የመኪና ሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ።
የደንበሳ ክ/ከተማ ወረዳ ፍርድ ቤት የፍታብሔር ችሎት
ጨረታ ማስታወቂያ
የፍርድ ባለመብት የሱፍ አብዶ የፍርድ ባለዕዳ አቶ ካልሐሪ ፋርም ኢንዱስትሪ PLC መካከል ያለውን የአፈጻጸም ከርከር እስመልከቶ 1ኛ/ ፒካኘ ሚትስቡሽ መኪና የሰሌዳ ቁጥሩ A3-32693 AA የሆነ የሞተር ቁጥር 4D56U-CFB0167P32513 የሆነ የሻንሲ ቁጥር MMBINKB40FD015480 የሆነ እና በአፈጻጸም ተከሣሽ ካልሐሪ ፋርም ኢንዱስትሪ PLC ስም ተመዝግቦ ያለውን በጨረታ ማስታወቂያ መነሻ ዋጋው ስምንት መቶ ሰባት ሺህ ሶስት መቶ ሰማኒያ አምስት ብር ከዘጠና አምስት ሣንቲም (807,385.95) እና 2ኛ/ የእርሻ ትራከተር ብዛት ሁለት/2/ 2ኛ/ የሞተር ቁጥር LM9B602V514456A የሆነ የሻንሲ ቁጥር K72167 የሆነ እንዲሁም የእርሻ ትራከተር የሞተር ቁጥር LM9B602V514485A የሻንሲ ቁጥር K72168 እና በአፈጻጸም ተከሣሽ ካልሐሪ ፋርም ኢንዱስትሪ PLC ስም ተመዝግቦ ያለውን በጨረታ ማስታወቂያ መነሻ ዋጋው እያንዳንዱ ትራከተር መኪና ዋጋ አራት መቶ ስልሳ ዘጠኝ ሺህ ስድስት መቶ ዘጠና ሶስት ብር ከሃምሣ ሶስት ሣንቲም (469,693.53) የሆነ በአጠቃላይ ከዚህ በላይየተገለጹት ሶስቱ/3/ መኪናዎች ፍ/ቤቱ ግልጽ በሆነ ጨረታ አካሂዶ መሸጥ ስለፈለገ፣ በዚህ ጨረታ ላይተሳትፈው የመግዛት ፍላጐት ያላቸው ሰዎች ከቀረበው ግምት ብር ላይ 1/4ኛውን አስቀድመው በባንከ CPO በማስያዝ በአዳማ ከተማ ደምበላ ከፍለ ከተማ ወንጂ ወረዳ በወንጂ ወረዳ ፖሊስ ጽ/ቤት ቅጥርግቢ መኪናዎቹ በቆሙበት በሚገኙበት ቀርበው መወዳደር ይችላሉ፣ የጨረታው ማስተወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ታትሞ እስከ ቀን 22/12/2018 እስከ 12፡00 ሰዓት በአየር ላይ ቆይቶ በቀን 22/12/2018 ከምሽቱ 12፡00 ላይ ተዘግቶ በቀን 23/12/2018 3፡30 ሰዓት እስከ 6፡30 ሰዓት ድረስ ተወዳዳሪዎች ፣ የጨረታ አጫራቾች እና ታዛቢዎች ባሉበት ተከፍቶ በቀረበው መነሻ ዋጋ ላይ ከፍተኛ ዋጋ ላቀረበው የሚሸጥ ወይም የሚካሄድ መሆኑን በማወቅ በአካል ቀርበው ተወዳድረው መግዛት እንደሚቻል የደምበላ ከፍለ ከተማ ወረዳ ፍ/ቤት አዟል፡፡
ማሳሰቢያ
1 በዚህ ጨረታ ላይ ለመወዳደር ወይም ለመሳተፍ የመጣ የግምቱ መነሻ ዋጋ ላይ 1/4ኛ CPO ያስያዘበትን ለጨረታ ኮሚቴ ማቅረብ አለበት፡፡
2. የጨረታው አሸናፊ ያሸነፈበትን ገንዘብ ዋጋ ጨረታው ከተካሄደበት ቀን አንስቶ በ15 ቀናቶች ውስጥ መክፈል መቻል ይኖርበታል፡፡
3. ጨረታው የሚካሄደውበት ቦታ በወንጂ ወረዳ ፖሊስ ጽ/ቤት ውስጥ ነው፡፡
4. የጨረታውን ውጤት በቀን 25/12/2018 4፡00 ሰዓት ላይ ይቀርባል፡፡
5. የስልክ ቁጥር 0911840256 ላይ መደወል ይቻላል፡፡
የደንበሳ ክ/ከተማ ወረዳ ፍርድ ቤት የፍታብሔር ችሎት
