Procurement of Dairy & fishery equipment's:- 104 pcs of Aluminum cans, 26 pcs of cream separators, 26 pcs of butter churners, 34 pcs of refrigerators & 8 pcs of Deep freezers.
Source: World Bank — Livestock and Fisheries Sector Development Project
በእንስሳት ዘርፍ ለተሰማሩ ደረጃ 2 ተጠቃሚዎች የተለያዩ ቁሳቁሶች ግዥ
የብሔራዊ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
የግዥው መለያ ቁጥር ET-AMH-LFSDP-GOS-RFB-0022/2023
የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የእንስሳትና አሳ ዘርፍ ልማት ፕሮጀክት ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ከአለምባንክ ባገኘው የበጀት ድጋፍ በእንስሳት ዘርፍ በወተት እና በአሳ ህብረት ስራ ማህበራት ለተደራጁ ማህበራት አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ ቁሳቁሶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል፡፡
- በዘመኑ የታደሰና በዘርፉ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ማቅረብ የሚችሉ
- የግዥው መጠን ብር 200,000.00 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) በላይ ከሆነ በተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሊ፡
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከኦሪጅናል ፋይናንሻል ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የሚፈለጉትን የእቃዎች አይነትና ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል አብክመ እንስሳትና አሳ ዘርፍ ልማት ፕሮጀክት ቢሮ ቢሮ ቁጥር 06 ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ወይም ቢድ ቦንድ ብር 400,000.00 (አራት መቶ ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲ.ፐ.ኦ) ወይም በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ አለባቸው፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሀሳቡን የቴክኒክ ዶክመንትና የዋጋ ማቅረቢያ (ፋይናንሻል ዶክመንት) ዋናና ቅጅ በማለት በተለያየ ፖስታ አሽጎ አብክመ እንስሳት ሀብት ልማት ማስፋፊያ ኤጀንሲ እንስሳትና አሳ ዘርፍ ልማት ፕሮጀክት ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 06 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ማቅረብ ይችላል፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በባህር ዳር ከተማ አብክመ እንስሳት ሀብት ልማት ማስፋፊያ ኤጀንሲ እንስሳትና አሳ ዘርፍ ልማት ፕሮጀክት ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 06 መጋቢት 12 ቀን 2015 ዓ.ም 4፡00 ላይ ተዘግቶ በዕለቱ 4፡30 ሰዓት ላይ በግልጽ ይከፈታል፡፡ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው የማይገኙ ከሆነ ጨረታውን ከመከፈት አያግደውም፡፡
- ቢሮው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር ማስረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 06 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 0583205297 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡
የአብክመ እንስሳትና አሳ ዘርፍ ልማት ፕሮጀክት
ባህር-ዳር
