቴክኒክ ለብቻ በማያያዝ በታሸገ ኤንቨሎፕ ለዚሁ ሲባል በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት የሚችሉ ሲሆን፤ ጨረታው ተጫራቾች/ ተወካዮች ባሉበት አስረኛው ቀን ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ተዘግቶ በእለቱ 9፡00 ሰዓት ላይ መሰብሰቢያ ክፍል ይከፈታል፡፡ ጨረታው የሚከፈትበት የስራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል።
የጨረታ ሰነዱ ላይ የተዘረዘሩትን መረጃዎች ሙሉ ለሙሉ መሙላት ይጠበቅባችኋል፤
የጨረታ አሸናፊው ጨረታውን አሸንፎ ከተዋዋለ በኋላ ለሌላ ሶስተኛ ወገን ማስተላለፍ አይፈቀድም፤
ማህበሩ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው፡፡
ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ አዲስ አበባ ደንበል ፊትለፊት በሚገኘው ዋናው ቢሮ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር0115582023 / 0115584416 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡
ጆሽዋ ቁጠባና ብድር ኃ/የተ/መ/የኅ/ሥ/ማህበር
