Tender Detail

Tender Details

  • Company በቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 01 ፋይናንስ ጽ/ቤት
  • Address ቦሌ ሚካኤል ከጉምሩክ ወረድ ብሎ ኮንደሚኒየም ጀርባ : አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0118 16 02 11
  • Website
  • Deadline28 Aug 2026, 5:00 AM
  • magazineAddis Zemen
  • Bid Document Priceየማይመለስ የኢትዮጵያ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) ለአንድ ጨረታ ሰነድ
  • Bid Securityበእያንዳንዱ ሎት 1) 30,000 ብር ሎት 2) 30,000 ብር ሎት 3) 30,000 ሎት 4) 2,000 ሎት 5) 2,000 ሎት 6) 2,000 ሎት 7) 20,000 ሎት 8) 2,000 ከላይ የተቀመጠው የማስከበሪያ ብር C.P.O ብቻ
  • opening dateበ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት
  • Categories Office Supplies And Services , Printing And Publishing , Ict Equipment'S And Its Accessories

በቦሌ ከ/ከተማ ወረዳ 01 ፋይናንስ ጽ/ቤት በወረዳው ስር ለሚገኙ ጽ/ቤቶች በ 2019 በጀት ዓመት በ 1ኛ ዙር ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል ፡፡

በቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 01 ፋይናንስ ጽ/ቤት


ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

በጨረታ ቁጥር 01/2019 ዓ.ም

በቦሌ ከ/ከተማ ወረዳ 01 ፋይናንስ ጽ/ቤት በወረዳው ስር ለሚገኙ ጽ/ቤቶች በ 2019 በጀት ዓመት በ 1ኛ ዙር ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል ፡፡ ስለሆነም የሚመለከታቸው ድርጅቶች ከዚህ በታች በተዘረዘረው መሰረት መስፈርቱን የምታሟሉ ተጫራቶች መሳተፍ የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን ፡፡

  • ሎት 1 የጽሕፈት መሳሪያዎች
  • ሎት 2 የዕዳት ዕቃዎች
  • ሎት 3 የደንብ ልብስ
  • ሎት 4 የህትመት ስራዎች
  • ሎት 5 የኮምፒውተር ጥገና አገልግሎት
  • ሎት 6 የመስተንግዶ አገልግሎት
  • ሎት 7 ቋሚ ዕቃ
  • ሎት 8 የትራንስፖርት አገልግሎት
  • ሎት 9 የድንኳን ኪራይ
  • ሎት 10 የጭነት አገልግሎት

ከላይ የተገለጹትን እቃዎች መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ መስፈርቱን የሚያሟሉ ተጫራቶች ቀርበው ሰነድ ገዝተው መወዳደር ይችላሉ፡፡

  • ህጋዊ ደረሰኝ ማቅረብ የሚችል የዘመኑ ግብር የገበረ የታደሰ ንግድ ፈቃድ እና ምዝገባ ፍቃድ ማቅረብ የሚችል፡፡
  • የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ እና በአቅራቢዎች ዝርዝር ላይ የተመዘገቡ የተጫራቾች የምስክር ወረቀት ያላቸው ተጫራቾች እያንዳንዱ የሚወዳደሩበት ጨረታው የእቃውን ዝርዝር ሰነዱን ላይ ያለውን ብቻ መሰረት ማድረግ ይኖርባችዋል ፡፡
  • የጨረታ ማስከበሪያ በእያንዳንዱ ሎት 1) 30,000 ብር ሎት 2) 30,000 ብር ሎት 3) 30,000 ሎት 4) 2,000 ሎት 5) 2,000 ሎት 6) 2,000 ሎት 7) 20,000 ሎት 8) 2,000 ከላይ የተቀመጠው የማስከበሪያ ብር C.P.O ብቻ ማቅረብ አለባቸው፡፡
  • ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ ሲያስገቡ የሚጫረቱባቸውን የእቃዎች በሙሉ ሳምፕል (ናሙና) ማቅረብ አለባቸው፡፡
  • የጨረታ ማስከበሪያ የማይመለስ የኢትዮጵያ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) ለአንድ ጨረታ ሰነድ በመከፈል በቦሌ ከ/ከተማ ወረዳ 1 ፋይናንስ/ጽ/ቤት 2ኛ ፎቅ ቢሮ መውሰድ ይችላል፡፡
  • የጨረታ አሸናፊዎች ያሸነፉበት እቃዎችን በራሳቸው ትራንስፖርት ማቅረብ አለባቸው፡፡
  • መስሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  • በጨረታው ሰነድ ውስጥ መ/ቤቱ ከጠቀሳቸው የእቃዎች ዝርዝር ውጪ ያስገቡ ተጫራቾች ከጨረታው ውጭ ይሆናሉ፡፡
  • የጨረታ አሸናፊዎች ያሸነፉበት ጠቅላላ ዋጋ 10% የውል ማስከበሪያ ዋስትና ማስያዝ አለባቸው ዋጋው ጸንቶ የሚቆይበት አሸናፊው ከተለየበት አንስቶ ለ60 ቀናት ይሆናል፡፡
  • ተጫራቾች የጨረታው ፖስታ ላይ የድርጅቱ ማህተም ማድረግ አለባቸው፡፡ ለእያንዳንዱ ለተወዳደሩበት በየሎቱ CPO ማስያዝ አለባችሁ ጥቅል CPO ካስገቡ ከጨረታ ውጭ ይሆናሉ፡፡
  • በጥቃቅን የተደራጁ ከሆነ በሚያመርቱት ምርት ከሆነ ጨረታ ሰነድ በነጻ የሚወስዱ ይሆናል በማያመርቱ ምርት ላይ ሰነድ የሚገዙ ይሆናል፡፡
  • በጨረታ ሂደት ላይ ለማሳሳትና የማጭበርበር ስራ ላይ የሚሳተፉ ተጫራቾች ህጉ በሚያዘው በኢትዮጵያ ህግ የሚዳኝ ይሆናል፡፡
  • ለቋሚ እቃዎች ናሙና ለማይቀርብላቸው የእቃዎቹ እስፔፊኬሽን ከኦርጅናል ሰነዱ ጋር ማያያዝ አለባቸው፡፡
  • ተጫራቾች የጨረታ ፖስታው ኮፒ ና ኦርጅናል በማሸግ ማስገባት አለባቸው፡፡ C.P.O ውን ኦርጅናሉን ሰነድ ላይ ማያያዝ አለበት ኮፒ ላይ ከተደረገ ከጨረታው ላይ ተሳታፊ አይሆኑም ተጫራቾች የሚያስገቡት ዋጋ ቫትን የጨመረ መሆን አለበት ፡፡
  • ማንኛውም ተጫራች በጨረታው አፈጻጸም ሂደት ላይ ቅሬታ ቢኖረው በ 5 የስራ ቀናቶች ውስጥ ቅሬታ ማስገባት ይችላሉ፡፡ በ 6ኛው ቀን ቅሬታ ማቅረብ አይችሉም፡፡
  • ለጨረታ የቀረቡትን የእቃ ናሙናዎች ውጤት በተገለጸ በ 10 ቀናት ውስጥ እቃዎችን መውሰድ አለባችሁ ይህ ባይሆን እቃዎቹ ለመስሪያ ቤቱ ገቢ ይሆናል ፡፡
  • ጨረታውም አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ 10 የስራ ቀናቶች የሚቆይ ይሆናል 10ኛ ቀን ላይ 11፡00 ሰዓት ላይ የሚዘጋ ይሆናል በ11ኛው ቀን ሰነድ ማስገባት አይቻልም በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ሲሆን ቀኑ በዓል ከሆነ በሚቀጥለው ቀን ተጫራቾች ወይም ወኪሎች ቢኖሩም ባይኖሩም የሚከፈት ይሆናል ፡፡

አድራሻ ቦሌ ሚካኤል ከጉምሩክ ወረድ ብሎ ኮንደምንም ጀርባ ቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 1 አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት

ለበሰጠ መረጃ ስልክ ቁጥር፡- 0118160211

በቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 01 ፋይናንስ ጽ/ቤት

✨ messages.ai_summary
Open tender for procurement of office supplies, printing, ICT equipment, and services across 10 lots, including stationery, uniforms, computer maintenance, catering, transport, tent rental, and freight. Bidders must meet legal, tax, and registration requirements.
Save Tender