የጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 2 ፋ/ጽ/ቤት ለ2018 በጀት ዓመት iኛ ዙር ለጽህፈት ቤቶች መገልገያ አላቂ የቢሮ መገልገያ እቃዎች የጽዳት እቃዎች እና የተለያዩ የደንብ ልብስ እና ስፈት ግዥዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
በጉለሌ ክ/ከተማ የወረዳ 2 ፋይናንስ ጽ/ቤት
ጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 002/2019
የጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 2 ፋ/ጽ/ቤት ለ2018 በጀት ዓመት iኛ ዙር ለጽህፈት ቤቶች መገልገያ አላቂ የቢሮ መገልገያ እቃዎች የጽዳት እቃዎች እና የተለያዩ የደንብ ልብስ እና ስፈት ግዥዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
1.ሎት1 01/የአለቂ የብሮ ዕቃዎች
2. ሎት 02/ የጽዳት ዕቃዎች
3. ሎት 03 የደንብ ልብስ ዕቃዎች
4. ሎት 04 የደንብ ልብስ ስፌት በግልጽ ጨረታ አወደድሮ መግዛት ይፈልጋል በመሆኑም በጨረታው መካፈል የሚፈልጉ ተጫራቾች የሚከተሉትን ሁኔታዎች በቅድሚያ ማሟላት ይኖርባቸዋል
ተጫራቾች በተሰማሩበት የስራ መስክ የዘመኑን ግብር ለመከፈላቸው እና የታደሰ የንግድ ፍቃድ የአቅራቢነት ሊስት ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
ተጫራቾች በጥቃቅንና እነስተኛ የተደራጁ ከሆን የሚወዳደሩት በሚያመርቱ እታ ወይም ተጨማሪ እሴት ለጨመሩት እቃ ሲሆን ከዚህ ውጭ ለሆኑ እቃዎች የሚወዳደሩት እንደማንኛውም ተጫራች ሰነድ በመግዛትና ሲፒኦ(cpo) በማስያዝ ይሆናል፡፡ ተወዳዳሪዎች በሚያመርቱት እታ ሲወዳደሩ እና ካደራጃቸው መስሪያ ቤት የድጋፍ ደብዳቤ ሲያመጡ ልዩ ድጋፍ ይደረግላቸዋል።
የመንግስት የግዥ ጨረታ ላይ ለመሳተፍ የሚያስችል የተሟላ ማስረጃ ያላቸው መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው፡፡
የጨረታ ሰነዱን በጉለሌ ክ/ከተማ ከወረዳ 2 ፋይናንስ ጽ/ቤት 4ኛ ፎቅ ላይ ቢሮ ቁጥር 12 በመምጣት ሰነዱን በማይመለስ ለእያንዳንዱ ሎት ብር 300 (ሶስት መቶ ብር ብቻ) በመግዛት መውሰድ ይችላሉ፡፡
የጨረታውን ሰነድ አርጅናል እና ኮፒ ሞልተው ማቅረብ አለባቸው።
ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀናት እንስቶ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት ይቆያል፡፡
ጨረታው በአስረኛው ቀን 10፡30 ሰዓት ላይ ታሽጎ በአስራ አንደኛው ቀን 3:30 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በጉለሌ ከ/ከተማ ወረዳ 2 ፋይናንስ ጽ/ቤት 4ኛ ፎቅ ላይ ቢሮ ቁጥር 12 ይከፈታል።
ተጫራቾች ከጨረታው ሰነድ ዉ ተሞልቶ የመጡት ሰነድ ተቀባይነት የለውም፡፡
መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፈል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ማስያዝ የሚኖርባቸው ሲሆን ይኸውም
ሎት 01/ የአላቂ የቢሮ ዕቃዎች የሚሆን ብር 15,000 ( አስራ አምስት ሺህ ብር ብቻ) ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
ሎት 02/ የጽዳት ዕቃዎች የሚሆን ብር 20,000 (ሀያ ሺህ ብር ብቻ) ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
ሎት 03/ የደንብ ልብስ ዕቃዎችና የሚሆን ብር 10.000 (እ ስ ር ሺህ ብር ብቻ) ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
ሎት 04/ የደንብ ልብስ ሰፊት የሚሆን ብር 10,000 (አስር ሺህ ብር ብቻ) ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ እንዲሁም የጨረታ አሸናፊ ከሆኑ በኋላ የውል ማስከበሪያ 10% ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
ተጫራቶች ናሙና ለሚያስፈልጋቸው ዕቃዎች ናሙና የማቅረብ ግዴታ ይኖርባቸዋል የሚቀርቡትም ናሙናዎች ተፈተው የሚታዩ መሆናቸውን ተጫራቾች ማወቅ አለባቸው::
ተጫራቾች በአማራጭ ገበያ መጠቀም የተከለከለ ነው፡፡
ተጫሪቶች የአሸነፉባቸውን ዕቃዎች በራሳቸው ትራንስፖርት ወረዳ ግቢ ድረስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
መ/ቤቱ ከአሸናፊው ድርጅት የአሸነፉበትን ዋጋ መጠን እና ብዛት 25 % ተጨማሪ ትዕዛዝ መጠየቅ የሚችል መሆኑ መታወቅ አለበት፡፡
መ/ቤቱ ከውል በፊት እንደ አስፈላጊነቱ የእቃውን ብዛት 20% መጨመር ወይም መቀነስ እንደሚችል መታወቅ አለበት፡፡
የጨረታውን ሰነድ አርጅናል እና ኮፒ ሞልተው ማቅረብ አለባቸው ሁለቱም ፖስታዎች አንድ አይነት ሰነድ ሞልተው መያያዝ አለበት
ለተጨማሪ ማብራርያ፦
አድራሻ፡- ስድስት ኪሎ ከፍ ብሎ ስብሰባ ማዕከል አጠገብ ወደ ሐምሌ19 መናፈሻ ሳይደርስ 50 ሜትር ገባ ብሎ
ስልክ ቁጥር፡- 011-1-23-43-69 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
የጉስሴ ክ/ከተማ ወረዳ 2 ፋ/ጽ/ቤት
