ቦሌ ማተሚያ ኃ.የተ.የግ.ማህበር፦ ልዩ ልዩ ወረቀቶችን፣ Green light balacren, A3 & A4 Kaki posta በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
Bole printing PLC
የሀገር ውስጥ የግዥ ጨረታ ማስታወቂያ
ቦሌ ማተሚያ ኃ.የተ.የግ.ማህበር፦ ልዩ ልዩ ወረቀቶችን፣ Green light balacren, A3 & A4 Kaki posta በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
1. ተጫራቾች በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፍቃድ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፣ የቫት ተመዝጋቢ የምስከርወረቀት፣ የንግድ ሰርተፍኬት እና ሌሎችም የህጋዊነት ማረጋገጫ ሰነዶች ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
2. ተጫራቾች በቅድሚያ የማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ/ ቢሮ ቁጥር 101 በመከፈል ለዚሁ ጨረታ የተዘጋጀውን ሰነድ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 /አስራ አምስት/ተከታታይ ቀናት ድረስ ቦሌ መንገድ ከቶታል ነዳጅ ማደያ ዝቅ ብሎ በሚገኘው ቢሯችን መግዛት ይኖርባቸዋል፡፡
3. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ የዋጋቸውን 2% በባንክ በተረጋገጠ ቼክ (ሲፒኦ) በቅድሚያ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
4. ተጫራቾች ቴከኒካል እና ፋይናንሺያል ሰነዶችን በተለያየ ፖስታ አሽገው ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ከግዥ ከፍል በሚገኘው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ያስገባሉ፡፡
5. ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባለው 15ኛው ቀን ከረፋዱ 3፡00 ሰዓት ላይ የጨረታ ሳጥኑ ታሽጎ በዚሁ እለት በ3፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኘበት በማህበሩ የስብሰባ አዳራሽ/የግዢ ክፍል ይከፈታል፡፡ 15ኛው ቀን በዝግ ቀን ከዋለ በቀጣይ የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
6. ሁሉም ተጫራቾች ለጥራት ሙከራ የሚሆን ናሙና ጨረታው በሚከፈትበት እለት ወይም አስቀድመው ማቅረብ የሚጠበቅባቸው ሲሆን ዝርዝር አፈጻጸሙም ለካኪ ፖስታ የሚሳተፉ ተጫራቾች በቀረበው ናሙና መሰረት ከብ ማህተም በማድረግ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
7. ለወረቀቶች የሚሳተፉ ተጫራቾች ለጥራት ሙከራ የሚሆን በቂ ናሙናዎችን በእያንዳንዱ ናሙና ጫፍ ላይ ከብ ማህተም በመምታት በA3 ፖስታ አሽገው ማምጣት አለባቸው፡፡
8. ለባራከረን የሚሳተፉ ደረጃውን የጠበቀ ናሙና ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
9. ሁሉም ተጫራቾች ለሚሳተፉበት ግብአት እቃው ከመጋዘን ያላቸው ወይም ውል በተፈረመ ቢዘገይበ5 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ብቻ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
10. ድርጅቱ ሌላ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ ::
አድራሻ፦ ቦሴ መንገድ ከቶታል ነዳጅ ማደያ ዝቅ ብሎ
ስልክ ቁጥር ...........01115 15 50 05/0115 51 88 72
ፋስክ.....0115 51 86 96
ፖ.ስ.ቁ. .2365
ቦሴ ማተሚያ ኃ/የተ/የግ/ማህበር
