በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የህብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን በግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ በሎት የተጠቀሱትን ዕቃዎችንና አገልግሎቶችን ተጫራቾችን በማወዳደር መግዛት ይፈልጋል፡፡
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የህብረተሰብ ተሳትፎና በጎፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን
የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
ቁጥር ህ/ተ/በጎ/ፈ/ማ/ኮ ከ01/2019
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የህብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን በግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ በሎት የተጠቀሱትን ዕቃዎችንና አገልግሎቶችን ተጫራቾችን በማወዳደር መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም
የጨረታ አይነት በሎት
የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ
| ሎት 1 | የህትመት አገልግሎት------------------ | 40,000.00 ብር |
| ሎት 2 | የኩነትና የመድረክ አገልግሎት------------ | 40,000.00 ብር |
| ሎት 3 | የአላቂ፣ የዕዳት ዕቃዎች፣ የደንብ ልብስ-------------------- | 25,000.00 ብር |
| ሎት 4 | የኤሌክትሪክ የሚኒባስ ተሽከርካሪ ኪራይ--------------------- | 50,000.00 ብር |
| ሎት 5 | የጋራዥ አገልግሎት ግዥ---------------------- | 50,000.00 ብር |
| ሎት 6 | የክህሎትና የባህሪ ማይንድ ሴት/ ስልጠና አገልግሎት ግዥ----------------- | 15,000.00 ብር |
| ሎት 7 | ቋሚ ዕቃዎች ግዥ ------------------------- | 50,000.00 ብር |
| ሎት 8 | የሚዲያ አገልግሎት ግዥ------------------------- | 30,000.00 ብር |
- ተጫራቾች በጨረታ መሳተፍ የሚችሉት በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፈቃድ፡ ንግድ ምዝገባ፣ ግብር ከፋይ ሰርተፊኬት፡ የተጨማሪ እሴት ታክስ ሰርተፊኬት እና የአቅራቢነት ተመዝጋቢ መረጃ ማቅረብ የሚችል፡ እንዲሁም ሌሎች እንደ አስፈላጊነቱ ለጨረታ ግምገማ የሚውሉ መረጃዎች በማቅረብ በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች ዝርዝር መረጃ የያዘውን የጨረታ ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 10/አስር የስራ ቀናት ውስጥ በግዥ ንብረትና ጠቅላላ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት የተዘጋጀውን ብሔራዊ ግልጽ ጨረታ ሰነድ በማይመለስ የእንዱን ሰነድ በ400/ አራት መቶ ብር/ ከፋይናንስ ዳይሬክቶሬት በአካል በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ 10 /አስር/ የስራ ቀናት ማለትም ከሰኞ እስከ አርብ ከጠዋቱ 2፡30 ሰዓት እስከ ማታ 1፡30 ሰዓት ድረስ በታሸገ ኢንቨሎፕ በማድረግ የቴክኒካልና የፋይናንሻል ሰነዶቻቸውን ኦርጅናልና ኮፒ በማድረግ በአንድ ፖስታ ከተጓዳኝ ማስረጃዎች ጋር ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ከጨረታው መዝጊያ ሰዓት አስቀድሞ በ11ኛው ቀን እስከ 4፡00 ሰዓት ድረስ በማስገባት የሚታሸግ ሲሆን ጨረታው በዚሁ ዕለት 4፡30 ሰዓት ላይ ይከፈታል፡፡ ሆኖም ማግስቱ የበዓል ቀን ከሆነ ቀጥሎ ባለው ቀን በተጠቀሰው ቦታና ሰዓት ተጫራቾቹ ወይም ህጋዊ ወኪሎች በተገኙበት ጨረታው ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን ሲመልሱ ናሙና ለተጠየቀባቸው ማምጣት ማቅረብ ግዴታ አለባቸው፡፡ እንዲሁም ናሙና ማቅረብ ለማይቻልባቸው ዕቃዎች ገላጭ ፎቶ ተያይዞ እንዲቀርብ እያሳወቅን ተጫራቹ የመጫረቻ ሰነዳችሁን ስትመልሱ ተቋማችን ባዘጋጀው የጨረታ ሰነድና በጨረታው በተቀመጠው ዝርዝር መግለጫ መሠረት ብቻ ማቅረብ ይኖርባችኋል፡፡ ከዚህ ውጪ በራሱ ሰነድ የሚያቀርብ ተጫራች ከውድድር ውጪ ይደረጋል፡፡
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት የመሸጫ ዋጋ ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ለ45 ቀናት የፀና ይሆናል፡፡
- ተቋማችን የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ ለሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ተጫራቹ ለጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ ሲያሰራ ዋጋ ፀንቶ ከሚቆይበት 45 ቀናት በተጨማሪ የከ5 ቀናት ተጨምሮበት ተሰርቶ መቅረብ አለበት፡፡ በድምሩ የ60 ቀናት
- አድራሻ:- ፒያሳ እሪበከንቱ ቢቲ ታወር 3ኛ ፎቅ ይገኛል፡፡
- ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር:- +251124738
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የህብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን
