Tender Detail

Tender Details

  • Deadline24 Feb 2021, 12:00 AM
  • magazineWorld Bank
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2021-02-02 00:00:00
  • Categories

procurement of 70 Quntals of pelleted fish feed


Source: World Bank — Livestock and Fisheries Sector Development Project

የአሳ መኖ፣ የሳር ማሰሪያ ቤለርና የዶሮ ማጓጓዣ ሳጥን ግዥ የብሔራዊ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የእንስሳትና አሳ ዘርፍ ልማት ፕሮጀክት ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ለባህር ዳር አሳና ሌሎች የውሀ ውስጥ ህይወት ምርመር ማዕከልና ለአንዳሳ እንስሳት ምርምር ማዕከል አገልግሎት የሚውሉ በግዥው መለያ ቁጥር ET-AMH-LFSDP-GO-RFB-03/2020 (ሎት 01) የተመጣጠነ የአሳ መኖ (ተንሳፋፊ የሆነ) እና በግዥው መለያ ቁጥር ET-AMH-LFSDP-GO-RFB-04/2020 (ሎት 02) የሳር ማሰሪያ ቤለርና የዶሮ ማጓጓዣ ሳጥን (ኩብ) በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል፡፡

  1. በዘመኑ የታደሰና በዘርፉ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ማቅረብ የሚችሉ
  3. የግዥው መጠን ብር 200,000.00 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) በላይ ከሆነ በተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሊ፡
  4. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከፋይናንሻል ፕሮፖዛል ከኦሪጅናል ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  5. የሚፈለገውን የእቃ አይነትና ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 100.00 (መቶ ብር) በመክፈል አብክመ እንስሳትና አሳ ዘርፍ ልማት ፕሮጀክት ቢሮ ቢሮ ቁጥር 04 ማግኘት ይችላሉ፡፡
  7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለሎት 01 (የአሳ መኖ) ብር 8,000.00 (ስምንት ሺህ ብር) ለሎት 02 (የሳር ማሰሪያ ቤለርና የዶሮ ማጓጓዣ ሳጥን) ብር 20,000.00 (ሀያ ሺ ብር) በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲ.ፐ.ኦ) ወይም በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ አለባቸው፡፡
  8. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሀሳቡን የቴክኒክ ዶክመንትና የዋጋ ማቅረቢያ (ፋይናንሻል ዶክመንት) ዋናና ቅጅ በማለት በፖስታ አሽጎ አብክመ እንስሳት ሀብት ልማት ማስፋፊያ ኤጀንሲ እንስሳትና አሳ ዘርፍ ልማት ፕሮጀክት ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 06 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ማቅረብ ይችላል፡፡
  9. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በባህር ዳር ከተማ አብክመ እንስሳት ሀብት ልማት ማስፋፊያ ኤጀንሲ እንስሳትና አሳ ዘርፍ ልማት ፕሮጀክት ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 06   -ታህሳስ 15 ቀን 2013 ዓ.ም 4፡00 ላይ ተዘግቶ በዕለቱ 4፡30 ሰዓት ላይ በግልጽ ይከፈታል፡፡ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው የማይገኙ ከሆነ ጨረታውን ከመከፈት አያግደውም፡፡
  10. ቢሮው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል  የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ 
  11. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር ማስረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 06 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 0583205297 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡

የአብክመ እንስሳትና አሳ ዘርፍ ልማት ፕሮጀክት

ባህር-ዳር

 

Save Tender