ድርጅታችን የተለያዩ የኮምፒዩተር ጥገና አገልግሎቶችን በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
በኦሮሚያ ደንና ዱር እንስሳት ድርጅት ሸገር ቅርንጫፍ ጽ/ቤት
የጨረታ ማስታወቂያ
ጨረታ ቁጥር 002/2018/19
ድርጅታችን የተለያዩ የኮምፒዩተር ጥገና አገልግሎቶችን በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ተጫራቾች የማይመለስ 300.00 (ሶስት መቶ ብር) በመክፈል የጨረታ ሠነዱን መግዛት የሚችሉ ሲሆን ተጨራቾች ማሟላት የሚገባቸው፡፡
1. በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ያላቸው እና ኮፒውን ማቅረብ የሚችሉ፡፡
2. የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) እና የሥራ መለያ ቁጥር ቲን ቁጥር ያላቸውና ኮፒውን ማቅረብ የሚችሉ፡፡
3. ተጫራቾቹ በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ ስለመኖራቸው የሚገልፅ ማስረጃ ማቅረብ የሚቸሉ መሆን አለባቸው፡፡
4. ተጫራቾች የተጫረቱበትን አገልግሎት በአግባቡ ለመስጠት ባለሙያ እና የሰው ኃይል ያላቸው መሆን አለባቸው፡፡
5. ተጫራቾች ጨረታ ለመወዳደር የሚያስችል ከሊራንስ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
6. የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ያቀረቡትን ጠቅላላ ዋጋ 5% በባንክ በተረጋገጠ በሲፒኦ በድርጅቱ ስም ማስያዝ ይኖርበታል፡፡
የጨረታ ሠነዱን ለቡ መብራት ኃይል ሮያል ከረሜላና ቸኮሌት ፋብሪካ ህንጻ 3ተኛ ፎቅ ላይ ከሚገኘው ቅርንጫፍ ጽ/ቤታችን ከሰኞ እስከ አርብ በሥራ ሰዓት መግዛት ይችላሉ፡፡
ጨረታው ይህ ማሰታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 15 ቀናት ክፍት ሆኖ የሚቆይ ሲሆን በ 16 ኛው ቀን እሁድ ወይም የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዕለቱ ከጠዋቱ በ4፡30 ላይተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎች በተገኙበት ይከፈታል፡፡
መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል መሰረዝ ይችላል፡፡
ለበለጠ መረጃ በስልክ 0912080221/0979238270 መጠየቅ ይቻላል፡፡
በኦሮሚያ ደንና ዱር እንስሳት ድርጅት
ሸገር ቅርንጫፍ ጽ/ቤት
