በቂርቆስ ክፍስ ከተማ ጎተራ ማሳስጫ ጤና ጣቢያ ጨረታ ማስታወቂያ።
በቂርቆስ ክፍስ ከተማ ጤና ጽ/ቤት የቂርቆስ ጤና ጣቢያ
የጨረታ ማስታወቂያ
ከተጫራቶች ሕጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን /2018 /ግብር ከፍለው ፈቃዳቸውን ያደሱ ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታከስ ከፋዮች መሆናቸውን የሚገልጽና፣ ከአቅራቢዎች ዝርዝርውስጥ የተመዘገቡ መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስከር ወረቀት፣ ቫት ሰርተፍኬት እና ቲን ሰርተፌኬት ያላቸው ማቅረብ አለባቸው፡፡
2. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ብቁ ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200.00(ሁለት መቶ ብር ብቻ በመክፈል ከመ/ቤቱ ረዳት ፋይናንስ ኦፊሰር ማግኘት ይችላሉ፡፡
3. ተጫራቾች ለሚጫረቱት የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ የከፍያ ማዘዣ CPO 50000 (ሃምሳ ሺህ) ብር ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
4.ተጫራቾች የሚጫረቱት የጨረታ ሰነድ ሞልተው ኦርጅናል ሰነድ
* ላይ ኦርጅናል እና ኮፒ ሰነድ ላይ ኮፒ በማለት ለየብቻቸው በማሸግ በአንድ ትልቅ ፖስታ ውስጥ ከተው በሁለቱም ዶክመንት ላይ ሕጋዊ የሆነ ማህተም በመምታት ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 10 (አስር) የሥራ ቀናት ውስጥ በመንግስት የስራ ሰዓት ቢሮ ቁጥር 410 በመቅረብ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይችላሉ፡፡
* ተጫራቾች ለሚጫረቱበት እቃ/አገልግሎት ዝርዝር በአንድ እቃ አገልግሎት ሳይሆን በጠቅላላ ድምር ዝቅተኛ ዋጋ መሰረት አሸናፊ ይለያል
* የመብራት፣ ውሃ እና የቤት ኪራይ ከፍያ በጤና ጣቢያው የሚሸፈን ይሆናል
*በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በአስራ አንደኛው የሥራ ቀን ከጠዋቱ 4፡ 00 ተጫራቾች (ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ወይም በሌሉበት ይከፈታል፡፡ ጨረታው የሚከፈትበት ቦታ ጎተራ ማሳለጫ ጤና ጣቢያ 4ኛ ፎቅ በሚገኘው 412 የስብሰባ አዳራሽ ነው፡፡
* የጨረታው አሸናፊ የአሸነፈበትን እቃ/አገልግሎትአገልግሎቶቹን ማንኛውም የማቴሪያል፣ የመሣሪያ ወጪዎች፣ ለግብር እና ለታከስ የሚከፈሉትን ጨምሮ አገልግሎት ለመስጠት የሚያስፈልጉ ወጪዎችን በሙሉ በራሱ መሸፈን አለበት፡፡
* ግዥ ፈጻሚው መ/ቤት ከአሸናፊው ተጫራች ጋር ውል ከመፈራረሙ በፊት በጨረታ ሰነዱ ከተገለጸው የግዥ መጠን ላይ አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ 20% መጨመር ወይም መቀነስ ይችላል፡፡
* መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ
ነው፡፡
አድራሻችን-
ከአጎና ሲኒማ ወደ መስቀል ፍላወር 300 ሜትር ገባ ብሎ በስተ ግራ በኩል ያሬድ ቤተ ክርስቲያን ፊት ለፊት
ስተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር - 0114700844 መጠየቅ ይችላሉ፡፡
በቂርቆስ ክፍስ ከተማ ጎተራ ማሳስጫ ጤና ጣቢያ
