የፈረስ ቤት ኮንዶሚንየም ቤት ባለቤቶች ኃ/የተ/የህ/ስራ ማህበር የጋራ መኖሪያ ህንፃውን የሕንፃ ጣሪያ፣ የጎሮንዳዮና የፍላሺንግ ጥገና ሥራዎችን በጨረታ አወዳድሮ ማስጠገን ይፈልጋል፡፡
የፈረስ ቤት ኮንዶሚንየም ቤት ባለቤቶች ኃ/የተ/የህ/ስራ ማህበር
የሕንፃ ጣሪያ የጎሮንዳዮና የፍሳሺንግ ጥገና ሥራዎች
የጨረታ ቁጥር ፈ/ቤ/ኮ/03/2018
የፈረስ ቤት ኮንዶሚንየም ቤት ባለቤቶች ኃ/የተ/የህ/ስራ ማህበር የጋራ መኖሪያ ህንፃውን የሕንፃ ጣሪያ፣ የጎሮንዳዮና የፍላሺንግ ጥገና ሥራዎችን በጨረታ አወዳድሮ ማስጠገን ይፈልጋል፡፡
ለጨረታው ውድድር የሚያስፈልገው መስፈርት፡-
1. በጨረታ መወዳደር የሚችሉት የሳኒተሪ እና የሕንጻ ሥራ ተቋራጮች
2. የታደሰ የብቃት ማረጋገጫ፣ የዘመኑ የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ፣ የንግድ ምዝገባ ሰርተፊኬት፣ የግብር ክሊራንስ፣ የመልካም ሥራ አፈጻጸም ደብዳቤ ከጨረታ ሰነዱ ጋር አሟልተው ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡
3. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) ዘወትርከሰኞ እስከ አርብ ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 11፡00 ሰዓት እና ቅዳሜ ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 6፡00 ሰዓት ከማህበሩ ቢሮ ገዝተው መውሰድ ይችላሉ፡፡
4. ተጫራቾች የቴከኒካል፣ የፋይናንሺያል ሰነዶቻቸውን በፖስታ አሽገዉ የተጫራቾች ፊርማ እና ማህተም አርፎባቸውና በአንድ ፖስታ አጠቃለው ማቅረብ አለባቸው፡፡
5. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 7 ቀናት ቆይቶ በ7ኛዉ ቀን በማህበሩ ቢሮ ይከፈታል፡፡
6. ስለሥራው ሁኔታ በበለጠ ለመረዳት ሳይቱን ማየት ግዴታ ነው፡፡
7. ማህበሩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ ከእንግሊዝ ኢምባሲ ወረድ ብሎ ወይም ከሲግናል ወደ እንግሊዝ ኢምባሲ በሚወስደዉ መንገድ
ስልክ 0913517803 / 0940391560 / 011658177
የፈረስ ቤት ኮንዶሚንየም ቤት ባለቤቶች
ኃ/የተ/የህ/ስራ ማህበር
