የየካ ክ/ከተማ ወረዳ 11 ፋ/ጽ/ቤት ለ2019 በጀት ዓመት ግልፅ ጨረታ ቁጥር 01/2019 የፅህፈት መሳሪያዎች (ሎት 01) ፣የፅዳት ዕቃዎች (ሎት 02) ፣የደንብ ልብስ (ሎት ዐ3) ፣ ቋሚ ዕቃዎች (ሎት 04) ፣ ህትመት ፣ የተለያዩ ኮምፒተሮች፣ ፎቶ ኮፒ፣ ፕሪንተር፣ ላፕቶፕ ፣ፈርኒቸር ጥገና እና አገልግሎት ግዥ (ሎት ዐ5) ስለሚፈልግ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
የየካ ክ/ከተማ ወረዳ 11 ፋይናንስ ጽ/ቤት
የጨረታ ማስታወቂያ
የየካ ክ/ከተማ ወረዳ 11 ፋ/ጽ/ቤት ለ2019 በጀት ዓመት ግልፅ ጨረታ ቁጥር 01/2019 የፅህፈት መሳሪያዎች (ሎት 01) ፣የፅዳት ዕቃዎች (ሎት 02) ፣የደንብ ልብስ (ሎት ዐ3) ፣ ቋሚ ዕቃዎች (ሎት 04) ፣ ህትመት ፣ የተለያዩ ኮምፒተሮች፣ ፎቶ ኮፒ፣ ፕሪንተር፣ ላፕቶፕ ፣ፈርኒቸር ጥገና እና አገልግሎት ግዥ (ሎት ዐ5) ስለሚፈልግ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም መጫረት ለምትፈልጉ፡-
1. የታደሰ ንግድ ፈቃድ ፎቶ ኮፒ ፣ ለአቅራቢነት የተመዘገቡበትን ማስረጃ ኮፒ ማቅረብ አለበት፡፡
2. በዘርፍ የተሰማራ እንዲሁም የዘመኑን ግብር የከፈለበት ምስክር ወረቀት ፎቶ ኮፒ ማቅረብ የሚችል፡፡
3. የግብር ኮድ መለያ ቁጥር /TIN/ ሰርተፍኬት፣ ተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ተመዝጋቢ የሆነበት ምስከር ወረቀት ፎቶ ኮፒ እንዲሁም በጥቃቅን የተደራጁ ለሚወዳደሩበት ሎት (የዕቃ ዓይነት) እራሱ ማህበሩ አምራች ስለመሆኑ የሚያሳይ ማስረጃ ያለውና ቫት ተመዝጋቢ የሆኑበት ምስከርወረቀት ማቅረብ የሚችል፡፡
4. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ለሎት (01) ብር 15,000 (አስራ አምስት ሺህ) ፣ ለሎት (02) ብር15,000 (አስራ አምስት ሺህ) ፣ ለሎት (03) ብር 15,000 (አስራ አምስት ሺህ) ፣ ለሎት (04) ብር 15,000 (አስራ አምስት ሺህ) ለየብቻው(በየሎቱ) በባንክ የተረጋገጠ CPO (ሲፒኦ) ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡ ሎት (05) ላይ ለሚወዳደሩ CPO (ሲፒኦ) ማስያዝ አይጠበቅባቸውም፡፡ የሚገቡ ሳንፕሎችም ለየብቻ በየሎቱ በማዳበሪያ ከረጢጥ መቅረብ አለባቸው፡፡
5. የጨረታ አሸናፊዎች ባሸነፉት እቃ ብር መጠን የውል ማስከበሪያ 10% በሲፒኦ ብቻ ማስያዝ አለበት
6. ጨረታው በጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ ተከታታይ የስራ ቀናት የሚቆይ ሲሆን በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ተዘግቶ በዛው እለት ከጠዋቱ 4፡30 ተጫራቾች ህጋዊ ውክልና ያላቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ በመንግስት ተቋም በጥቃቅን ለተደራጁ ሰነድ በነፃ እዲወስዱ ከተደራጁበት መ/ቤት የተፃፈላቸውን ደብዳቤ ኦሪጅናል ማቅረብ አለባቸው፡፡
7. የመወዳደሪያ ሀሳብ ፋይናሻልና ቴከኒካል ሁለት በታሸገ ፖስታ ኮፒ እና ኦርጅናል በማድረግ ፋ/ጽ/ቤት በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
8. በየ ሎቱ የጨረታ ሰነዱ የተዘጋጀ ስለሆነ የተዘጋጀው ጨረታ ዝርዝር ሰነድ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የማይመለስ ብር 200/ሁለት መቶ ብር ለእያንዳንዱ ሎት በመክፈል ሰነዱን ከመስሪያ ቤቱ በአካል(በውከልና) ቀርቦ መግዛት ይቻላል፡፡
9. የጨረታ አሸናፊ ድርጅቶች ያሸነፉትን እቃዎች በራሱ ወጪ እስከ መስሪያ ቤቱ መጋዘን ድረስ ማቅረብ አለበት፡፡
10. ተጫራቾች የሚወዳደሩበት እቃ ናሙና ማቅረብ አለባቸው ፡፡ የሚገቡ ሳንፕሎችም(ናሙናዎች) ስየብቻ በየሎቱ በማዳበሪያ ከረጢጥ መቅረብ አስባቸው፡፡
11. ጽ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻ ፡- አዲስ አበባ ከተማ የካ ክ/ከተማ ወረዳ 11 አስተዳደር
ልዩ ቦታ ኮተቤ 02 አለፍ ብሎ ደጃዝማች ወንድይራድ 1ኛ ደረጃ ት/ቤት ፊት ለፊት iኛ ፎቅ ፋይናንስ ጽ/ቤት
ስለ ጉዳዩ ተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈለገዎ በስልክ ቁጠር 011-6-50-80-50
የየካ ክ/ከተማ ወረዳ 1 ፋይናንስ ጽ/ቤት
