Tender Detail

Tender Details


የጌራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በ2019 በጀት በወረዳው ስር ለሚገኙ ሴክተር መ/ቤቶች ኤሌክትሮኒከስ እቃዎች እና በአንድ መስኮት አገልግሎት መስጫ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል።

የጌራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት


የጨረታ ማስታወቂያ

የጌራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በ2019 በጀት በወረዳው ስር ለሚገኙ ሴክተር መ/ቤቶች ኤሌክትሮኒከስ እቃዎች እና በአንድ መስኮት አገልግሎት መስጫ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል። ስለዚህ በዚህ ጨረታ ላይ ለመወዳደር ለምትፈልጉ ተወዳዳሪዎች በሙሉ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት አለባቸው።

1- የ2019 ዓ.ም ግብር የገበረ እና የንግድ ፈቃዱን ያደሰ።

2- ቲን ወይም የቫት ተመዝጋቢ የሆነ

3. የጨረታ ማስከበርያ ከአጠቃላይ ዋጋ 2% በሲፒኦ ወይም በባንክ በተረጋገጠ ቼክማስያዝ ይኖርባቸዋል

4- ከመስረያ ቤቱ ጋር ውል ለመፈራረም ፈቃደኛ የሆነ፣

5- የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ 500 (አምስት መቶ) ብር በመክፈል መግዛት ይኖርባቸዋል

6- Withholding Tax (3%) ለመክፈል ፍቃደኛ የሆነ፡፡

7- በወረዳው ስር የሚገኘ በማይክሮ የተደራጁት በውድድር ውስጥ ከገቡ ይበረታታሉ።

8- በማይክሮ የተደራጁ ካደራጃቸው መስሪያቤት ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

9. ተጫራቾች ሰነዳቸውን ዋናውንና ፎቶ ኮፒውን በመለየት በማሸግ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡

10- ተጫራቾች ሌሎች በሚያቀርቡት ዋጋ ላይ ተንተርሰው ዋጋ ማቅረብ በህግ የተከለከለ ነው፡፡

11- የመዝገቢያ ቦታ ጌራ ወረዳ ገንዘብ/ጽ/ቤት የግዥ እና ንብረት አስተዳደር ይሆናል፡፡

12- የመመዝገቢያ ቀን ይህ ጨረታ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ከሁለት የስራ ቀናት በኃላ ለ15 ተከታታይ የስራ ቀናቶች አየር ላይ ይቆያል፡፡ ጨረታው የሚከፈተው በ15ኛው ቀን በ6፡00 ተዘግቶ በዚያው ቀን ከቀኑ በ8፡00 ይከፈታል፡፡

13- የጨረታው አሸናፊ የአሸነፈበትን እቃ እስከ ጌራ ወረዳ ገንዘብ/ጽ/ቤት ድረስ በራሱ ወጪ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

14- የእቃው ብዛት በ20% ሊቀንስም ሊጨምርም ይችላል፡፡

15- መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።

ለበለጠ መረጃ፡- በስልክ ቁጥር: 047-342-00-24/0473420043

የጌራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት

✨ messages.ai_summary
- **Procurement:** Electronics items and one-stop service provision for sector offices under Gera district, procured through open tender under the 2019 budget. - **Issuer:** Gera District Finance Office, Oromia. - **Dates:** Posted 2026-07-31; submission deadline and bid opening on 2026-08-18. - **Cost & Bond:** Non-refundable bid document price of 500 ETB; bid bond of 2% of the total price via CPO or bank-guaranteed check. - **Requirements:** Valid 2019 tax payment and renewed trade license; TIN or VAT registration; willingness to pay 3% withholding tax; winner must deliver goods to Gera District Finance Office at own cost; quantity may vary by ±20%; micro-enterprises under the district are encouraged and must provide evidence from their organizing office.
Save Tender