procurement of Screen house, water supply equipment & furniture (lot 01), laboratory equipment (lot 02) & forage seed, Baler & forage nursery sit hand tools & equipment s (lot 03)
Source: World Bank — Livestock and Fisheries Sector Development Project
የተለያዩ የላብራቶሪ መሳሪያዎችና ቁሳቁሶች እና የመኖ ዘር ግዥ የብሔራዊ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የእንስሳትና አሳ ዘርፍ ልማት ፕሮጀክት ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ለባህር ዳር አሳና ሌሎች የውሀ ውስጥ ህይወት ምርመር ማዕከል፣ ለባህር ዳር እንስሳት በሽታ ቅኝት፣ ጥናትና ምርመራ ማዕከል እንዲሁም ለፕሮጀክቱ ወረዳዎች አገልግሎት የሚውሉ በግዥው መለያ ቁጥር ET-AMH-LFSDP-GO-RFB-05/2020 የተዘረዘሩትን ሎት 01 (ስክሪን ሀውስ፣ ለውሀ መሳቢያ የሚያገለግሉ ፓምፕ እና የመሰብሰቢያ አዳራሽ ፈርኒቸሮች)፣ ሎት 02 (የላብራቶሪ መሳሪያዎች) እና ሎት 03 (የእንስሳት መኖ ዘር፣ የሳር ማሰሪያ ቤለር እና ለመኖ ልማት የሚያገለግሉ ቀላል የእጅ መሳሪያዎችን) በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል፡፡
- በዘመኑ የታደሰና በዘርፉ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ማቅረብ የሚችሉ
- የግዥው መጠን ብር 200,000.00 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) በላይ ከሆነ በተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሊ፡
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከፋይናንሻል ፕሮፖዛል ከኦሪጅናል ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የሚፈለገውን የእቃ አይነትና ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል አብክመ እንስሳትና አሳ ዘርፍ ልማት ፕሮጀክት ቢሮ ቢሮ ቁጥር 04 ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለሎት 01 (ስክሪን ሀውስ፣ ለውሀ መሳቢያ የሚያገለግሉ ፓምፕ እና የመሰብሰቢያ አዳራሽ ፈርኒቸሮች) ብር 20,000.00 (ሀያ ሺህ ብር)፣ ለሎት 02 (የላብራቶሪ መሳሪያዎች) ብር 5,000.00 (አምስት ሺህ ብር) ሎት 03 (የእንስሳት መኖ ዘር፣ የሳር ማሰሪያ ቤለር እና ለመኖ ልማት የሚያገለግሉ ቀላል የእጅ መሳሪያዎችን) ብር 80,000.00 (ሰማንያ ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲ.ፐ.ኦ) ወይም በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ አለባቸው፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሀሳቡን የቴክኒክ ዶክመንትና የዋጋ ማቅረቢያ (ፋይናንሻል ዶክመንት) ዋናና ቅጅ በማለት በፖስታ አሽጎ አብክመ እንስሳት ሀብት ልማት ማስፋፊያ ኤጀንሲ እንስሳትና አሳ ዘርፍ ልማት ፕሮጀክት ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 06 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ማቅረብ ይችላል፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በባህር ዳር ከተማ አብክመ እንስሳት ሀብት ልማት ማስፋፊያ ኤጀንሲ እንስሳትና አሳ ዘርፍ ልማት ፕሮጀክት ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 06 ታህሳስ 22 ቀን 2013 ዓ.ም 4፡00 ላይ ተዘግቶ በዕለቱ 4፡30 ሰዓት ላይ በግልጽ ይከፈታል፡፡ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው የማይገኙ ከሆነ ጨረታውን ከመከፈት አያግደውም፡፡
- ቢሮው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር ማስረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 06 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 0583205297 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡
የአብክመ እንስሳትና አሳ ዘርፍ ልማት ፕሮጀክት
ባህር-ዳር
