አላቂና ቋሚ የቢሮ እቃዎች ግዥ
በጉራጌ ዞን የእኖር ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት
ብሔራዊ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 001/12/2019
በጉራጌ ዞን የእኖር ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት አላቂና ቋሚ የቢሮ እቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
- ሎት 1 እስቴሽነሪ
- ሎት 2 የመኪናና የሞተር ጎማዎች
- ሎት 3 ኤሌክትሮኒክስ
- ሎት 4 የደንብ ልብሶች
- ሎት 5 የጽዳት እቃዎች
- ሎት 6 ሞተር ሳይክል
በዚሁ መሰረት ተጫራቾች:-
- በዘርፉ ህጋዊ ፍቃድ ያላችሁና የዘመኑን ግብር በመክፈል ፈቃድ ያሳደሳችሁ እና ታከስ ክሊራንስ ማቅረብ የምትችሉ።
- የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር /ቲን/ ማቅረብ የሚችሉ።
- በእቃ አቅራቢነት የተመዘገቡ፣ በተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡበት የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ከጠቅላላ ገንዘብ ለሎት 1 ብር 50,000 /ሃምሳ ሺህ ብር/ ለሎት2 ብር 50,000 / ሃምሳ ሺህ ብር/ ለሎት 3 ብር 30,000 /ሰላሳ ሺህ ብር/ ለሎት 4 ብር 20,000 /ሃያ ሺህ ብር/ ለሎት 5 ብር 20,000 /ሃያ ሺህ ብር/ እና ለሎት 6 ብር 50,000 /ሃምሳ ሺህ ብር/ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ የተረጋገጠ CPO ወይም የባንክ ጋራንት በእኖር ወረዳ ፋይናንስ ፅ/ቤት ስም ማሰራት አለባቸው።
- ተጫራቾች አሸናፊ የሆኑባቸው እቃዎች የእኖር ወረዳ ፋይናንስ ፅ/ቤት መጋዘን ድረስ አጠቃለው በአንድ ጊዜ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው
- ተጫራቾች የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ከእኖር ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 5 መውሰድ ይችላሉ።
- ተጫራቾቸ ማሸነፋቸው ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ በ5 የስራ ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ጠቅላላ ዋጋ 10% በባንክ በተረጋገጠ CPO ወይም በጥሬ ገንዘብ በማስያዝ ውል መፈፀም አለባቸው።
- ተጫራቾች በጨረታው ማሸነፋቸውን ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ በ5 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ውል ማስከበሪያ አሰርቶ ውል ካልፈፀሙ መስሪያ ቤቱ የጨረታው ማስከበሪያውን የመውረስ መብት አለው።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸውን አንድ ኦርጅናል እና ሁለት ኮፒ በማድረግ በታሸገ ፖስታ በማድረግ ከ7/12/2018 ዓ.ም ጀምሮ እስከ 21/12/2018 እስከ 8፡00 ድረስ ለጨረታው በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት ይችላሉ።
- ጨረታው በዚህ እለት ከቀኑ 8፡10 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። ነገር ግን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው አለመገኘት ጨረታው ከመክፈት አያስተጓጉለውም፣
- የጨረታ ዋጋው ፀንቶ የሚቆይበት ጊዜ 60/ስልሳ/ ቀናት ብቻ ይሆናል።
- የጨረታ መክፈቻ ቀን ቅዳሜ እና እሁድ ወይም የህዝብ በዓል ቀን ከሆነ ወደ ቀጣይ የስራ ቀን ይዛወራል።
- 7.5 ቫት ዊዝ ሆልድ የምንቆርጥ መሆኑን።
ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር በ09 10 10 67 16 ወይም 09 28 01 17 46 ይደውሉ።
በጉራጌ ዞን የእኖር ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት
ጉንችሬ
✨ messages.ai_summary
Procurement of office supplies and equipment across six lots: stationery, vehicle/motor tires, electronics, uniforms, cleaning supplies, and motorcycles. Bidders must hold valid licenses, tax clearance, TIN, and VAT registration. Delivery required to the district finance office warehouse.
