Tender Detail

Tender Details

  • Company በየካ ክ/ከተማ ት/ጽ/ቤት ደጃ/ወንድይራድ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት
  • Address ኮተቤ ደጃዝማች ወንድይራድ የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት በስተጀርባ በኩል 300 ሜትር ገባ ብሎ : አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 011 645 61 99
  • Website
  • Deadline24 Aug 2026, 10:00 AM
  • magazineAddis Zemen
  • Bid Document Priceብር 400/አራት መቶ/ (non-refundable)
  • Bid Securityየጨረታ ማስከበሪያ ገንዘብ መጠን በየሎቱ ይለያያል።
  • opening dateበአስራ አንደኛው ቀን 4፡30 ሰዓት
  • Categories Other

የእቃ ግዥ ጨረታ

በየካ ክ/ከተማ ት/ጽ/ቤት ደጃ/ወንድይራድ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት


የእቃ ግዥ ጨረታ ማስታወቂያ

በየካ ከ/ከተማ የደጃዝማች ወንድይራድ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት በልዩ ልዩ ሎት የወጡ እቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል። ስለሆነም በጨረታው ለመሣተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች በሙሉ የሚከተሉትን ከ1-10 ያሉትን ሁኔታዎች በቅድሚያ ሟሟላት ይኖርባችኋል፡፡

  1. የዘመኑን የታደሰ ንግድ ፈቃድ፣የንግድ ምዝገባና የምስከር ወረቀት የግብር ከፋይ ምዝገባ ሰርተፊኬት፣ የቫት ተመዝጋቢና ካሽ ሪጅስተር ያለው፤ ታክስ ከፋይነት ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባችኋል፡፡
  2. ለጨረታ የተዘጋጀውን ሰነድ ለመውሰድ ሲመጡ የማይመለስ ብር 400/አራት መቶ/ በመክፈል ከት/ቤቱ ግዥ ክፍል መውሰድ ይችላሉ፡፡
  3. ለጨረታ ማስረከቢያ ተመላሽ የሚሆን ለእያንዳንዱ ሎት በባንክ የተረጋገጠ ሲፒአ/CPO/ ከሎት አንድ እስከ ሎት ሶስት ለእያንዳንዳቸው ብር 20,000.00(ሀያ ሺህ)፤ ከሎት አራት እስከ ሎት ሰባት ለእያንዳንዳቸው ብር 12,500 (አስራ ሁለት ሺህ አምስት መቶ)፣ ለሎት ስምንት እና ዘጠኝ ለእያንዳንዳቸው ብር 10,000 (አስር ሺህ)፣ ለሎት አስር፣ አስራ አንድ እና አስራ ሁለት ለእያንዳንዳቸው ብር 10,000 (አስር ሺህ) ለሎት አስራ ሶስት፤ አስራ አራት እና አስራ አምስት ለእያንዳንዳቸው ብር 5,000 ከጨረታ ሰነዳችሁ ጋር በፖስታ ውስጥ ተያይዞ በጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸኋል፡፡
  4. ተጫራቾች የምትጫረቱበትን ዋጋ በጨረታ ሰነዱ ላይ በተመለከተው መሠረት ከነቫቱ በማሰብ ጠቅላላ ዋጋ ላይ በታሸገ ፖስታ ማህተም ባረፈበት ኦርጂናልና ኮፒ እሽግ ለይቶ በማዘጋጀት በጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸኋል፤
  5. የጨረታው ውጤት እንደታወቀ አሸናፊው ድርጅት ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ 10% በሲፒኦ ማስያዝ አለበት፡፡
  6. ጨረታው በአየር ላይ የሚውለው በጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 10/አስር/ ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 11፡30 ድረስ ክፍት ሆኖ የሚቆይ ሲሆን በማግስቱ በአስራ አንደኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ላይ ሳጥኑ ታሽጎ ፣ 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግዥ ክፍል ቢሮ ቁጥር 5 ጨረታው ይከፈታል፡፡
  7. የጨረታው አሸናፊ ድርጅቶች ያሸነፉበትን ዕቃ በራሳቸው ትራንስፖርት አጓጉዘው ት/ቤቱ ድረስ በማምጣት ገቢ ማድረግ አለባቸው፡፡
  8. ተጫራቾች የሚወዳደሩበት ሎት ከንግድ ፈቃዳቸው ጋር ተዛማጅ ወይም በዛ ዘርፍ የንግድ ፈቃድ ያላቸው መሆን አለበት፡፡
  9. ተጫራቾች የዋጋ ዝርዝራቸውን በገዙት ሰነድ ላይ ብቻ ሞልተው ማቅረብ ይኖርባቸዋል እንጂ በሌላ ዋጋ ላይ ተንተርሰው ማቅረብ አይችሉም፡፡
  10. ተጫራቾች ከጨረታ መክፈቻ ቀን በፊት ባሉት ሥራ ቀናት ውስጥ ለሚወዳደሩበት ዕቃ በየአይነቱ ሳምፕል ማቅረብ አለባቸው፡፡
  11. በጥቃቅን እና አነስተኛ የተደራጃችሁ የንግድ ዘርፍአችሁን የሚገልጽ ደብዳቤ አጽፋችሁ ማምጣት ይኖርባችኋል።
  12. ተጫራቾች ዋጋ ሲሞሉ ሰነዱ ላይ ባለው የዋጋ መሙያ ሰንጠረዥ የእቃው ዋጋ ከቫት በፊት ቫት፣ ጠቅላላ ዋጋ ተብሎ በተገለጸው ቦታ በትክክል መሙላት አለባቸው፡፡
  13. ት/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

አድራሻችን፦ ኮተቤ ደጃዝማች ወንድይራድ የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት በስተጀርባ በኩል 300 ሜትር ገባ ብሎ ሲሆን ለበለጠ መረጃ ደጃ/ወንድይራድ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ስልክ ቁጥር 011 645 61 99

በየካ ክ/ከተማ የደጃዝማች ወንድራድ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት

✨ messages.ai_summary
Open tender for procurement of goods in multiple lots by Dejazmach Wondirad General Secondary School. Bidders must hold valid trade license, VAT registration, and tax clearance. Samples required before bid opening. Transport of goods to school is bidder's responsibility.
Save Tender