የተለያዩ ግብዓት ግዥ በሎት ተከፋፍሎ
አቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ የወረዳ 2 አስተዳደር ጽ/ቤት
1ኛ ዙር ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 02 አስተዳደር ጽ/ቤት በ2019 በጀት ዓመት ለወረዳው የሚያስፈልገውን የተለያዩ ግብዓት በሎት አከፋፍለው፣
- ሎት 1 - ደንልብስ ግዥ፣
- ሎት2፡- የጽሕፈት መሣሪያ ግዥ፣
- ሎት3፡- የሕትመት ሥራዎች
- ሎት4፡- የፅዳት ዕቃዎች ግዥ፣
- ሎት5፡- ሌሎች አላቂ ዕቃዎች፤
- ሎት6፡- የግብርና ምርት ማሳደጊያና ዘር ግዥ
- ሎት7- የተለያዩ ንቅናቄ የትራንስፖርት አገልግሎት
- ሎት8፡- የተሸከርካር ወንበር ልብስ፤ የጎማና ሌሎች ግዥን በጨረታ ቁጥር፡-01/2019 የ2019 በጀት ዓመት በስሩ ለሚገኙት የተለያዩ ጽ/ቤቶች መገልገያ የሚሆኑ ዕቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳደድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ በዚህ ሥራ ላይ የተሰማራችሁ አቅራቢዎች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርት የምታሟሉት ቀርባችሁ መወዳደር እንደምትችሉ እናሳውቃለን።
የጨረታዉ መስፈርት -
- በዘርፉ ሕጋዊ ንግድ ፈቃድና የንግድ ምዝገባ ምስከር ወረቀት ያለው፤
- የዘመኑን የመንግሥት ግብር የከፈለና ከሊራንስ ያለው እና የዘመኑን ንግድ ፍቃዱን ያሳደሰ፤
- VAT ተመዝጋቢ የሆነ እና ሕጋዊ ደረሰኝ ያለው
- በመንግሥት ግዥ በአቅራቢነት የተመዘገበበትን መረጃ ማቅረብ የሚችል፤
- በሥራ ክህሎት የተደራጁት ኢንተርፕራይዝ በሀገር ውስጥ ምርቶች ላይ ብቻ ልዩ ድጋፍ የሚደረግላቸው ሲሆን፤ ይህም የሚደረገው ከአደራጃቸው ጽ/ቤት ኃላፊ በተፈረመ የድጋፍ ዳብዳቤ ይሆናል፡፡ ከሥራ ዘርፉ እና ከሀገር ውስጥ ምርቶች ውጪ ለሆኑት እንደማንኛውም ነጋዴ የሚስተናገዱ ይሆናል፡፡
- የጨረታውን ሰነድ ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ አቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ ቆርቆሮ ፋብሪካ አካባቢ ወረዳ 2 አስተዳደር ሕንጻ ፋይናንስ ጽ/ቤት 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 203 በመገኘት ከጠዋቱ 2፡30 እሰከ ከሰአት 11፡30 በብር 300.00 /ሶስት መቶ ብር/ በካሽ በመግዛት መጫረት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በባንከ በተረጋገጠ ሲፒኦ/CPO/ የሚጫረቱበትን ለእያንዳንዱ
| 1. ሎት 1 -- የጨረታ ማስከበሪያ:- 62100 |
| 2. ሎት 2 የጨረታ ማስከበሪያ:- 20,000 |
| 3. ሎት 3 የጨረታ ማስከበሪያ:- 7000 |
| 4. ሎት 4 -የጨረታ ማስከበሪያ- 60,000 |
| 5. ሎት 5 የጨረታ ማስከበሪያ:- 26000 |
| 6. ሎት 6 -የጨረታ ማስከበሪያ:- 5000 |
| 7. ሎት 7 የጨረታ ማስከበሪያ፡- 21000 |
| 8. ሎት 8 የጨረታ ማስከበሪያ 3000 |
በኢትዮጵያ ብር ማስያዝ ይኖርባቸዋል የጨረታው ማስከበሪያ በየሎት በተጠየቀው መሰረት በሲፒኦ (CPO) ዋስትና በወረዳ 02 አስተዳደር ጽ/ቤት በሚል በማሠራት በዋናው ሰነድ ውስጥ ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የጨረታ ማስከበሪያ ያላስያዘ በጨረታው ሰነድ በቅድመ ምርመራ ውድቅ ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት የመወዳደሪያ ሃሳብ ላይ በግልጽ የሚታይ እና የሚነበብ የዕቃውን ዓይነት ስም፣ የተመረተበት ሀገር፣ የሞዴሉን ቁጥር ፤ የተመረተበትን ጊዜ ያካተተ መሆን ይገባዋል፡፡
- ግዥ ፈጻሚው አካል አሸናፊ ተጫራቾች በሚያቀርቡት እቃ ወይም አገልግሎት ላይእንዳስፈላጊነቱ 20% መቀነስ ወይም መጨመር ይቻላል፡፡
- ተጫራቾች የሚያቀርቡትን ዕቃ እስከ መ/ቤቱ ግምጃ ቤት ንብረት ከፍል ድረስ የመጓጓዣ አካተው ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- የጨረታው ሰነድ በሁለት ፖስታ የሚቀርብ ሆኖ ዋና እና ፎቶ ኮፒ የጨረታው ሰነድ መቅረብ አለባቸው እነዚህም ሰነዶች በጨረታው ሲቀርቡ ድርጅቶቹ ወይም ሕጋዊ ውከልና ባለው አካል መፈረም አለባቸው፤ በሰነዶቹ እና ፖስታዎቹ ላይ የድርጅቱ አቅራቢው ማህተም መኖር ይገባል፤ ሰነዱ በሚሞላበት ወቅት ስርዝ ድልዝ (ለማንበብ አስቸጋሪ) ከሆነ ከውድድር ውጪ ያስደርጋል፡፡
- ጨረታውን ለመገምገም በሥራ ላይ የሚውሉትን ዘዴዎች ለዚሁ ግምገማ የሚያገለግሉትን መስፈርቶች እና እያንዳንዱ መስፈርት የሚኖረውን ድርሻ እንዲሁም ሁለት እና ከሁለት በላይ የሆኑ ዕጩ ተወዳዳሪዎች በግምግማ እኩል በሆነ ጊዜ አሸናፊን ለመለየት በግዥ መመረያው መሰረት የሚለይ ይሆናል፡፡
- ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ተጫራቶች ባቀረቡት የመወዳደሪያ ሀሳብ ላይ ለውጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግ እንዲሁም ከጨረታው እራሳቸውን ማግለል የተከለከለ ነው፡፡
- የጨረታውን አካሄድ ለማዛባት የሚሞከር ማንኛውም ተጫራች ከጨረታው ውጪ እንደሚሆን፤ ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ /ሲፒኦ/ እንደሚወረስ እና ለወደፊቱም በመንግሥት ግዥ ጨረታ እንደማይሳተፉ ለሚመለከተው አካል ሪፖርት እንደሚደረግ ማወቅ ይኖርበታል፤
- የውል ማስከበሪያ የጠቅላላ ግዥውን 10% በብር/ሕጋዊ CPO/ በወረዳ 02 አስተዳደር ጽ/ቤት /woreda 02 administration office/በሚል በማሠራት ማስያዝ የሚችል፡፡
- ጨረታው በአስራ አንደኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ላይ ተጫራቹ ሕጋዊ ወኪል በተገኘበት ተዘግቶ በ4፡30 በአቃ/ቃ/ከ/ከ/ወ 02 ህዳሴ አዳራሽ የሚከፈት ሲሆን ተጫራቹ/ሕጋዊ ወኪሉ/ ያለመገኘት የጨረታ አከፋፈት ላይ ተጽዕኖ እያመጣም፡፡ ሆኖም ግን ከኛው ቀን የሥራ ቀን ላይ ካልዋለ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይከፈታል፡፡
- ውድድሩን ያሸነፈ ተወዳዳሪ ውድድሩን ማሸነፉ ከታወቀ ቀን እና የቅሬታ እና አቤቱታ 7 ቀን ከአለቀ በኋላ በ15 (አስራ አምስት) ቀን ውስጥ በአካል ቀርቦ የውል ስምምነት መፈረም አለበት ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታው ሰነድ ላይ የማብራሪያ ወይም የማሻሻያ ጥያቄ ካለቸው የጨረታ ሰነዱ የመክፈቻ ቀን ከሶስት የሥራ ቀናት በፈት በጽሑፍ ማቅረብ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታው አፈፃፀም ሂደት ላይ ቅሬታ ካላቸው ለጽ/ቤት ኃላፊ በጽሑፍ ማቅረብ ይችላሉ፡፡
- ከፍያን በተመለከተ አቅራቢው ዕቃውን ሙሉ በሙሉ በጥራት እና በናሙና መሰረት ማቅረቡ በቴከኒክ ኮሚቴ ተረጋግጦ ወደ ንብረት ከፍል ገቢ ሲሆን የሚከፈል ይሆናል፤
- ለደንብ ልብስ፣ ለጽሕፈት መሣሪያ የሕትመት ሥራዎች ለፅዳት እቃ፤ ለሌሎች አላቂ እቃ እና ለተሸካሪካሪ ጎማ፤ የወንበር ልብስና ሌሎች ተወዳዳሪዎች ምንም አይነት ምልከት ያልተደረገበት ለእያንዳንዱ እቃ አንድ ናሙና ብቻ አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ oz ፋይናንስ ጽ/ቤት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ ከተጠየቀው ናሙና በላይ ያሉ ተጫራች በናሙና አሻሚነት ከውድድር ውጭ ይደረጋል የጨረታው ውጤት ከታወቀ በኋላ ያቀረቡት ናሙናዎች ለተሸናፊዎች ናሙናው የሚመለስም ሲሆን የአሸናፊዎቹ ተጫራቾች ናሙና ግን ያሸነፉት እቃ ሙሉ ለሙሉ አስገብተው ክፍያ ከተፈፀመ በኋላ የሚመለስም ይሆናል፡፡
- መደበኛ የጨረታው ሰነዱ በራሱ አንድ የጨረታ መመሪያና ውል መሆኑን ተጫራቾች መረዳት ይገባቸዋል፤
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ውድድሩን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በሕግ የተጠበቀ ይሆናል፡፡
- አድራሻ፡- አቃቂ ቃሊቲ ከ/ከተማ ቆርቆሮ ፋብሪካ ሳይደርሱ ወረዳ 2 አስተዳደር ሕንፃ ፋይናንስ ጽ/ቤት 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 203 ይገኛል፤
- ስተጨማሪ መረጃ የስልክ ቁጥር- 0114622360 ደውለው ማረጋገጥ ይችላሉ፡፡
በአቃቂ ቃሊቲ ክፍስ ከተማ አስተዳደር የወረዳ 02 አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት
✨ messages.ai_summary
Open tender for procurement of various supplies divided into 8 lots: uniforms, office equipment, printing services, cleaning supplies, consumables, agricultural inputs/seeds, transport services, and wheelchair covers/tires. Bidders must hold valid trade licenses, tax clearance, VAT registration, and supplier registration.
