Tender Detail

Tender Details

  • Company በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ጤና ጽ/ቤት
  • Address በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ መሣለሚያ ወደ 18 አጠና ተራ በሚወስደው መንገድ ከበለስ ሆቴል ትንሽ ገባ ብሎ, Phone: 0112 73 70 72
  • Website
  • Deadline22 Aug 2026, 10:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን ጋዜጣ
  • Bid Document Priceብር 200.00 /ሁለት መቶ/ ብር ብቻ
  • Bid Securityበባንክ በተረጋገጠ (በተመሰከረለት) ሲፒአ (CPO)
  • opening date11ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ በዛው ዕለትና ሰዓት 4:30
  • Categories Health Care, Medical Industry , Office Supplies And Services , Printing And Publishing

Supply of medical drugs, laboratory reagents, office supplies, furniture, clothing, cleaning items, medical equipment, printing, electronics, maintenance and renovation works

በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ጤና ጽ/ቤት


ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

የግዥ መለያ ቁጥር 001/2019ዓ/ም

በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ጤና ጽ/ቤት ሥር የሚገኘው የወረዳ 9 ኳስ ሜዳ ጤና ጣቢያ በ2019ዓ/ም የበጀት ዓመት የሚያስፈልጉትን እቃዎችና አቅርቦቶች ማለትም የህክምና መድሀኒቶችና የላብራቶሪ ሪኤጀንት፣ አላቂ የፅህፈት መሣሪያ፣ ቋሚ የቢሮ እቃዎች፣ የደንብ ልብስ ጨርቆች፣ የፅዳት ዕቃዎች፣ ቋሚ የህክምና መገልገያ መሳሪያዎች፣ ህትመት፣ የኤሌክትሮኒከስ እቃዎች፣ ጥገናና ሰርቪስ፣ አላቂ የቢሮ እቃዎች፣ የተለያዩ ከፍሎች የጥገናና እድሳት ስራ በ2019 ዓ.ም የበጀት ዓመት ግዥ ለመፈጸም ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ይህንን የጨረታ ማስታወቂያ አውጥቷል፡፡

በመሆኑም በዚህ የጨረታ ማስታወቂያ ላይ መወዳደር የሚፈልግ ማንኛውም ህጋዊ ተጫራቾች የሚከተሉትን መስፈርቶች አሟልቶ በጨረታው መወዳደር የሚችሉ መሆኑን እናሳውቃለን ፡፡

  1. በዘርፉ ህጋዊና የታደሰ ንግድ ስራ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን የሀገር ውስጥ ገቢ ግብር አጠናቀው የከፈሉ፡፡
  2. የንግድ ምዝገባ ፈቃድ ወይም ሰርተፍኬት ያላቸው፡፡
  3. ንግድ ፈቃዳቸው በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር በእቅራቢነት የተመዘገበና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ እንዲሁም በዌብሳይት የሚረጋገጥ፡፡
  4. የግብር መክፈያ መለያ ቁጥር (TIN) ያላቸዉ፡፡
  5. የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት ተመዝጋቢ) መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት (ሰርተፍኬት) ማቅረብ የሚችሉና የሚያቀርቡት የጨረታ ዋጋ ከቫት ጋር የተሰላ /ተጨማሪ እሴት ታክስን ያካተተ መሆን አለበት፡፡
  6. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያውን በባንክ በተረጋገጠ (በተመሰከረለት) ሲፒአ (CPO) ከጨረታው ፖስታ ጋር በየግዥ መደቡ (በየሎቱ) ለየብቻ በማሽን አብረው ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡

ማንኛውም ተጫራች ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 (አስር) ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ የጨረታ ሰነዱን ዘወትር በስራ ሰዓት የማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ/ ብር ብቻ በመከፈል በወረዳ 9 ኳስ ሜዳ ጤና ጣቢያ በግዥና ንብረት አስተዳደር ቢሮ በኩል በመቅረብ የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።

ተጫራቾች ሰነዱን ከገዙ በኋላ የሚወዳደሩበትን ዋጋ በመሙላት በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ማህተምና ፊርማ በማድረግ ዋናውንና ፎቶ ኮፒ ሰነዶችን ለየብቻ በማድረግ ማስታወቂያው ለመጀመሪያ ጊዜ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ ከላይ በተጠቀሰው ቢሮ በመገኘት ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡

ለተጫራቾች ጨረታው እንደተጠናቀቀ ተመላሽ የሚደረግ የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ፡፡

ሎት 1፣ መድሀኒቶችና የላብራቶሪ ሪኤጀንቶች22, 500(0.5) (ሃያ ሁለት ሺህ አምስት መቶ ብር)
ሎት 2፣ አላቂ የፅህፈት መሳሪያዎች10,000(0.5) (አስር ሺህ ብር)
ሎት 3 ቋሚ የቢሮ እቃዎች15.000(0.5) (አስራ አምስት ሺህ ብር)
ሎት 4፣ የደንብ ልብስ15,000(0.5) (አስራ አምስት ሺህ ብር)
ሎት 5 ፣ አላቂ የፅዳት ዕቃዎች12.500(0.5) (አስራ ሁለት ሺህ አምስት መቶ ብር)
ሎት 6 ፣ ቋሚና አላቂ የህክምና መገልገያ መሳሪያዎች10.500(0.7) (አስር ሺህ አምስት መቶ ብር)
ሎት 7፥ ህትመት6,000(0.8) (ስድስት ሺህ ብር)
ሎት 8፣ የኤሌክትሮኒከስ እቃዎች ጥገናና ሰርቪስ2,100(0.7) (ሁለት ሺህ አንድ መቶ ብር)
ሎት 9፣ አላቂ የቢሮ ዕቃዎች13.500(0.9) (አስራ ሶስት ሺህ አምስት መቶ ብር)
ሎት 10 የተለያዩ ከፍሎች የጥገናና እድሳት ስራ6,000(05) (ስድስት ሺህ ብር ብቻ)
  1. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት አየር ላይ ቆይቶ 11ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ በ4፡00 ሰዓት ታዛቢዎችና ወኪሎች ባሉበት የጨረታ መቀበያ ጊዜ ያበቃ መሆኑን የሚገልፅ ቃለ-ጉባኤ በመያዝ ታሽጎ በዛው ዕለትና ሰዓት 4:30 ላይ የመከፈቻ ቃለ-ጉባኤ ተይዞ ሲታሸግ የነበሩ ታዛቢዎችና ወኪሎች በተገኙበት ይከፈታል፡፡ በዚህ ዕለት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው እንዲገኙ ይጋበዛሉ፤ ባይገኙ ግን የጨረታ መዝጊያም ሆነ የመከፈቻ ቀኑም ሆነ ሰዓቱ የማይራዘም መሆኑን እናሳስባለን፡፡
  2. አሸናፊ ተጫራቾች የውል ማስከበሪያ የውሉን ዋጋ 10% (አሥር በመቶ) በውል ማስከበሪያነት ለመንግስት መስሪያ ቤቱ ማስያዝ አለባቸው፡፡
  3. ተጫራቾች ለሚያቀርቧቸው ዕቃዎች በጥራት ደረጃ አስተማማኝነቱን የጠበቀ ናሙና ከጨረታው በፊት ማቅረብ አለባቸው።
  4. ማንኛውም የጥቃቅን ተጫራች ካደራጃቸው አካል አምራች መሆናቸውን የሚገልፅ ህጋዊ ደብዳቤ ወይም ሰርተፍኬት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  5. መስሪያ ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥራችን 1-011-275-09-75 ሲያገኙን ይችላሉ። አድራሻ፡- በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ አስተዳደር መማሰሚያ ወዲ ኮልፌ ስጠና ተራ በሚወስደው መንገድ ከበስስ ሆቴል ፊት ስፊት ወይም ከባስሶር ህንፃ በስተጀርባ በኩል የወረዳ 9 ኳስ ሜዳ ጤና ጣቢያ

አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ጽ/ቤት

✨ messages.ai_summary
Open tender for supply of medical drugs, lab reagents, office supplies, furniture, clothing, cleaning items, medical equipment, printing, electronics, maintenance and renovation works for Addis Ketema Health Office. Bidders need valid trade license, TIN, VAT registration, and supplier registration with Ministry.
Save Tender