Tender Detail

Tender Details


Lot 01 (fish production materials), Lot 02 (laboratory equipment), Lot 03 (Nursery materials ), Lot 04 ( poultry production equipment


Source: World Bank — Livestock and Fisheries Sector Development Project

የአሳ መኖ፣ ላብራቶሪ መሳሪያዎች እና የተለያዩ ቁሳቁሶች ግዥ

የብሔራዊ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የእንስሳትና አሳ ዘርፍ ልማት ፕሮጀክት ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ለባህር ዳር አሳና ሌሎች የውሀ ውስጥ ህይወት ምርመር ማዕከል፣ ለባህር ዳር እንስሳት በሽታ ቅኝት፣ ጥናትና ምርምር ላብራቶሪ ማዕከል፣ ለአንዳሳ እንስሳት ምርምር ማዕከል እና ለፕሮጀክቱ ወረዳዎች አገልግሎት የሚውሉ በግዥው መለያ ቁጥር ET-AMH-LFSDP-GO-RFB-06/2021 የተዘረዘሩትን ሎት 01 (የተመጣጠነ የአሳ መኖ፣ ስክሪን ሀውስ፣ የውሀ መሳቢያ ፓምፕ እና በአካባቢ ባለሙያ የሚሰሩ አዳራሽ ፈርኒቸሮች)፣ ሎት 02 (የእንስሳት ጤና ላብራቶሪ መሳሪያዎች)፣  ሎት 03 (የችግኝ ጣቢያ ቁሳቁሶች እና የሳር ማሰሪያ ቤለር) እና ሎት 04 (የዶሮ ማጓጓዥ ኩብ፣ ስፔክትሮ ፎቶ ሜትር እና የቅልጠት መጠን መለኪያ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል፡፡

  1. በዘመኑ የታደሰና በዘርፉ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ማቅረብ የሚችሉ
  3. የግዥው መጠን ብር 200,000.00 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) በላይ ከሆነ በተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሊ፡
  4. የተመጣጠነ የአሳ መኖ ተወዳዳሪዎች የመድሀኒትና መኖ አስተዳደር ቁጥጥር ባለስልጣን የሰጠውን የብቃት ማረጋገጫ እና የደረጃዎች መዳቢ ባለስልጣን ያወጣውን መስፈርት ማሟላት ይጠበቅባቸዋል፡፡
  5. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-4 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከፋይናንሻል ፕሮፖዛል ከኦሪጅናል ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  6. የሚፈለገውን የእቃ አይነትና ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  7. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 100.00 (መቶ ብር) በመክፈል አብክመ እንስሳትና አሳ ዘርፍ ልማት ፕሮጀክት ቢሮ ቢሮ ቁጥር 04 ማግኘት ይችላሉ፡፡
  8. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለሎት 01 (የተመጣጠነ የአሳ መኖ፣ ስክሪን ሀውስ፣ የውሀ መሳቢያ ፓምፕ እና የአዳራሽ ፈርኒቸሮች) ብር 20,000.00 (ሀያ ሺ ብር)፣ ለሎት 02 (የእንስሳት ጤና ላብራቶሪ መሳሪያዎች) ብር 5,000.00 (አምስት ሺ ብር)፣ ለሎት 03 (የችግኝ ጣቢያ ቁሳቁሶች እና የሳር ማሰሪያ ቤለር) ብር 80,000.00 (ሰማንያ ሺህ ብር) እና ለሎት 04 (የዶሮ ማጓጓዥ ኩብ፣ ስፔክትሮ ፎቶ ሜትር እና የቅልጠት መጠን መለኪያ ብር 20,000.00 (ሀያ ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲ.ፐ.ኦ) ወይም በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ አለባቸው፡፡
  9. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሀሳቡን የቴክኒክ ዶክመንትና የዋጋ ማቅረቢያ (ፋይናንሻል ዶክመንት) ዋናና ቅጅ በማለት በፖስታ አሽጎ አብክመ እንስሳት ሀብት ልማት ማስፋፊያ ኤጀንሲ እንስሳትና አሳ ዘርፍ ልማት ፕሮጀክት ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 06 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ማቅረብ ይችላል፡፡ አንድ ተጫራቾች በአንዱ ወይም በሁሉም ሎት መወዳደር ይችላል፡፡
  10. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በባህር ዳር ከተማ አብክመ እንስሳት ሀብት ልማት ማስፋፊያ ኤጀንሲ እንስሳትና አሳ ዘርፍ ልማት ፕሮጀክት ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 06   -መጋቢት 23 ቀን 2013 ዓ.ም 4፡00 ላይ ተዘግቶ በዕለቱ 4፡30 ሰዓት ላይ በግልጽ ይከፈታል፡፡ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው የማይገኙ ከሆነ ጨረታውን ከመከፈት አያግደውም፡፡
  11. ቢሮው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል  የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ 
  12. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር ማስረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 06 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 0583205297 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡

የአብክመ እንስሳትና አሳ ዘርፍ ልማት ፕሮጀክት

ባህር-ዳር


 

Save Tender