Tender Detail

Tender Details

  • Company NABU Ethiopia
  • Address , Phone:
  • Website
  • Deadline05 Aug 2026, 3:59 PM
  • magazineReporter Tenders
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2026-07-29 15:59:00
  • Categories

ናቡ ኢትዮጵያ (The Nature and Biodiversity Conservation Union (NABU) ETHIOPIA፣ ደቡብ ምዕራብ ሪጅናል ጽ/ቤት በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል በካፋ ዞን በሚገኙ ሦስት ወረዳዎች (ጨታ ፣ጊምቦ እና ገዋታ)  እየተገበረ ላለው “Strategic Partnership Agreement”  ፕሮጀክት ለሚደገፉ ተጠቃሚዎች የሚሰራጭ እስከ 2000 /ሁለት ሺህ/ የሚሆን የተዳቀለ /grafted Avocado seedlings/ ከህጋዊ አምራቾች /አቅራቢዎች/ በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

NABU Ethiopia


የአቮካዶ ችግኝ ግዥ ጨረታ ማስታወቂያ

ናቡ ኢትዮጵያ (The Nature and Biodiversity Conservation Union (NABU) ETHIOPIA፣ ደቡብ ምዕራብ ሪጅናል ጽ/ቤት በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል በካፋ ዞን በሚገኙ ሦስት ወረዳዎች (ጨታ ፣ጊምቦ እና ገዋታ)  እየተገበረ ላለው “Strategic Partnership Agreement”  ፕሮጀክት ለሚደገፉ ተጠቃሚዎች የሚሰራጭ እስከ 2000 /ሁለት ሺህ/ የሚሆን የተዳቀለ /grafted Avocado seedlings/ ከህጋዊ አምራቾች /አቅራቢዎች/ በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

በዚህም መሰረት ከታች የተቀመጠውን ዝርዝር መስፈርት የምታሟሉ ህጋዊ አምራቾች/አቅራቢዎች /የችግኝ መግለጫ (Seedling’s Specification) ላይ በተቀመጠዉ መሰረት ቫትን ጨምሮ የአንዱን ችግኝ መሸጫ ዋጋ

  1. ያለትራንስፖርት እና
  2. እስከ ካፋ ዞን ጨታ ወረዳ ኮላና ቀይ ቀበሌዎች (በአንድ መስመር) ከቦንጋ ከተማ 65ኪ/ሜ ፡ ጊምቦ ወረዳ ተጋ ቀበሌ ከቦንጋ ከተማ 40 ኪ/ሜ ድረስ ያለውን የማጓጓዣ ዋጋን ጨምሮ በዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ (Proforma) ሞልታችሁና በኤንቬሎፕ አሽጋችሁ ቦንጋ ከተማ ብሔራዊ ቡና ሙዚዬም ከፍ ብሎ በሚገኘው የናቡ ኢትዮጵያ ደ/ም/ማ/ጽ/ቤት ወይንም በፈጣን SMS በቢሯችን ፖ.ሳ.ቁ 130 ቦንጋ ብላችሁ ከቀን 22/11/2018ዓ.ም እስከ 28/11/2018ዓ.ም በሥራ ሰዓት ዉስጥ እንድታስገቡ እያሳሰብን ጨረታዉ በቀን 29/11/2018ዓ.ም በ 8፡30 ላይ ተጫራቾች ወይንም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት በቦንጋ ከተማ በሚገኘው የናቡ ኢትዮጵያ ደ/ም/ማ/ጽ/ቤት የሚከፈት መሆኑንን እንገልጻለን፡፡

 በጨረታው ለመወዳደር መሟላት ያለባቸው መስፈርቶች

  1. ለ 2018 ዓ.ም የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያለዉ፣
  2. የዘመኑን ግብር የከፈለ፣
  3. የተጨማሪ እሴት ታክስ/ቫት/ተመዝጋቢ የሆነ፣
  4. ለሚከፈለው ገንዘን ሕጋዊ ደረሰኝ መስጠት የሚችል
  5. ከላይ የተጠቀሱትን ህጋዊ ሰነዶች ኮፒ ከጨረታ ዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ጋር አያይዞ ማቅረብ የሚችል፣

ማሳሰቢያ፡

  • የጨረታ ሰነድ ማስገቢያ ቀን ከ ሐምሌ 22-28/2018ዓ.ም ባሉት አምስት ተከታታይ የስራ ቀናት ስለሆነ በ ፖስታ ሳጥን ቁጥር የምትልኩ ተጫራቾች በፈጣን SMS በኩል መላክ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  • የአንዱን ችግኝ ዋጋ ያለ ትራንስፖርት እና ከላይ እስከተጠቀሰው አደራሻ ድረስ ማድረሻ ትራንስፖርት ዋጋን ጨምሮ በሚል በሁለት መንገድ ዋጋ በማቅረብ ሞልታችሁ ማስገባት ይጠበቅባችኋል፡፡
  • ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  1. የሚገዛው የአቮካዶ ችግኝ መግለጫ (Seedling’s Specification)
  • Grafted Hass
  • Grafted Ettinger
  1. ለበለጠ መረጃ የፕሮጀክት ባለሙያ አቶ ልሳኑ ተሾመን በስልክ ቁጥር +251910506379 ማግኘት ይቻላል፡፡
Save Tender