procurement of laboratory equipment
Source: World Bank — Livestock and Fisheries Sector Development Project
የእንስሳት ህክምና መገልገያ መሳሪያዎች የብሔራዊ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
የግዥው መለያ ቁጥር ET-AMH-LFSDP-GO-RFB-02/2020
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የእንስሳትና አሳ ዘርፍ ልማት ፕሮጀክት ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ፕሮጀክቱ ለሚደግፋቸው ወረዳዎች ለወረዳ እና ቀበሌ የእንስሳት ክሊኒኮች አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ እንስሳት ጤና ህክምና መገልገያ መሳሪያዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል፡፡
- በዘመኑ የታደሰና በዘርፉ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ማቅረብ የሚችሉ
- የግዥው መጠን ብር 200,000.00 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) በላይ ከሆነ በተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሊ፡
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከፋይናንሻል ፕሮፖዛል ከኦሪጅናል ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የሚፈለገውን የእቃ አይነትና ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 100.00 (መቶ ብር) በመክፈል አብክመ እንስሳትና አሳ ዘርፍ ልማት ፕሮጀክት ቢሮ ቢሮ ቁጥር 04 ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ወይም ቢድ ቦንድ ብር 68,000.00 (ስልሳ ስምንት ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲ.ፐ.ኦ) ወይም በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ አለባቸው፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሀሳቡን የቴክኒክ ዶክመንትና የዋጋ ማቅረቢያ (ፋይናንሻል ዶክመንት) ዋናና ቅጅ በማለት በፖስታ አሽጎ አብክመ እንስሳት ሀብት ልማት ማስፋፊያ ኤጀንሲ እንስሳትና አሳ ዘርፍ ልማት ፕሮጀክት ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 06 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ማቅረብ ይችላል፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በባህር ዳር ከተማ አብክመ እንስሳት ሀብት ልማት ማስፋፊያ ኤጀንሲ እንስሳትና አሳ ዘርፍ ልማት ፕሮጀክት ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 06 ህዳር 28 ቀን 2013 ዓ.ም 4፡00 ላይ ተዘግቶ በዕለቱ 4፡30 ሰዓት ላይ በግልጽ ይከፈታል፡፡ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው የማይገኙ ከሆነ ጨረታውን ከመከፈት አያግደውም፡፡
- ቢሮው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር ማስረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 06 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 0583205297 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡
የአብክመ እንስሳትና አሳ ዘርፍ ልማት ፕሮጀክት
ባህር-ዳር
